Get Mystery Box with random crypto!

የሥነ ባሕርይ ሕክምና (Behavioral Therapy) የሥነ ባሕርይ ሕክምና የአእምሮ ጤና መታወ | Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የሥነ ባሕርይ ሕክምና (Behavioral Therapy)

የሥነ ባሕርይ ሕክምና የአእምሮ ጤና መታወክን ለማከም የሚደረጉ የሕክምና ዓይነቶችን አቅፎ የያዘ ነው፡፡ ማንነትን የሚያበላሹ እና ጤናማ ያልሆኑ ባሕርያትን ለመለየት እና ለመለወጥ ይረዳል።

የሥነ ባሕርይ ሕክምና ሁሉም የሰው ልጅ ባሕርያት በትምህርት የመጡ እና መለወጥ የሚችሉ ናቸው በሚለው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ነው። ሕክምናው አብዛኛውን ጊዜ በወቅቱ ባሉ የባሕርይ ችግሮች እና እንዴት መቀየር ይቻላል በሚለው ላይ ያተኩራል።

የሥነ ባሕርይ ሕክምና ለማን ይጠቅማል?

የሥነ ባሕርይ ሕክምና የተለያዩ ዓይነት የአእምሮ ጤንነት እክል ላጋጠማቸው ሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል።

ከእነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ፤

- ለድባቴ
- ለጭንቀት
- በቀላሉ የመደናገጥ እክል (panic disorder)
- ከመጠን ለአለፈ ቁጣ እና ብስጭት
- የአመጋገብ ሥርዓት መዛባት (eating disorder)
- በአሰቃቂ ሁኔታዎች ውስጥ ከአለፉ በኋላ የሚፈጠር ጭንቀት (post traumatic stress disorder)
- ተለዋዋጭ የስሜት መዋዥቅ (bipolar disorder)
- በሕፃናት ላይ የሚታይ ትኩረት እና ዕረፍት ማጣት (ADHD)
- ከፍተኛ ፍርሃት (phobias)
- ራስን የመጉዳት ባሕርይ ላለባቸው ሰዎች
- ለሱስ

#Wecare

@melkam_enaseb