Get Mystery Box with random crypto!

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ medihanaelem — Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት F
የቴሌግራም ቻናል አርማ medihanaelem — Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @medihanaelem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.41K
የሰርጥ መግለጫ

በፌስቡክ ያግኙን፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 10:52:33 /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
፠፠፠
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
805 views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:52:33 ከዚህም ሌላ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እጅግ አስደናቂ ምሥጢራትን ፈጽሞላታል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከጎኑ በፈሰሰው ደም ግንባሯ ላይ ቅዱስ ስሙን አትሞባታል፣ በዕለተ ዐርብ በጦር የተወጋ ጎኑንም እንድትጠባ ካደረጋት በኋላ ‹‹ቶማስ የተወጋውን ጎኔን ዳሰሰ፣ አንቺ ግን ጠባሽ›› ብሏታል፡፡ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሠራዒ ካህን ሆኖ ቀድሶ ሥጋ ወደሙን አቀብሏታል፡፡ በቸርነቱም የእናቱን ጡቶች እንድትጠባ ስለፈቀላት እመቤታችን ቅድስት የሆኑ ጡቷን አጥብታታለች፡፡ በመጨረሻም ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ብዙ አስደናቂ የሆኑ ቃልኪዳኖችን ከገባላትና ዐሥር አክሊላትን ካቀዳጃት በኋላ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታ ቅዱሳን መላእክት በዝማሬ አሳርገዋታል፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡ እኛንም በአማላጅነታቸው የምንታመን ሁላችንን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን፣ የአቡነ ቶማስ ዘመርዓስን እና የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፡፡ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
✤✣✤
ዳግመኛም መልአኩ ‹‹አሁንም እንደልማድሽ ሂጂና ጠይቂው ማን እንደሆነ ይነግርሻል›› አላት፡፡ በዚህን ጊዜ ወደ እርሱ ሄደችና ‹‹እሰግድልህ ዘንድ አንተ ማን ነህ?፣ ስምህስ ማን ይባላል?›› ስትል ጠየቀችው፡፡ ሰይጣንም ‹‹የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ›› አላት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሷ ጋር እንዳለ አላወቀም ነበርና፡፡ እርሱ በእርሷ ላይ ተንኮል ለመሥራት እንደተራቀቀ ሁሉ እርሷም ነቃችበት ተራቀቀችበት፡፡ ቀጥሎም ‹‹እንግዲያውስ አንተ ሚካኤል ከሆንክ እስቲ ስለ ጽድቅ ነገር አስተምረኝ›› አለችው፡፡ በዚህም ጊዜ ሰይጣን ፈጽሞ ተደሰተ ከዓላማዋ አሳስቶ በእጁ የገባችለት መስሎታልና፡፡ እንዲህም አላት፡- ‹‹ለምን ሰውነትሽን ታደክሚዋለሽ? ከዛሬ ጀምሮ ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ማረፍ ያስፈልግሻል፣ መጾምና መጸለይስ ለምን ይጠቅምሻል? በባሕርስ ውስጥ ቆሞ መጸለይና ሰውነትን ማድከም ማን አስተማረሽ?›› አላት፡፡ በዚያን ጊዜ ‹‹አንተ የምትለውና መጻሕፍት የሚናገሩት የተለያየ ሆነሳ!?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ማነው የለያየን?›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ከአነጋገርህ የተነሣ እኔ ለየኋችሁ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹እስኪ ልዩነታችንን ንገሪኝ?›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹መጻሕፍት የጾመ፣ የጸለየ፣ የለመነም ሁሉ ፍጹም ዋጋውን ያገኛል ይላሉ፡፡ አንተ ግን አትጹሙ፣ አትጸልዩ ትላለህ›› አለችው፡፡ ይህንንም ባለችው ጊዜ በእርሷ ላይ ፈጽሞ ተቆጣ፣ እጅግም አድርጎ አስደነገጣት፡፡ ዳግመኛም መለሰችና ‹‹በምን ትሸነፋለህ?›› አለችው፡፡ አሁንም ቁጣውን አወረደባት፡፡ በሦስተኛው ጊዜ ከተቆጣ በኋላ ‹‹በእነዚህ በሦስቱ ነገሮች እሸነፋለሁ›› ሲል መለሰላት፡፡ ‹‹አንደኛ ማንኛውም ሰው በዚህ ዓለም በሚኖርበት ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት እንግዳ ተቀብሎ የሚያስተናግድ፤ ሁለተኛው በራሱ ላይ ችግርና መከራ በመጣበት ጊዜ መከራውን ታግሦ የሚኖር፤ ሦስተኛው ቀድሞም ከመሬት የተገኘሁ ነኝ፣ ኋላም ተመልሼ ወደ መሬት እገባለሁ እሞታለሁ እፈርሳለሁ ብሎ በማሰብ ትሕትና የሚሠራና የመሳሰሉትን ሁሉ የሚያደርግ እርሱ ፈጽሞ ያሸንፈኛል›› አላት፡፡ ይህንንም ከተናገረ በኋላ ክንፉን እያማታ ወደ አየር በረረ፡፡ እርሷም ከግርማው የተነሣ ፈጽማ ደነገጠች፤ በመሬትም ላይ ወደቀች፡፡ በዚያን ጊዜ ለጌትነቱ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ቅዱሳት በሚሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣት፡፡ ከዚያም ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! አይዞሽ አትፍሪው ነገር ግን ወደ ላይ ወደ ሰማይ አቅንተሽ ተመልከቺ›› አላት፡፡ ወደ ሰማይ አቅንታ በተመለከተች ጊዜ የዲያብሎስ ክንፉ በሰማይ ላይ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ ተዘርግቶ (መላው ዓለምን ሞልቶ) አየች፡፡ ቀጥሎም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በእኔ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ያላመነ ሊያሸንፈው አይችልም›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ማንም ሰው ኃጢአት ቢኖርበት ወደ ቀደመ ኃጢአቱ ባለመመለስ ንስሐ ቢገባ ከወጥመዱ ያመልጣል›› አላት፡፡
ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በቁመቷ ልክ ጉድጓድ አስቆፍራ በአራቱም አቅጣጫ ከፊትና ከኋላ፣ በግራና በቀኝ ሦስት ሦስት የተሳሉ ጦሮችን ተክላ የፊጥኝ ታስራ ስለ ዓለሙ ሁሉ ይልቁንም ስለ ኢትዮጵያ ልጆች ስትጸልይ ኖራለች፡፡ በምትሰግድበትም ጊዜ ጦሩ እየወጋት ከቁስሉ የተነሳ ጦሩ የወጋትና ገመዱ የከረከራት መላ ሰውነቷ እስኪሸትና እስኪተላ ድረስ ለ12 ዓመታት በጉድጓድ ውስጥ በተጋድሎ ኖራለች፡፡ ያረፈችውም በዚሁ ጉድጓድ ውስጥ ቆማ ስለ ዓለሙ ስትጸልይ ነው፡፡ ጌታችንም ክብሯ ከሙሴ፣ ከአሮን፣ ከጴጥሮስ፣ ከጳውሎስ፣ ከሕጻኑ ቂርቆስ፣ ከእንጦንስ፣ ከጊዮርጊስና ከእስጢፋኖስ ጋር የተካከለ መሆኑን በማይታበል ቃሉ ነግሯታል፡፡ በዚህች ምድር ላይም 375 ዓመት ኖራ አባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት ባረፉበት ዕለት ነሐሴ 24 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፋለች፡፡
በዚህችም ዕለት ከማረፏ በፊት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ቅድስት እናቱን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ሌሎች ቅዱሳንን ሁሉ አስከትሎ ወደ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጥቶ ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! ዛሬ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም አሳርፍሽ ዘንድ መጥቻለው›› አላት፡፡ ‹‹ድካምሽ ወደ ዕረፍት፣ ኀዘንሽም ወደ ደስታ ተለውጦልሻልና›› ሲላት እርሷም ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እኔ ባሪያህ በፊትህ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆን አንድ ነገር እንድናገር ፍቀድልኝ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ትናገሪ ዘንድ ፈቅጄልሻለው›› ሲላት ‹‹አቤቱ ሥጋዬ የሚቀበርበት ቦታ ወዴት እንዲሆን ታዛለህ?›› አለችው፡፡ ጌታችንም ‹‹መቃብርሽ በዚህች ደሴት ይሆናል›› ካላት በኋላ የሚከተለውን ቃልኪዳን ሰጣት፡- ‹‹… በስምሽ ለተራበ ያበላ እኔ ዕለተ ዓርብ ከተቆረሰው ሥጋዬ አበላዋለሁ፣ በስምሽ ለተጠማ እፍኝ ውኃ ያጠጣውን እኔ በዕለተ ዓርብ ከጎኔ በፈሰሰው ደሜ አረካዋለሁ፡፡ እውነት እውነት እልሻለሁ ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሣለመ ይቆጠርለታል፡፡ ምሕረት ሊደረግለት የማይገባው ሁሉ ወደ አንቺ መጥቶ ዜና ገድልሽን ሊሰማ አይችልም፡፡ ስለሆነም ገድልሽን ለመስማት፣ ትሩፋትሽን ለማየት ወደ አንቺ የሚመጡትን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን እሰጣቸዋለሁ፣ አንቺን የሚያፈቅሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፣ እውነት እውነት እልሻለሁ አንቺን የወደደሽን እኔ ደግሞ እወደዋለሁ፡፡ መኖሪያሽ ከእናቴ ከድንግል ማርያም ጋር ነው፣ እነሆ በትረ ማርያም ብዬ ሰየምኩሽ፣ ደረጃሽን ከእርሷ ቀጥሎ ሁለተኛ አደረግሁልሽ›› ብሏታል፡፡ ከዚያም በፊት የቅዱሳን ገድላቸው ሲነበብ ሐሰት ነው ብለው የሚያቃልሉ ሰዎች ዕጣ ክፍላቸው ከነአርዮስ ጋር መሆኑን ጌታችን ለክርስቶስ ሠምራ ነግሯታል፡፡ ይኸውም ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅዱስ ሚካኤል በጌታችን ፊት አቁሟት ሳለ እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ጌታችንን ‹‹አቤቱ ጌታዬ የቅዱሳን ገድላቸው ሲነበብ ሐሰት ነው በማለት የማያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን ትምራቸዋለህ? ወይስ አትምራቸውም?›› አለችው፡፡ ጌታችንም ‹‹በጥቡዕ ልብ ሆነው ያለመጠራጠር የሚያምኑት ወደ መንግሥቴ ይገባሉ፣ የማያምኑ ቢኖሩ ግን ክፍላቸው ከነ አርዮስና ሰባልዮስ ጋር ነው›› አላት፡፡
የእናታችን የቅድስትክርስቶስ ሠምራ ምልጃና ጸሎት አይለየን
763 views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 11:27:43
#Orthodox_Quotes
ቅድስት ሥላሴ
948 viewsedited  08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:04:56
1.6K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:02:25 -------
#ሐምሌ_7_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤
#ወልዱ_ለአቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ልደቱና_እረፍቱ_ነው፡፡
ዕረፍቱ የኾነው በሐምሌ 7 (6,705 ዓመተ ዓለም፥ በ2ት እንድቅትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፥ በ7ት ጥንተ ዮን፥ በወንጌላዊው ማቴዎስ ዘመን በዕለተ ረቡዕ) ነው፡፡ ያረፈውም በአፄ ይስሐቅ ጥያቄ የጋራ መናገሻ መድኀኔ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ባርኮ ሲመለስ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ሲኾን ፤ አርድዕቱ ሥጋውን ይዘው ሂደው በአባቱ መካን በደብረ ጎል (አሁን በደብረ ባሕርይ) አሳርፈውታል፡፡
፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤
፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥
፠ ዐምደ ሃይማኖት
፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤
፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤
፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥
፠ አፈ በረከት
፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል
ከ40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤
1. ✼ ኆኀተ ብርሃን
2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም)
3. ✼ መዝሙረ ድንግል
4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ
5. ✼ ውዳሴ መላእክት
6. ✼ ውዳሴ ነቢያት
7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት
8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት
9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን
10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን
11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር
12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን
14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ
15. ✼ መሰንቆ መዝሙር
16. ✼ እንዚራ ስብሐት
17. ✼ ውዳሴ መስቀል
18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት
19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት
20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት
21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ
22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ
23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም)
24. ✼ ውዳሴ ስብሐት
25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ
26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ
27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት
28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት)
29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ)
30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት
31. ✼ መልክአ ቊርባን
32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን
33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም
34. ✼ ክብረ ቅዱሳን

(በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ በቦረና አውራጃ ነው፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
1.5K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:02:07
1.2K views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:01:05 ፮. #መካነ_ሥላሴ_ደቡብ_ወሎ_ወረኢሉ፤ (በ1500ዓ.ም. በዐፄ ናዖድ የተመሠረተና በልጁ በዐፄ ልብነ ድንግል ሥራው የተጠናቀቀ፤ ባለ 16 መንበር፥ በዕንቊና በወርቅ የታነጸ የነበረ፤ /ኋላ በግራኝ የፈረሰ/፤ ነገር ግን ጽላቱ በዐፄ ምኒልክ ዳግማዊ ወደ አ.አ. መጥቶ ቀድሞ 4 ኪሎ መካነ ሥላሴ አሁን መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ በመባል የሚጠራ)፤ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና ወሎ መካነ ሥላሴ ላይ በቀድሞው ቅርጹ በባለ 16 መንበር ተደርጎ 2009 ዓ.ም. አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በመገንባት ላይ ይገኛል፤ (ለሕንፀታ ቤቱ ሁላችንንም ያብቃን)፡፡
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ወረኢሉ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወረኢሉ፡፡
፯. #ፀዓዳ_አምባ_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል_ገዳም፤ (በ1669 ዓ.ም. የተገደመ፤ መሄጃ መንገዱ እጅግ አስደናቂና በ2ቱም በኩል ገደል የኾነ)
አድራሻ፤ ኤርትራ፥ ዞባ አንሰባ፥ ከረን፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ (በአውሮፕላን)→ ኤርትራ → ከረን → /25ኪ.ሜ/ ፀዓዳ አምባ፡፡
፰. #ጎንደር_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በጥር 26 ቀን 1683 ዓ.ም. በዐፄ አድያም ሰገድ የታነጸ፤ በጎንደር ከተማና ዙሪያ ከሚገኙ 44ቱ ታቦታተ ጎንደር በአሠራሩ ልዩ የኾነ፤ በ1880ዎቹ ድርቡሽ ጎንደር ከተማን ሲያጠፋ ከ44ት አብያተ ክርስቲያናት በተአምራት ሳይቃጣል የቀረ፤ የታላላቅ ሊቃውንት /የእነ ሊቁ ክፍለ ማርያም/ መፍለቂያ፡፡
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፱. #ናርጋ_ሥላሴ_ገዳም፤ (በጣና ሐይቅ ላይ ካሉ ደሴቶች ትልቁ በሆነው በደቅ(7ት ደብር ሃገር) ደሴት ከሚገኙ 7 ገዳማት አንዱ)፡፡ (በአፄ በካፋ ባለቤት በበእቴጌ ምንትዋብ /1730-1755 ዓ.ም./ የተሠራ፤ ግድግዳዎቹ በሚያስደንቁና ልቡናና መንፈስን በሚመስጡ ሥዕላት ያሸበረቁ፡፡)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጣና ሐይቅ (ከባሕር ዳር ከተማ ሰሜናዊ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ /በጀልባ 3 ሰዓት/፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባህር ዳር/ጎንደር → በጀልባ/በታንኳ/ /በመርከብ/ ናርጋ ሥላሴ፡፡
፲. #ጨለቆት_ሥላሴ_ትግራይ፤ መቀለ አጠገብ፡፡ (በ1787 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲኾን ተካዩ ደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ክፍለ ኢየሱስ ሃገረ ገዢ ናቸው) (የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያ ነው፤ ለአብነትም በዐፄ ዮሐንስ /1864 – 1881ዓ.ም./ ዘመነ መንግሥት አራት ጳጳሳትን እንዲያመጡ ከተላኩት መካከል አንዱ ሊቅ አለቃ ዐሥራት ዘውጉ ዘጨለቆት ሥላሴ ናቸው፡፡) (የእንግሊዝ ጦር ዐፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ ሰብስቦት የነበረውን ዘርፈው ሲወስዱ የበዛባቸውን ለዚህ ደብር ሰጥተው ሄደዋል፡፡)
አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ እንደርታ አውራጃ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ /እንደርታ/፡፡
፲፩. #ሐረር_ሐድሬ_ጥቆ_መካነ_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት፥ ሐረር ከተማ፥ ሐድሬ ጥቆ ወረዳ፤ (በዐፄ ኀይለ ሥላሴ በ1941-43 ዓ.ም. የተሠራ)
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐረር፡፡
፲፪. #ድሬዳዋ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ድሬዳዋ ሃገረ ስብከት፥ ድሬዳዋ፥ ሳቢያን ሰባተኛ ሰፈር፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ድሬዳዋ፡፡
፲፫. #ኤረር_በዓታ_ወቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምሥራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ አድአ ወረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ዘይት → ኤረር፡፡
፲፬. #ሰንዳፋ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት፥ ሰንዳፋ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ሰንዳፋ፡፡
፲፭. #ሱልልታ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት፥ ሱልልታ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ (ከፒያሳ /አዲሱ ገበያ/ → ሱልልታ፡፡
፲፮. #ጫንጮ_ሞዬ_ጋጆ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት፥ ጫንጮ፥ ሞዬ ጋጆ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ (ከፒያሳ /አዲሱ ገበያ/ → ጫንጮ → ሞዬ ጋጆ፡፡
፲፯. #ሚዳ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መርሐ ቤቴ፥ ሚዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ሚዳ /መርሐ ቤቴ/፡፡
፲፰. #ደሴ_ደብረ_ቤቴል_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደሴ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ፡፡
፲፱. #እንጂባራ (ኮሶ በር)_መንበረ_ፀባዖት_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ እንጂባራ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → እንጂባራ፡፡
፳. #ባሕር_ዳር_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ባሕር ዳር ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳራ /ቀበሌ 07/፡፡
፳፩. #ጎንደር_አዘዞ_መናኸሪያ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ አዘዞ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንድረ /አዘዞ/፡፡
፳፪. #ናዝሬት_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምሥራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ናዝሬት /አዳማ/፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት /አዳማ/፡፡
፳፫. #ቡታጅራ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ቡታጅራ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ቡታጅራ፡፡
፳፬. #ጉብርየ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ጉብርየ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ጉብርየ፡፡
፳፭. #ሐዋሳ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሲዳማ ሐዋሳ ሃገረ ስብከት፥ ሐዋሳ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐዋሳ፡፡
፳፮. #ቦረዳ_ዳግማዊ_ዮርዳኖስ_ቅድስት_ሥላሴና_ሚካኤል፤
አድራሻ፤ ጋሞ ጎፋ ሃገረ ስብከት፥ ቦረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ቦረዳ፡፡
፳፯. #ምሥራቅ_ሐረርጌ_ፈዲስ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት፥ ፈዲስ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ፈዲስ፡፡
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከበርባቸው_ #፬ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #አሜሪካ_ሲያትል_መንበረ_ፀባኦት_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ዋሽንግተን ዲሲ ሃገረ ስብከት፥ ዋሽንግተን ስቴት ሲያትል (ፌደራል ዌይ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ጀርመን ሐሚልተን፡፡
፪. #አሜሪካ_ሚኒሶታ_ጽርሐ_አርያም_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሚኒሶታ ሃገረ ስብከት፥ ሚኒሶታ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → አሜሪካ /ሚኒሶታ/፡፡
፫. #ጀርመን_ሐሚልተን_ኦንታርዮ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ጀርመን ሐሚልተን ሃገረ ስብከት፥ 420 Aberdeen Ave. Hamilton, ON L8P 2R5፥ ሞዬ ጋጆ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ጀርመን ሐሚልተን፡፡
፬. #ሮም_ደብረ_ከነዓን_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ኢጣሊያና አካባቢው ሃገረ ስብከት፥ ሮም፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ኢጣሊያ /ሮም/፡፡አቅጣጫ ከ በኢ.ቦ ዋሊ ገጽ
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ
1.2K viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:01:05 #ሐምሌ_7_ቀን ቅድስት ሥላሴ ለአብርሃም የተገለጹበት ነው፡፡
#ሐምሌ_7 የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት ፥ አፈ በረከት ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤
ልደቱና እረፍቱ ነው፡፡
-------------------
ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ ስለኾነ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ፍጹም ሦስትነት የሌለውና ምሳሌ ዘየኀጽጽ ስለሆነ)፤ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡
በዚህች #ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤
#፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤
ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡
ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤
አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡
እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤
፠ #ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤
፠ #ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤
፠ #ለዳንኤል በአረጋዊ፣
፠ #ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤
፠ #ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን #አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡
#፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡
#፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤
ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤
ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤
ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡
--
#ጥር ፯፤ #በዓለ_ሥላሴ_ (#_አብርሃምና_ሣራ_ሥላሴን_በእንግድነት_የተቀበሉበት_)
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፶፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ አሳውቁን)
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በአዲስ_አበባ_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፳፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #መካነ_ሥላሴ ( #ኋላ_መንበረ_ፀባዖት_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ.ክ.)፤ (አዲስ አበባ ላይ በ1883 ዓ.ም. የተመሠረተ፤ ነገር ግን ታቦቱ ቀድሞ የነበረና ከ600 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው)
አድራሻው 4 ኪሎ፤
፪. #መንበረ_ስብሐት_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ሽሮ ሜዳ፤
፫. #መሪ_ምሥራቀ_ፀሐይ_ቅድስት_ሥላሴ_ዑራኤል_ማርያም_ጊዮርጊስና_አቡነ_አረጋዊ_
አድራሻ፤ አያት መሪ፤
፬. #ካራ_አሎ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ አባዶ አጠገብ፤
፭. #ጠሮ_ኮልፌ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ጠሮ፤
፮. #ሰፈረ_ገነት_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ላፍቶ፡፡
፯. #ፈለገ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ላፍቶ፡፡
፰. #ቂሊንጦ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ቂሊንጦ፡፡
፱. #ኤረር_በር_ጽርሐ_አርያም_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ጎሮ፡፡
፲. #ፈለገ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ሳሪስ /58/፡፡
፲፩. #ጀሞ_ፈለገ_ኮሬብ_ቅድስት_ሥላሴና_ቅድስት_ማርያም
አድራሻ፤ ጀሞ፡፡
፲፪.#ቃሊቲ_አረጋውያን_እንክብካቤ_መካነ_ስብሐት_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_፤
አድራሻ፤ አረጋውያን እንክብካቤ፡፡
፲፫. #ቦሌ_አራብሳ_ዋሻ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤አራብሳ፡፡
፲፬. #ካራ_አሎ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ካራ፡፡
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#እንዲሁም_በድርብነት_፤
፲፭. #ደብረ_ሲና_ቅዱስ_እግዚአብሔር_አብ፤

፲፮. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔ ዓለም፤
፲፯. #ኤረር_ምሥራቀ_ፀሐይ_ዑራኤል_
፲፰. #መካነ_ቅዱሳን_ኢያቄም_ወሐና፤
፲፱. #አየር_ጤና_አንቀጸ_ብርሃን_ቅድስት_ኪዳነ_ምሕረት፤
፳. #ቶታል_ደብረ_ገነት_ቅድስት_ሥላሴ_፤
፳፩. #ደብረ_መድኀኒት_አቡነ_ሀብተ_ማርያም_ልደታና_አርሴማ_ገዳም፤
፳፪. #አዲስ_አምባ_ደብረ_ገነት_ኪዳነ_ምሕረትና_ደብረ_ፍስሐ_ገብርኤል_፤
፳፫. #ላፍቶ_ደብረ_ትጉሃን_ሚካኤል_፤
፳፬. #ለቡ_ደብረ_ታቦር_በዓለ_ወልድና_አበ_ብዙሃን_አብርሃም_ገዳም_፤
፳፭. #ቦሌ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም፤
፳፮. #ቦሌ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም፤
፳፯. #ቱሉ_ዲምቱ_ደብረ_ሰላም_ጊዮርጊስና_ሚካኤል_፤
፳፰. #ቃሊቲ_ደብረ_መድኀኒት_መድኀኔ_ዓለምና_አቡነ_አረጋዊ_፤
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፳፯ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (ከ2014 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፤ የብዙ ቅዱሳን /የአባ ዐምደ ሥላሴ፣ የአባ ክፍለ ማርያም፣ የ7ቱ ዘሥላሴ፣ የአባ አርከ ሥሉስ ቅዱስ፣ …….. ) መፍለቂያ፡፡
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ቋራ (መተማ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር/አዘዞ/ → ሸዲ/መተማ/ → በእግር፡፡
፪. #ዱገም_ሥላሴ_ገዳም፤
አድራሻ፤ ትግራይ፥ ገርዓልታ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ → በመቀለ (በጎንደር) → ገርዓልታ፡፡
፫. #ደብረ_ወገግ_አሰቦት_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሳሙኤል፤ (በ13ኛው ክ/ዘመን በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተስፋፋ፥ ቅዱስ ዑርኤል የጌታን ደም በጽዋው የመጨረሻውን እንጥፍጣፊ ያፈሰሰበት፥ በርካታ ቅዱሳን የተሰወሩበት፥ አሁንም የሚሠወሩበት፥ የምሥጢር ቦታ)
አድራሻ፤ ሐረርጌ፥ አሰበ ተፈሪ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት/አዳማ/→ አሰበ ተፈሪ → አሰቦት፡፡
፬. #ሰሜን_ሸዋ_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በ14ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን ከተማ፡፡
፭. #ጀሩ_ሥላሴ_፤ (በ1495 ዓ.ም በዐፄ ናዖድ ዘመን፤ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት በጻድቁ አቡነ እያሱ የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ እንሳሮ /ለሚ/ ወረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ለሚ /እንሳሮ/፡፡
1.2K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:00:43
1.3K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 11:56:38
የመጨረሻውን ክፍል በድረ ገፃችን ያድምጡ ፡፡
https://cutt.ly/lLqXnQg
1.6K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ