Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawimeker — መንፈሳዊ የህይወት ምክር
የቴሌግራም ቻናል አርማ menfesawimeker — መንፈሳዊ የህይወት ምክር
የሰርጥ አድራሻ: @menfesawimeker
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.40K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ የህይወት ምክር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ወዳጄ ሆይ ! መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡ ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡ እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡
ለ አስተያየት ወይም መንፈሳዊ ጥያቄ ካሎት
@menfesawimekerbot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2020-09-03 00:28:23 #አንጨነቅ

በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡

ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)

ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
55.8K views21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-02 09:51:41 "ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡

እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ወደ_ኦሎምፒያስ)

ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
53.5K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-01 13:50:33 "ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል። ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው። የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።"
(መጽሐፈ ምሳሌ፡ 16፥21-24)
42.3K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-29 08:12:39 #ኹሉንም_ነገር_ለእግዚአብሔር_እንስጠው
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ወርቅን የሚያነጥር ሰው አንዲትን የወርቅ ቅንጣት ወደ እሳት ውስጥ ጨምሮ እጅግ ንጹህ እስክትኾን ድረስ ይጠብቃታል፡፡ እግዚአብሔርም ልክ እንደዚሁ ሰዎች እስኪነጹ፣ እስኪለወጡና ባገኛቸው ነገር ጥቅም እስኪያገኙ ድረስ ፈተና ውስጥ እንዲቆዩ ይፈቅዳል፡፡ ይህ ደግሞ ከጥቅምም እጅግ ከፍ ያለ ጥቅም ነው፡፡
ስለዚህ ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም ተስፋ ሊቈርጥ አይገባውም፡፡ ያ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያኽል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኵሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንሔድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቈርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡
ይህን በማስመልከትም ጠቢቡ ሰው እንደዚህ ሲል መክሮናል፡- “ልጄ ሆይ! ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሔድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ፤ ልብህን አቅና፤ ኹልጊዜ ታገሥ፤ አታወላውልም፤ በመከራ ብትጨነቅም አትጠራጠር” /ሲራ.2፥1-2/፡፡ “ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ስጠው፡፡” ለምን? እግዚአብሔር ከዚያ መከራ መቼ እኛን ማውጣት እንዳለበት ያውቃልና፡፡ ስለዚህ ኹሉንም ለእርሱ ልንሰጥ፣ ዘወትር እርሱን ልናመሰግን፣ ኹሉንም ነገር - ጥቅምም ይኹን ቅጣት - በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፤ ይህም ቢኾን ለእኛ ረብሕ የሚኾን ነውና፡፡ አንድ ሐኪም፥ ሐኪም የሚባለው ታካሚውን ገላዉን ሲያጥበውና ሲመግበው እንዲሁም ደስ ወደሚያሰኝ ስፍራ ሲወስደው ብቻ አይደለም፤ በእርሱ (በታማሚው) ሰውነት ላይ የቀዶ ጥገና ምላጭና ቢላ ሲያሳርፍም ጭምር ሐኪም ነው፡፡ አባትም አባት የሚባለው ልጁን ሲንከባከብ ብቻ አይደለም፤ የገዛ ልጁን ከቤት ሲያስወጣው፣ ሲገሥጸው፣ ሲገርፈውም ያው አባት ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔር ከሐኪሞችም በላይ ሰውን ወዳጅ እንደ ኾነ በማወቅ፥ ምን ዓይነት የሕክምና ዓይነት እንደሚሰጠን በጥልቀት አንጠይቅ፤ ወይም ደግሞ ለደረሰብን መከራ እርሱን ተጠያቂ አናድርግ፡፡ ከዚህ ይልቅ እርሱ የወደደውን ነገር - ቅጣትም ይኹን ቅጣት የሌለው ነገር - ብቻ ምንም ይኹን ምን በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፡፡ በየትኛውም መንገድም ቢኾን የእርሱ ፈቃድ እኛ እንድንድንና ከእርሱ ጋር አንድ እንድንኾን ነውና፡፡ የትኛው መንገድ ለእኛ እንደሚጠቅምም እርሱ ያውቋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የትኛው መንገድ ወደ እርሱ እንደሚመልሰው ያውቃል፡፡ ኹላችንም እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ልንድን እንደምንችል ያውቃል፡፡ በመኾኑም የሚመራን በዚህ እኛ በምንድንበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ወደየትኛውም መንገድ ቢወስደንም - ልክ እንደ መጻጉዑ - እርሱ እንደሚያዘ’ን ተከትለን መሔድ እንጂ ትልቁ ጉዳያችን በለስላሳና በቀላል አልያም ደግሞ በከባድና በሸካራ ጎዳና እንድንሔድ የሚያዘ’ንን ትእዛዝ መኾን የለበትም (ልንሔድበት የሚገባ’ው መንገድ እርሱ ስለሚያውቀው እንዲሁ መታዘዝ እንጂ የመንገዱን ከባድነት ወይም ቀላልነት የእኛ አጀንዳ ሊኾን አይገባውም፡፡)

(ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልእክታት)
52.0K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-28 08:50:20 ‟መብረቅ ሲጮህ ሰው ሁሉ እንደሚደነግጥ የአንቺንም ስም ሲሰማ ዲያቢሎስ ይደነግጣል። አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ እረፍት አላገኘምና ነው። በአንቺ ታመመ በልችሽ መስቀል ተሰቃየ ስለሆንም ከፍጥረት ሁሉ አንቺን ይጠላል”።
(ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
44.5K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ