Get Mystery Box with random crypto!

ሽበት ለሚያስቸግረው   የአንድ ሰውን እድሜ ተንተርሰው ከሚመጡ የተፈጥሮ ለውጦች መሀል አ | Medical Laboratory

ሽበት ለሚያስቸግረው

  የአንድ ሰውን እድሜ ተንተርሰው ከሚመጡ የተፈጥሮ ለውጦች መሀል አንደኛው የሽበት መውጣት ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሽበት ሁልግዜ የእድሜ መግፋትን ብቻ አመላካች አይደለም።

የአንድ ሰው ፀጉር ያለግዜው ሲሸብት ታዲያ፣ በማህበረሰብ ዘንድ የእድሜ መግፋትን የሚያመላክት ሆኖ ስለሚታይ፣ ከስነውበት አኳያ የስነልቦና ጫና ማሳደሩ የማይቀር ነው።

ካለግዜው የሚመጣ ሽበት ሲኖር አንዳንድ ሰው ላይ የስነልቦና ጫና ከመፍጠሩ ባሻገር ሊያደርስ የሚችለው ተጨባጭ የጤና እክል አይኖርም።

አንድ ሰው ላይ በተፈጥሮ ሽበት የሚጀምርበት እድሜ ፣በዘር የተለያየ ነው፣ ያም ማለት ከአፍሪካውያኖች ፀጉር ይልቅ፣ የምእራባውያን እና የእሲያውያን ፀጉር ቀድሞ ይሸብታል።

በአፍሪካውያኖች ወይም በጥቁር ማህበረሰቦች ላይ፣ ሽበት ከ 34 እስከ 54 አመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይጀምራል ፣ ለዚህም አማካዩ እድሜ 43 አመት ነው።

ከ6 እስከ 23 በመቶ የሚሆኑ አፍሪካውያን ወይም የጥቁር ማህበረሰቦች፣ እድሜያቸው 50 አመት ሲደርስ፣ ግማሽ የሚሆነው የራስ ቅላቸው ላይ ያለው ፀጉር ይሸብታል።

በዚህ መሰረት ታዲያ፣ በጥቁር ማህበረሰቦች ዘንድ፣ ያለግዜው የሚመጣ ሽበት የሚባለው፣ ሽበቱ የጀመረው ከ 30 አመት እድሜ በታች የሆነ ሰው ላይ ከሆነ ነው።

ካለግዜው የሚመጣ ሽበትን ከሚያስከትሉ ምክኒያቶች ውስጥ አብላጫውን ድርሻ የሚይዘው ተፈጥሮ ነው፣ በቤተሰብ የሚኖር ቀድሞ የሚመጣ ተፈጥሮአዊ ሽበት፣ በልጆች ላይም ሊከሰት ይችላል።

በዚህ ቪዲዮ ላይ የፀጉር ቀለም አይነቶችን በተመለከተ፣ እና ሽበት ያለግዜው የሚጀምርበትን ምክኒያት፣ እንዲሁም በህክምናው ዘርፍ የሚደረገውን ሁኔታ አብራርቻለሁ።