Get Mystery Box with random crypto!

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_enaseb — Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠 P
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_enaseb — Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_enaseb
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.23K
የሰርጥ መግለጫ

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon.
''There is no health without Mental Health.''
Contact @FikrConsultSupportbot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-18 17:02:16
ልባም ሕይወት አዕምሮና ስብዕናን የማሳደግ ስልጠና!

በኒውሮ ሊንጉዊስቲክ ፕሮግራሚንግ የተቃኘዉ የ30 ሰዓት (ሶስት ሳምንት) ስልጠና ሰኞ ነሃሴ 16፣ 2014 ይጀምራል።

ስልጠናውን ከሚከተሉት በሚመችዎ ሰዓት መርጠው መሳተፍ ይችላሉ፦
ከሰዓት ከ8፡00 - 10፡00
ምሽት ከ12፡00 - 2፡00

ቦታ፡ ቫምዳስ ሲኒማ (መገናኛ ቶታል አጠገብ)

ያለው ውስን ቦታ ስለሆነ ስልጠናውን ለመካፈል በስልክ ወይም በቴሌግራም ቁጥር +251974046870 ስምዎን ቴክስት ያድርጉ።

@melkam_enaseb
1.4K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 16:58:16
እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@melkam_enaseb
1.2K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:12:03
ነፃ ስልጠና!

በኖቫ የስልጠና ማዕከል የሚዘጋጀውን ሳምንታዊ የስነልቦና ስልጠናና ውይይት ይካፈሉ፡፡ በየሳምንቱ በሚመረጡ ርዕሶች አመለካከትዎንና ሕይወትዎን የሚቀይሩ ቁም ነገሮች ይገብዩ፡፡

የሳምንቱ አሰልጣኝና አወያይ:- ናሁሰናይ ፀዳሉ

ሀሙስ፡ ነሃሴ 12, 2014
ከ11:30 ጀምሮ

ውስን ቦታዎች ስላሉ በስልክ +251912664084 በመደወል ቀድመው ወንበር ይያዙ፡፡

አድራሻ በምስሉ ላይ ያገኛሉ።

@melkam_enaseb
1.4K viewsedited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 07:27:48
የሥነ ባሕርይ ሕክምና (Behavioral Therapy)

የሥነ ባሕርይ ሕክምና የአእምሮ ጤና መታወክን ለማከም የሚደረጉ የሕክምና ዓይነቶችን አቅፎ የያዘ ነው፡፡ ማንነትን የሚያበላሹ እና ጤናማ ያልሆኑ ባሕርያትን ለመለየት እና ለመለወጥ ይረዳል።

የሥነ ባሕርይ ሕክምና ሁሉም የሰው ልጅ ባሕርያት በትምህርት የመጡ እና መለወጥ የሚችሉ ናቸው በሚለው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ነው። ሕክምናው አብዛኛውን ጊዜ በወቅቱ ባሉ የባሕርይ ችግሮች እና እንዴት መቀየር ይቻላል በሚለው ላይ ያተኩራል።

የሥነ ባሕርይ ሕክምና ለማን ይጠቅማል?

የሥነ ባሕርይ ሕክምና የተለያዩ ዓይነት የአእምሮ ጤንነት እክል ላጋጠማቸው ሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል።

ከእነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ፤

- ለድባቴ
- ለጭንቀት
- በቀላሉ የመደናገጥ እክል (panic disorder)
- ከመጠን ለአለፈ ቁጣ እና ብስጭት
- የአመጋገብ ሥርዓት መዛባት (eating disorder)
- በአሰቃቂ ሁኔታዎች ውስጥ ከአለፉ በኋላ የሚፈጠር ጭንቀት (post traumatic stress disorder)
- ተለዋዋጭ የስሜት መዋዥቅ (bipolar disorder)
- በሕፃናት ላይ የሚታይ ትኩረት እና ዕረፍት ማጣት (ADHD)
- ከፍተኛ ፍርሃት (phobias)
- ራስን የመጉዳት ባሕርይ ላለባቸው ሰዎች
- ለሱስ

#Wecare

@melkam_enaseb
1.7K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 07:27:17
#Dailytips

ሁሌም ማለዳ ከእንቅልፍህ ስትነቃ ሁለት ምርጫዎች አሉህ፦

አንድም ወደ አልጋህ መመለስ እና ህልምህን መቀጠል ወይም ተነስተህ ህልምህን በውኑ አባረህ መያዝ።

መልካም የስራ ሳምንት!

@melkam_enaseb
1.3K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 07:43:57
#ወዳጄ!

ስትበላ ድሀ አደጎችን፣ ስትጠጣ በረኸኞችን፣ ስትለብስ የተራቆቱትን፣ ወደ ቤትህ ስትገባ ጎዳና የወደቁትን፣ ስትተኛ ማረፊያ ያጡ በሽተኞችን፣ ስትሠራ ሥራ ያጡትን፣ ስትራመድ እግር አልባዎችን፣ አስብ። ሁሉን መርዳት ባትችል እንኳ' አንዱን ደግፈህ የዓለምን ሥቃይ ቀንስ።

#የማለዳድምፅ

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb
1.6K views04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 11:16:14
ነፃ የልባም ሕይወት ስልጠና እንዲሳተፋ ተጋብዘዋል!

ኒውሮ ሊንጉስቲዊክ ፕሮግራሚንግ ህልማችንን ከተግባር ጋር የምናገናኝባቸውን ጠንካራ ስልቶች ቀላል በሆነ መንገድ ያስተምረናል። ውስብስብ የነበረውን ህልማችንን አቅልሎና አጥርቶ መንገዳችንን ግልፅ ያደርገዋል።

ከሁሉም በላይ ይህን ፍላጎታችንን ዕውን ማድረግ የሚችል ስብዕና መፍጠር የምንችልበትን መንገድ ያስተምረናል።

ስልጠናው ከ15 አመት በላይ በሙያው ልምድ ባለው አስለጣኝ ይሰጣል።

ቅዳሜ፡ ነሃሴ 07, 2014
ሰዓት፡ 4፡00 - 06፡00
ቦታው፦ መገናኛ ቶታል ቫምዳስ ሲኒማ

ስልጠናውን ለመካፈል በስልክ +251974046870 ደውሉው ይመዝገቡ።

@melkam_enaseb
1.7K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:20:29
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን|
International Youth Day

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ከወጣቶች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዓለም አቀፉ ማሀበረሰብ ዘንድ ልዩ ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል እ.ኤ.አ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ኦገስት 12 (ነሀሴ 6) ቀን ይከበራል፡፡

ዘንድሮ ቀኑ 'Intergenerational Solidarity: Creating a World for All Ages' ‘በትውልዶች መደጋገፍ ለሁሉም የእድሜ ክልል የምትሆን ዓለም መፍጠር’ በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

መሪ ቃሉ የዘላቂ ልማት ግቦችን (Sustainable Development Goals (SDGs)) ለማሳካት የሁሉም ትውልድ ርብረብ ወሳኝ መሆኑ እንዲተኮርበት ለማስገንዘብ የተቀረፀ ነው፡፡ በተጨማሪም በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ትብብርና መደጋገፍን በማበላሸት በወጣቶች እና በአረጋውያን እንዲሁም አጠቃላይ በማህበረሰቡ ላይ ጎጂ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

#መልእክታችን፦ ወጣቶች የነገ የሀገርን መልክ መመልከቻ መስታወቶች ናቸው፡፡ እንደ ወጣት ተምሮ ማደግ፣ ሰርቶ መለወጥ ማይሻ ወጣት የለም ስለዚህ ፍሬያማ ህይወትን ለመኖር ኑር!

Happy International Youth Day!

@melkam_enaseb
1.5K viewsedited  07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 08:20:53
አመስግን!

"ደስታህን የሰረቀው ምንድን ነው? ገንዘብ ስለሌህ ነው? እዳ ስላለብህ ነው? ህይወትህ አሰልቺ ስለሆነ ነው?

ብቸኛው ማድረግ ያለብህ ቅድሚያ ማመስገን ነው፤ ምስጋና የጎደለውን ነገር ሁሉ ይሞላል ባለን ደስተኛ እንሁን፤ ስለሁሉም ነገር ተመስገን እንበል፤ ተመስገን ማለት ትኩረቴ በችግሬ ላይ ሳይሆን በደስታዬ ላይ ብቻ ነው ማለት ነው።'' - ዳዊት ድሪምስ

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb
1.4K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:40:42
የእናት አእምሮ ጤና፤ ልጇ ደህና።

ዶክተር ዘላለም የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ነው። አንዲት እናት ልጇን ይዛ እሱ ጋር ትመጣና በተደጋጋሚ ልጇን ታሳክማለች። የህመሟ መንስኤ አጥጋቢ ስላልሆነለት ስለኑሮዋቸው ይጠይቃታል። በኋላ እንደተረዳው ህፃኗ ልጅ የምትታመመው ወላጆቿ ሲጣሉ ነው። ሲጣሉ እናቷ በጣም ትናደዳለች ሆኖም ንዴቷን ለባሏ መግለፅ አትችልም። ከዛ ልጅቷ ትታመማለች። ዶክተር ዘላለም "ዝም ብዬ ልጇን ከማክም እናት የአእምሮ ህክምና ክፍል ብትታይ ይሻላል።" ብሎ ወደ አእምሮ ህክምና ክፍል ይልካታል።

የአእምሮ ህክምና ክፍል ከታየች በኋላ Munchausen syndrome by proxy እና የDepression ህመም እንዳለባት ተነግሯት የአእምሮ ህክምና ጀመረች።

የMunchausen ህመም ሰዎች ከሰዎች ትኩረት እና አዘኔታ ለማግኘት ሳይታወቃቸው የሚፈጠር የአእምሮ ህመም ነው። By proxy ሲሆን በልጅ ህመም ትኩረትና አዘኔታ ለማግኘት የሚደረግ ከግንዛቤ ውጭ የሆነ ህመም ነው።

እናት የአእምሮ ህክምና አድርጋ ደህና ስትሆን ልጇ መታመሟ ቀረ። ዶክተር ዘላለም ልጇን ሳትታመም በቀጠሮ ይዛት እንድትመጣ ነገራት። እናት ደስተኛ ናት ልጇ ደግሞ ተስማምቷት ድንቡሽቡሽ ብላለች።

#Mentalwellness

@melkam_enaseb
1.5K views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ