Get Mystery Box with random crypto!

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_enaseb — Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠 P
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_enaseb — Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_enaseb
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.23K
የሰርጥ መግለጫ

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon.
''There is no health without Mental Health.''
Contact @FikrConsultSupportbot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-10 13:41:59 የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀን ከ500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአዕምሮ ህክምና እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

በተገባደደዉ የ2014 በጀት ዓመት 130ሺ ለሚደርሱ ታካሚዎች በተመላላሽ ህክምና ለመስጥት ሆስፒታሉ አቅዶ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ለ128,129 ታካሚዎች በተመላላሽ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል፡፡ ከ1930 ዓ.ም ጀምሮ በአዕምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ሆስፒታሉ በአሁን ሰዓት በቀን ከ500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአዕምሮ ጤና ህክምና እየሠጠ መሆኑን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዩ የኔአለም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የአዕምሮ ጤና አገልገሎቱ ባልተማከለ ሁኔታ በሁሉም ጤና ተቋማት ተደራሽ ማድረግ እንዲቻል ሆስፒታሉ የተቀናጀ የማህበረሰብ የአዕምሮ ጤና አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ስርና በአዲስ አበባ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለሚገኙ 28 ጤና ጣቢያዎች የባለሙያ እገዛ በማድረግ ያልተማከለ የማህበረሰብ አእምሮ ጤና ክብካቤ አገልገሎቱን በበጀት ዓመቱ እንዲጀምሩ ማድረግ መቻሉንም አስታውቋል፡፡

ሆስፒታሉ በተጨማሪም በመቂዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ባለሙያ መድቦ በማሰራት፤ በጎርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል፣ በሰዋሰዎ ገነት የህፃናት፤ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ተቋማት ላይ ደግሞ የመድሃኒት ድጋፍን ጨምሮ ማህበራዊ አገልግሎት መስጠቱን አቶ አብዩ ተናግረዋል፡፡ ሆስፒታሉ በበጀት ዓመቱ የተመላላሽ ህክምናን አገልግሎት ጥራት ማሻሻልን ትኩረት አድርጎ መስራቱን የገለጹት ኃላፊዉ የተመላላሽ ታካሚ የቆይታ ግዜ ወደ አንድ ሰዓት ለማድረስ እቅድ ተይዞ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የእቅዱን ያህል ባይሆንም ወደ አንድ ሰዓት ከ18 ደቂቃ ማድረስ መቻሉ ተነግሯል፡፡ (ብስራት ራዲዮ)

@melkam_enaseb
1.6K views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 13:41:57
1.3K views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ