Get Mystery Box with random crypto!

ከጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ወቅታዊና | ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹

ከጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ

የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ወቅታዊና ዞናዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:-

ሠላም በሁላችንም እጅ ያለ ትልቅ ሀብት መሆኑን አውቀን በአግባቡ እንከባከበው እንጠቀምበት ።

በሀገራችን እውነተኛ ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅም ይሁን ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ።

የተከበራችሁ በገጠር በከተማ የምትኖሩ የዞናችን ነዋሪዎች፣ አመራሮች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ ሙሑራን፣አርሶ አደሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ ውድ ወጣቶች ፣በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም የምትገኙ የማህበረሰብ አንቂ አካላት፣የፍትህና ፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ሠሞኑን የለውጥ መንግስታችን ሲንከባለል የቆየውን የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ለመመለስ በአንድ በኩል ከውስጥና ከውጪ የተቃጣበትን ፈተና እየመከተ በሌላ በኩል ለህዝቦች ሠላም እና ብልጽግና ጉዞ የመልካም አስተዳደር ተግዳሮት የሆነውን በክልል እንደራጅ ጥያቄን ለመመለስ እየሠራ ይገኛል።

በዞናችን የህዝብ ጥያቄ ለሆኑ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት መንግስት ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ እየሰራ ያለ ሲሆን ይህንንም በቁርጠኝነት ለማከናወን አቅዶ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ።

ይህንን የዞኑ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ተከትሎ ለሕዝብ ቀጣይ አብሮነትና ዕድገት ይበጃል ያለውን ምክረሀሳብ ሕዝቡ በየደረጃው እንድወያይበትና ሕጋዊና ዴሞክራሲያው አግባብ ተከትሎ የውሳኔ ሀሳቡን እንዲያስቀምጥ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው ።

ይህ ጉዳይ በዚሁ መንገድ በውይይት እና በውይይት ብቻ ወደ መግባባትና የጋራ ድምዳሜ ላይ የሚደረስ ሲሆን በህደትም በየ ምክር ቤቱ ቀርቦ እየፀደቀ በህዝበ ውሳኔ የሚጠናቀቅ ሕጋዊ አሠራር ያለው ግልጽና የማያሻማ ሐቅ ነው ።

ይህ ጉዳይ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ሙሉ የነቃ ተሳትፎ የሚፈልግ በመሆኑ የዞናችን ወጣቶችን ጨምሮ ሌሎች በውይይቱ እስከ አሁን ያልተወያዩ አካላትን በሙሉ በተቀመጠው የውይይት የጊዜ ሠሌዳ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እያወያየን ባለንበትና ውይይቱ ባልተጠናቀቀበት በአሁኑ ሰዓት ሌላ ትርጉም በመስጠት በተለያዩ የዞናችን ወረዳዎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ልንወጣ ነው የሚሉ የተለያዩ ወሬዎችና አሉባልታዎች በመበራከታቸው በህዝባችን ውስጥ ስጋት አሳድሯል ።

መላው ህዝባችን እንዲያውቀው የምንፈልገው መንግስት ያቀረበው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ያለመኖሩንና ሰላማዊ ሰልፍ እንወጣለን ብሎ ጥያቄ ያቀረበ ግለሰብም ሆነ ቡድን ያለመኖሩን ነው ።

በመሆኑም የህዝባችን ሰላምና ደህንነት ተጠብቆ እንዲቀጥል ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነት እንዲወስድና ከቤተሰብ ጀምሮ ስለ ሰላም እንዲመካከርና እንዲጠብቅ በአጽንኦት እናሳስባለን።

በመቀጠልም የህዝባችን የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ህጉን ተከትሎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተጠየቀና መንግስትም ይህንን አስመልክቶ ከሁሉም ከህብረተሰብ ክፍል ጋር በግልጽ እየተወያየ በመሆኑ በትዕግስት መጠበቅ ያለብን ሲሆን ይህንን ባልተገባ መንገድ በማዛባት በውስጥም በዙሪያውም ሰላማችንን ለማደፍረስ የሚቋምጡ ኃይሎች እንዳሉ ተገንዝበን ምንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ ያልተፈቀደና የማይሄካድ መሆኑን በጥብቅ እንገልጻለን ።

በሰላማዊ ሰልፍ ይሁን በሌላ መልኩ ሰላም ለማደፍረስ የሚሞክር ሃይል ካለ ህዝቡ እንዲያወግዝና የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል የፀጥታ ሃይሉ በጠንቀቅ ላይ ያለ መሆኑን እየገለፅን ከዚህ ሁኔታ ውጪ ለሚፈጠር ማንኛውም ክስተት የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን ።

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01