Get Mystery Box with random crypto!

ለጥንቃቄ !! ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው? ሄፒታይተስ ከጉበት መቆጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን፥ | Medical Laboratory

ለጥንቃቄ !!
ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

ሄፒታይተስ ከጉበት መቆጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን፥ ከኤድስና ከቲቢ የበለጠ ገዳይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡
እንደ አጠቃላይ ሄፓታይተስ በኬሚካሎች፣ በእጾች፣ ከመጠን በላይ አልኮል በመጠጣት ወይም በቫይረስ ሊመጣ ይችላል። ሄፓታይተስ ቢ የሚመጣው በሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ነው።

የህመሙ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ብዙ ሰዎች በሄፓታይተስ ቢ ሲያዙ መጀመሪያ ምንም ዓይነት ምልክት አያሳዩም፤ ከነዚህም መሃል አንዳንዶቹ ከብዙ ዓመታት በኋላ ጉበታቸው ይጎዳል ወይም የጉበት ካንሰር ይይዛቸዋል። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች የበሽታው “ተሸካሚዎች” የሚባሉ ሲሆን ቫይረሱንም ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ።

የህመሙ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊጨምር ይችላል፦

ቆዳና የዓይን ነጩ ክፍል ቢጫ ይሆናሉ (ጃውንዲስ በመባል ይታወቃል)
ሽንት ጥቁር ይሆናል
ፊት ይገረጣል
ድካም ይሰማል
የሆድ ዕቃ ህመም ይሰማል
የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል
ማቅለሽለሽና ማስመለስ
የመጋጠሚያ (የአንጓ) ህመም ናቸው።

አንድ ሰው ሄፓታይተስ ቢ እንዴት ሊይዘው ይችላል?

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በበሽታው በተያዘ ሰው ደም፣ ጉበት እና የሰውነት ፈሳሽ ውስጥ ይገኛል። ሄፓታይተስ ቢ ተሸካሚ የሆነች ሴት በእርግዝናዋ ወቅት ወይም በወሊድ ጊዜ ቫይረሱ ወደ ሕፃኑ ልጅ ሊሰራጭ ይችላል።

በአውስትራሊያ ውስጥ ሕፃናት በሙሉ ከተወለዱ በኋላ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ይሰጣቸዋል።