Get Mystery Box with random crypto!

ሰራዊታችን ዛሬም እንደቀደመው ሁሉ የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ መምታት የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጁነት | ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹

ሰራዊታችን ዛሬም እንደቀደመው ሁሉ የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ መምታት የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጁነት እንዳለው የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ገለፁ፡፡

የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን ሊቃጡብን የሚችልን ማንኛውንም አይነት ትንኮሳ መክቶ ድባቅ መምታት የሚያስችል ሙሉ ዝግጅት እንዳለው የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜ/ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

ጀኔራል መኮንኑ እንደተናገሩት ሰራዊታችን በስነ-ልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በቴክኒክ ያለውን አቅም ከምንጊዜውም በላይ እያሳደገ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሽብርተኛውን ህወሃትን ሆነ ሌሎች ተላላኪ ሽብርተኞችን ድል አድርጎ የአገራችንን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ገንብቶ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሰራዊታችን ከመንግስትና ከህዝባችን ሊሰጠው የሚችልን ማንኛውንም አይነት ተልዕኮ ተቀብሎ በማንኛውም የሀገራችንን አካባቢ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ከመላው ህዝባችን ጋር በመተባበር ድል አድርጎ ሀገር መከታ መሆኑን ለማስመስከር የሚያስችል ወታደራዊ፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ዝግጅቱን አጠናክሮ እንደሚገኝ ሜ/ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01