2022-07-18 11:24:42
ሽንት በምንሸናበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት መንስኤውና መፍትሄው
ሽንት በምንሸናበት ጊዜ የህመም ወይም የማቃጠል ስሜት መሠማት በህክምና ቋንቋ ዲስዮሪያ (Dysuria) ይባላል። ይህ የማቃጠል ስሜት በምንሸናበት ጊዜ ወይም ከሸናን በኋላ ይከሰታል።
ይህ ችግር በተፈጥሮአዊ የመራቢያ አካል አቀማመጥ ምክንያት በሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል። ሴቶች አጭር የሽንት ፊኛ ቱቦ አላቸው (ሽንትን ከሽንት ፊኛ ወደ ውጪ የሚያወጡ)። እና የሽንት ቧንቧ ሥርዓት ከሰገራ መውጫ ቀዳዳና ከሴት አባላዘር በጣም በቅርብ እርቀት ተጠጋግተው ይገኛሉ።
ሽንት ከሸናሁ በኋላ ለምን የማቃጠል ስሜት ይሰማኛል?
ይህ የማቃጠል ስሜት ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዘ ነው። ኢንፌክሽኑ በማንኛውም የሽንት ቧንቧ ሥርዓት ክፍል ውስጥ ሊከሰት ይችላል።
በአንድ ክፍል ላይ ከጀመረን በኋላ ካልታከምነው ወደተለያዮ ክፍሎች ይዛመታል። በዚህም ኢንፌክሽን ዩሬትራ፣ የሽንት ፊኛ፣ ዩሬተር እና ኩላሊት የመጠቃት ዕድል አላቸው።
ሽንት ከሸኑ በኋላ የማቃጠል ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፦
1. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
ይህ በጣም ከተለመድት ምክንያቶች ውስጥ አንድ ነው። ይህ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መነሾ ወደ ሽንት ሥርዓት የመግባት ዕድል ባገኙ ባክቴሪያዎች ምክንያት ይከሰታል። ከዚያም ወደተያያዙ የሰውነት ክፍሎችና ዩሬትራ ይዛመታል። የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሌሎች ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:-
የሆድ ህመም ወይም በሚሸኑበት ጊዜ ህመም።
ፒንክ ወይም ቀይ ቀለም ያለው ሽንት።
ከወትሮው ለየት ያለ ጥሩ ያልሆነ ሽታ ያለው ሽንት።
የሽንት ፊኛቸው ባዶ ቢሆን እንኳን ለመሽናት መጣደፍ/መቸኮል።
የጀርባ ህመምና አጠቃላይ የህመም ስሜት መሰማት።
በዳሌ አካባቢ የምቾት ማጣት ስሜት።
ይህ ኢንፌክሽን ከሽንት ቧንቧ መስመር ካለፈ ለምሳሌ ወደ ኩላሊት ከተዛመተ ምልክቶቹ በደንብ ይወጣሉ ከነዚህም ምልክቶች መካከል ፦
ትኩሳት
የጀርባ ህመም
የጎን ወይም ዳሌ አካባቢ ህመም
ማቅለሽለሽ
ማስመለስና
ተቅማጥ ናቸው።
ለሽንት ቧንቧ የሚያጋልጡ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:-
በዕድሜ የገፉ ሰዎች
የስኳር በሽተኞች
ሴቶች
የኩላሊት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች
እርጉዝ ሴቶች
በመጠን ትልቅ የሆነ ፕሮስቴት ዕጢ ያላቸው ሰዎች (በተለይ በዕድሜ የገፉ ሰዎች)
የሽንት መሽኒያ ቱቦ ወይም ካቲተር የተገጠመላቸው ሰዎች።
2. በግብረ - ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች
ባክቴሪያዎች በምንሸናበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ለመከሰቱ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው። ይህም የብልት ኸርፐስ፣ ክላሚዲያ እና ጨብጥ ይጠቀሳሉ። ሌሎች ከግብረ - ሥጋ ግንኙነት ኢንፌክሽን ጋር የሚያያዙ ምልክቶች እነሆ:-
ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ
ከማቃጠል ስሜት በተጨማሪ የማሳከክ ምልክት
3. የብልት ኢንፌክሽን
የብልት ኢንፌክሽን ለምሳሌ እንደ ይስት ኢንፌክሽን (Yeast Infection) የማቃጠል ስሜት ከማስከተላቸው በተጨማሪ በብልት አካባቢ ማሳከክና መቅላት (Redness) ምልክቶች ያስከትላሉ።
ሌሎች የይስት ኢንፌክሽን ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ:-
ያልተለመደ ነጭ አይብ የመሰለ የብልት ፈሳሽ
በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የህመምና የማቃጠል ስሜት መሰማት
በውጫዊ የብልት አካባቢ የህመምና የማሳከክ ስሜት መሰማት።
4. የዩሬትራ አቀማመጥ (Urethral structure)
ይህ ችግር በብዛት ወንዶችን የሚያጠቃ ሲሆን በዙሪያው ያሉ ስጋዎች ቀልተው በሚያብጡበት ጊዜ ወይም ጠባሳ በሚኖርበት ጊዜ ይፈጠራል። ከዚያም ሽንት ከሰዉነታችን በነፃነት መወገድ ስለሚሳነው በሚሸኑበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ይሰማዎታል።
5. ሌሎች ምልክቶች
ጠንከር ያለ የግብረ ሥጋ እንቅስቃሴ ዩሬትራ እንዲቆጣ ያደርገዋል። ሌሎች አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ፦ ብስክሌት ወይም ፈረስ መጋለብ በውጫዊው የብልት አካባቢ ሰበቃና (ፍጭት) ቁጣ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ለተለያዩ ሳሙናዎች፣ የሽንት ቤት ወረቀቶች፣ አረፋማ መታጠቢያዎችና የውበት መጠበቂያዎች አለርጂ ካለብዎ ከሸኑ በኋላ የማቃጠል ስሜት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ሃኪምዎን ማናገር ያለብዎት መቸ ነው?
ከወንድ ወይም ሴት የመራቢያ አካል ውስጥ ያልተለመደ ፈሳሽ የሚወጣ ከሆነ
ከህክምና በኋላ የህመሙና የማቃጠል ስሜት የማያቆም ከሆነ
በጎን ወይም በጀርባ የሰውነት ክፍልዎ ላይ የህመምና የትኩሳት ስሜት ከተሰማዎ
የሽንት ፊኛ ወይም የኩላሊት ጠጠር በሚወጣዎ ጊዜ ከባድ ህመም ካለዎ
በሽንትዎ ውስጥ ደም ካዩ ናቸው
ይህን ችግር በራስዎ እንዴት ማከም ይችላሉ?
በዛ ያለ ውሃ ይጠጡ
ሽንትዎ ሲመጣ ቶሎ ይሽኑት
በጠርሙሱ ላይ በታዘዘው መሠረት አላካላይን ግራኒውልስ ይጠቀሙ።
ፓርስሊ ውሃ ይጠጡ
ኩከምበር ይመገቡ
ክሬይንቤሪ ጭማቂ ይጠጡ
ብሉቤሪስ ይመገቡ
ሆርስ ራዲሽ ይመገቡ
120 viewsEshetie Bishaw, 08:24