2020-09-16 08:13:52
ኦሪት ዘፍጥረት 2፥1-3
1.“ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።”
#ሠራዊቶቻቸውም : - በውስጣቸው ያሉት ፍጥረታትንም ሁሉ ፈጥሮ ጨረሰ።
@yemetshaf_qdus_tinat
2.“እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።”
#ሰባተኛው_ቀን : - ብርሃንና ጨለማ የተለያዩበት ከስነ ፍጥረት የመጀመርያው ቀን(እሁድ) አንስተን አዳም እስከ ተፈጠረበት(አርብ) ያለውን የብርሃንና የጨለማ ዑደት(ዙር፣መፈራረቅ) ብንቆጥር 6ቀን ይሆናል ስለዚህ ሰባተኛዋ ቀን ቀዳሚት ሰንበት (የመጀመርያዋ ሰንበት) በአይሁድ "sabbath" የምትባለዋ ናት።የመጀመርያዋ ሰንበት ወይም ቀዳሚት ሰንበት (በተለምዷዊ አጠራር ቅዳሜ) የመባልዋ ምክንያት #እሁድም ሁለተኛዋ ሰንበት(የክርስቲያን ሰንበት፣ሰንበት ዓባይ፣የጌታ ቀን) ተብላ ስለምትጠራ ነው።ስለዚህ እግዚአብሔር ከመፍጠር ያረፈው በሰባተኛይቱ ቀን ቀዳሚት ሰንበት ላይ ነው።
@yemetshaf_qdus_tinat
#ዐረፈ : -በስድስቱ ቀናት ከፈጠራቸው ፍጥረታት ተጨማሪ መፍጠርን #አቆመ #ተወ ማለት ነው እንጂ ፈጣሪ ውጣ ውረድ ድካም የለበትም!!።ይህ ቃል እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለው ግንኙነት መገለጫም ነው። እንዴት? በሰባተኛይቱ ቀን ከስራው ሁሉ ዐረፈ ካለ በኋላ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አይልም አንድ የዕረፍት ቀን ላይ ነው።ፍጥረቱ የሆነው የሰው ልጅ ደግሞ ወደእርሱ እንዲመጣ(እርሱን እንዲያውቅ) በቃሉም እየኖረ እንዲያመልከው ከፈጣሪው ጋር ህብረት እንዲያደርግ ይፈልጋል።
@yemetshaf_qdus_tinat
እስራኤል ከግብፅ ሲወጡ ለአብርሃም ወደ ማለለት ምድር ይገቡና እርሱን እያመለኩ በመንፈሳዊ ሐሳብ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲኖራቸው ነበረ ዓላማው ይህም ለዘለአለማዊው ከእግዚአብሔር ጋር የመኖርን ምሳሌ ነው።በእምነት ቃሉን ሰምተው እየታዘዙት መኖር በመንፈስ ዕረፍቱን መውረስ መካፈል ነው።ነገር ግን ከግብፅ የወጡት ቃሉን ሰምተው አላመኑም ባለመታዘዝ አሳዘኑት ፈጣሪም ከኔ ጋር አንድነት ዕድል ፈንታ የላቸውም አለ።
@yemetshaf_qdus_tinat
“ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም፤”— ዘኍልቁ 14፥23
መዝ94(95)፥10-11 “ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ።ወደ #ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ።”
ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ዕረፍት በዕብራውያን መልእክቱ ሲያብራራው እንዲህ ይላል
“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር #በእምነት_ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።ስለ #ሰባተኛው_ቀን በአንድ ስፍራ፦ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤በዚህ ስፍራም ደግሞ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም።እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ #ዛሬ_ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ #በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ #አንድ_ቀን እንደ ገና ይቀጥራል(ይወስናል)።” ዕብ4፥1-7
@yemetshaf_qdus_tinat
3.“እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።”
#ባረከው_ቀደሰውም : - መልካም ነገር እንዲያስገኝ መልካም እንዲሆን መረቀው ለራሱም ለየው።
#በረከቱም እስራኤላውያን በነቢዩ ሙሴ መሪነት ከባርነት ወጥተው አምላካቸውን አውቀው ህግም በተሰጣቸው ጊዜ ከባርነት ወጥተው ብቻ ሳይሆን ከስጋ ስራም በእግዚአብሔር ስራና ዕረፍት ምሳሌ 6 ቀን ሰርተው በሰባተኛይቱ ቀን እንዲያርፉ ሲታዘዙ፤ከሰማይ ይዘንብላቸው የነበረው መና ለነገው ማሳደር አልተፈቀደላቸውም ለቀኑ በቅቷቸው ካደረ መናው ይበላሻል ለየቀኑም አዲስ የዘነበ ይበሉ ነበር በስድስተኛይቱ ቀን ግን ከዘነበው መና የሁለት ቀን ይሰበስቡና በሰባተኛይቱ ቀን መናም አይዘንብም ያደረውም አይበላሽም አርፈው ይመገቡት ነበር (ዘጸ16)።
ዕብራውያን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
¹⁰ ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
¹¹ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።
76.5K views05:13