Get Mystery Box with random crypto!

#ሐምሌ_7_ቀን ቅድስት ሥላሴ ለአብርሃም የተገለጹበት ነው፡፡ #ሐምሌ_7 የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት | Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

#ሐምሌ_7_ቀን ቅድስት ሥላሴ ለአብርሃም የተገለጹበት ነው፡፡
#ሐምሌ_7 የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት ፥ አፈ በረከት ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤
ልደቱና እረፍቱ ነው፡፡
-------------------
ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ ስለኾነ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ፍጹም ሦስትነት የሌለውና ምሳሌ ዘየኀጽጽ ስለሆነ)፤ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡
በዚህች #ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤
#፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤
ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡
ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤
አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡
እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤
፠ #ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤
፠ #ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤
፠ #ለዳንኤል በአረጋዊ፣
፠ #ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤
፠ #ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን #አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡
#፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡
#፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤
ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤
ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤
ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡
--
#ጥር ፯፤ #በዓለ_ሥላሴ_ (#_አብርሃምና_ሣራ_ሥላሴን_በእንግድነት_የተቀበሉበት_)
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፶፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ አሳውቁን)
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በአዲስ_አበባ_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፳፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #መካነ_ሥላሴ ( #ኋላ_መንበረ_ፀባዖት_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ.ክ.)፤ (አዲስ አበባ ላይ በ1883 ዓ.ም. የተመሠረተ፤ ነገር ግን ታቦቱ ቀድሞ የነበረና ከ600 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው)
አድራሻው 4 ኪሎ፤
፪. #መንበረ_ስብሐት_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ሽሮ ሜዳ፤
፫. #መሪ_ምሥራቀ_ፀሐይ_ቅድስት_ሥላሴ_ዑራኤል_ማርያም_ጊዮርጊስና_አቡነ_አረጋዊ_
አድራሻ፤ አያት መሪ፤
፬. #ካራ_አሎ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ አባዶ አጠገብ፤
፭. #ጠሮ_ኮልፌ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ጠሮ፤
፮. #ሰፈረ_ገነት_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ላፍቶ፡፡
፯. #ፈለገ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ላፍቶ፡፡
፰. #ቂሊንጦ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ቂሊንጦ፡፡
፱. #ኤረር_በር_ጽርሐ_አርያም_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ጎሮ፡፡
፲. #ፈለገ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ሳሪስ /58/፡፡
፲፩. #ጀሞ_ፈለገ_ኮሬብ_ቅድስት_ሥላሴና_ቅድስት_ማርያም
አድራሻ፤ ጀሞ፡፡
፲፪.#ቃሊቲ_አረጋውያን_እንክብካቤ_መካነ_ስብሐት_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_፤
አድራሻ፤ አረጋውያን እንክብካቤ፡፡
፲፫. #ቦሌ_አራብሳ_ዋሻ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤አራብሳ፡፡
፲፬. #ካራ_አሎ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ካራ፡፡
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#እንዲሁም_በድርብነት_፤
፲፭. #ደብረ_ሲና_ቅዱስ_እግዚአብሔር_አብ፤

፲፮. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔ ዓለም፤
፲፯. #ኤረር_ምሥራቀ_ፀሐይ_ዑራኤል_
፲፰. #መካነ_ቅዱሳን_ኢያቄም_ወሐና፤
፲፱. #አየር_ጤና_አንቀጸ_ብርሃን_ቅድስት_ኪዳነ_ምሕረት፤
፳. #ቶታል_ደብረ_ገነት_ቅድስት_ሥላሴ_፤
፳፩. #ደብረ_መድኀኒት_አቡነ_ሀብተ_ማርያም_ልደታና_አርሴማ_ገዳም፤
፳፪. #አዲስ_አምባ_ደብረ_ገነት_ኪዳነ_ምሕረትና_ደብረ_ፍስሐ_ገብርኤል_፤
፳፫. #ላፍቶ_ደብረ_ትጉሃን_ሚካኤል_፤
፳፬. #ለቡ_ደብረ_ታቦር_በዓለ_ወልድና_አበ_ብዙሃን_አብርሃም_ገዳም_፤
፳፭. #ቦሌ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም፤
፳፮. #ቦሌ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም፤
፳፯. #ቱሉ_ዲምቱ_ደብረ_ሰላም_ጊዮርጊስና_ሚካኤል_፤
፳፰. #ቃሊቲ_ደብረ_መድኀኒት_መድኀኔ_ዓለምና_አቡነ_አረጋዊ_፤
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፳፯ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (ከ2014 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፤ የብዙ ቅዱሳን /የአባ ዐምደ ሥላሴ፣ የአባ ክፍለ ማርያም፣ የ7ቱ ዘሥላሴ፣ የአባ አርከ ሥሉስ ቅዱስ፣ …….. ) መፍለቂያ፡፡
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ቋራ (መተማ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር/አዘዞ/ → ሸዲ/መተማ/ → በእግር፡፡
፪. #ዱገም_ሥላሴ_ገዳም፤
አድራሻ፤ ትግራይ፥ ገርዓልታ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ → በመቀለ (በጎንደር) → ገርዓልታ፡፡
፫. #ደብረ_ወገግ_አሰቦት_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሳሙኤል፤ (በ13ኛው ክ/ዘመን በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተስፋፋ፥ ቅዱስ ዑርኤል የጌታን ደም በጽዋው የመጨረሻውን እንጥፍጣፊ ያፈሰሰበት፥ በርካታ ቅዱሳን የተሰወሩበት፥ አሁንም የሚሠወሩበት፥ የምሥጢር ቦታ)
አድራሻ፤ ሐረርጌ፥ አሰበ ተፈሪ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት/አዳማ/→ አሰበ ተፈሪ → አሰቦት፡፡
፬. #ሰሜን_ሸዋ_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በ14ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን ከተማ፡፡
፭. #ጀሩ_ሥላሴ_፤ (በ1495 ዓ.ም በዐፄ ናዖድ ዘመን፤ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት በጻድቁ አቡነ እያሱ የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ እንሳሮ /ለሚ/ ወረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ለሚ /እንሳሮ/፡፡