Get Mystery Box with random crypto!

#የኩላሊት_ጠጠር ሰላም ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች እንደት ናችሁ? ለዛሬ ስለ ኩላሊት ጠጠ | Medical Laboratory

#የኩላሊት_ጠጠር
ሰላም ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች እንደት ናችሁ? ለዛሬ ስለ ኩላሊት ጠጠር ይጠቅማል ያልነውን አጠር ያለች መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል።
#የኩላሊት ጠጠር ማለት
• በጣም ጠንካራ የሆነ፡ ጠጠር መሳይ ዝቃጭ፡ ከተለያዩ ሚኒራልስ የተሰራ፡ ኩላሊትንና የሽንት ከረጢትን ጭምር መጉዳት የሚችል ችግር ነው።
• ሽንት በውስጡ መወገድ የነበረባቸውን ብዙ ማዕድናትን ከመያዙ የተነሳና የውሀ መጠን በመቀነሱ የሚፈጠር የጤና ችግር ነው።
• የኩላሊት ጠጠር ከሚከተሉት በአንድ ምክናየት ይፈጠራል
1. ካልሽየም የሚባል ሚኒራል በመብዛቱና መጠራቀሙ
2. በኢንፌክሽን ምክናየት
3. በቂ ውሀ ባለመጠጣት ዩሪክ አሲድ ተጠራቅሞ ሽንት በመወፈሩ
4. ምን አልባት በቤተሰብ ከነበረ ከዘር ይወረሳል
#ተጨማሪ ለኩላሊት መፈጠር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ነገሮች
• በቤተሰብ ከነበረ
• በቂ ፈሳሽ አለመኖር
• ፈሳሽ በተለያየ መንገድ ከሰውነት መወገድ
• የጨው መብዛት
• የፕሮቲን መብዛት
• የስኳር መብዛት
• ወፍራም መሆን
• የተለያዩ በሽታዎች
• ያልታዘዙ መድሀኒቶችና ሌሎችም ናቸው።
• ጠጠሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ካልጀመረ ህመም አይኖረውም። እንቅስቃሴ ሲጀምር ግን የሚከተሉት ዋና ዋና ምልክቶች ይታያሉ።
#10ዋና ዋና የኩላሊት ጠጠር ምልክቶች
1. ከባድ የጀርባ ህመም(ጎንና ጎን ጠጋ ያለ)
2. የሚደጋገምና የሚቆራረጥ ሽንት
3. ሲቆሙ መጥፎ ስሜት መሰማት
4. ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት
5. ማቅለሽለሽና ማስታወክ
6. ከሽንት ጋር የተቀላቀለ ደም
7. መጥፎ የሽንት ሽታ
8. የኩላሊት ማበጥ
9. ማላብና የቆዳ ማሳከክ
10. ግራ መጋባትና የሀሳብ መበታተን
#መከላከያ መንገዶች
• በቂ ውሀ መጠጣት
• ክብደት መቀነስ
• ጨው፡ ስኳር(ጣፋጭ)፡ ፕሮቲን፡ ካልሽየም የያዙ ምግቦችን በመጠኑ መውሰድ
• የአካል እንቅስቃሴ
• በራስ ፈቃድ መድሀኒት አለመጠቀም
• ቫይታሚን ሲ፡ኢና ቢን የያዙ ፍራፍሬ መውሰድ።