Get Mystery Box with random crypto!

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ medihanaelem — Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት F
የቴሌግራም ቻናል አርማ medihanaelem — Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @medihanaelem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.41K
የሰርጥ መግለጫ

በፌስቡክ ያግኙን፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 14:19:20 እንኳን ለአባታችን #አቡነ_ሃብተማርያም በዓለ ጽንሰት በሰላም አደረሳቹ::

አቡነ ሀብተማርያም

፠፠በማዕጠንታቸው የታወቁ፤
፠፠በጽድቅ ሥራቸው የተደነቁ፤
፠፠5ት መቅሰፍቶችን የሚያርቁ ታለቅ አባታችን ናቸው፡፡፡፨

፠ታላቁ ጻድቅ አባታችን #አቡነ_ሃብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በንጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡

የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሐሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡ ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ እናታቸውም ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ #7_አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡

፠አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡

፠ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡
ለአብነትም፤
ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤
በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤
በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤
ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋል፤
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤
በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡
የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡
"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም" የተባለላቸው ታላቅ አባታችን ናቸው ፡፡

፠ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡
፠ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡
*የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡
፠ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው::

"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው::

+ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: መላእክትም ዝማሬም ወሰዷት::

 ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
፩ኛ. #መብረቅ፣
፪ኛ. #ቸነፈር፣
፫ኛ. #ረሃብ፣
፬ኛ. #ወረርሽኝ፣
፭ኛ. #የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

፨በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)



✞✞✞✞✞
#አቡነ #ተክለሃይማኖት አና #አቡነ #ሃብተማርያም


#ያን ጊዜ ክቡር የሆነ #አቡነ_ተክለሃይማኖት ጠርቶኝ ልጄ #ሀብተ_ማርያም ሆይ ፈጣሪየ እግዚአብሔር ስለ ወደደህ ብዙ ምህርኮ እንደአገኝህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል አለኝ ፤
#ነገር ግን የሞለምንክ አንድ ነገር አለና እሽ በለኝ ቢለኝ አቤቱ ጌታዩ ምንድን ነው ነገሩ አልሁት ፣
#ክቡር አባታችን አባ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀብር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለኝ፤
ይንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትለምነኛለህ ብየ ብመልስለት፣ እነሆ በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስ መቅሰፍቶች አሉና ስለዚህ ነው ፤ እሊሁም አንዱ መብረቅ ነው ፣ ሁለተኛው ቸነፈር ነው ፤ ሦስተኛው የረኃብ ጦር ነው ፣ አራተኛ ወረርሽኝ ነው ፡፡ አምስተኛ የእሳት ቃጠሎ ነው ፤ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደ ሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገር ከእንዚህ መቅስፍታት ትድናለች፣
#……ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሄር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው አለኝ ፣ ይልቁንስ እንዳልኩክ በተቀበርኩበት ቦታ እንተቀበርልኝ ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ መላልሶ ማለደኝ.
ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም

#አቡነ_ሀብተ_ማርያም በቃል ኪዳናቸው ሀገራችንን ከአምስቱ መቅሰፍታት ይጠብቁልን አሜን !

በአ.አ በዓሉ በድምቀት ከሚከበርባቸው አድባራት አንዱ በቃሌ ተራራ ደብር መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም ገዳም አንዱ ነው ::
በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
፠፠፠
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
822 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:19:01
823 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:56:19
1.0K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:20:53
691 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:42:40

1.1K views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:42:10

1.6K views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:55:31
2.0K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:55:29
1.5K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:52:57 #ቅዱስ_ቶማስ_ዘመርዓስ_
የመርዓስ ኤጵስ ቆጶስ የነበረው አባት አባ ቶማስ ክርስቶስን በማመን በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀንና ሌሊት በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የሚኖር ነበር። በዚህ ፅናቱ የክብር ባለቤት ጌታችን መርዓስ ለሚባል አገር ኤጲስ ቆጶስ ይሆን ዘንድ መንጋውንም ይጠብቅ ዘንድ መረጠው አባታችን ቶማስም ሐዋርያዊ ተልዕኮውን እየፈፀመ፣ ሕዝቡን እየመራ ሳለ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሱ ላይ፣ በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይም ተነሳባቸው፣ ክርስቲያኖችንም ያሰቃያቸው ጀመር በአንድ ወቅት ከመኳንንቶች አንዱ የነበረው፣ ቅዱስ ቶማስን ወደ እርሱ ያቀርቡት ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ እነርሱም እየደበደቡ በምድር ላይ እየጎተቱ ወሰዱት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ ከዚህም በኋላ መኮንኑ ቅዱስ ቶማስን ለአማልክት ስገድ አለው ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት «እኔ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ ጣኦታት አልሰግድም ለረከሱ ጣዖታት የሚሰግድ ሁሉ የተረገመ ነውና» በዚህም ጊዜ መኮንንኑ በጣም ተቆጥቶ እጅግ የበዛ ስቃይን አሰቃየው የነዳጅ ድፍድፍን አፍልተው በላዩ በአፉና በአፍንጫው እስከመጨመርም ደረሱ ልባቸው እንደ ድንጋያ የፀና ስለ ነበር ቅዱስ ቶማስን ገድለው ቶሎ ማሣረፍ አልፈለጉም ይልቁንም የስቃዩን ዘመን አስረዘሙ እንጂ እርሱም ስለ ስህተታቸው ይዘልፋቸው ነበር፣ እንደ ማይመልስም ሲገባቸው በጨለማ ቦታ ጣሉት በየዓመቱም ወደ እርሱ እየሄዱ ከሕዋሳቱ አንድ፣ አንዱን ይቆርጡ ነበር፡፡
በዚህም ለሃያ ሁለት(፳፪) ዓመት ቆየ ሲቆይ ግን አፍንጫውን፣ ከንፈሮቹን፣ ጆሮዎቹን፣ እጆቹንና እግሮቹን ቆርጠው ነበር፤ በዚህም ምክንያት የአገሬው ሰው ሞቷል ብለው አስበው በየዓመቱ መታሰቢያ ያደርጉለት ነበር ይህ ለምን ሳይሞት ቢሉ ጊዜው ሲረዝም ቢሞት ነው እንጂ እስካሁንማ ይመጣ ነበር ብለው ስላሰቡ ነበር፤ ነገር ግን ከሕዋሳቶቹ አብዛኛው ክፍል ቆርጠው ቢጥሉትም አካሉ ግን ተቆራርጦ ሲጣል አንዲት ሴት አየችው፣ ይህችም ሴት በሌሊት ወደርሱ ተሠውራ በመሔድ ትመግበው ነበር፡፡
ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም እስከነገሠና የቀናች የክርስቶስን ሃይማኖት ክብር እስከገለጥ ድረስ እንዲህ ሲሰቃይ ኖረ፡፡
#ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ስለክርስቶስ በመታመን የታሠሩ እስረኞች ሁሉ እንዲፈቱ በማዘዙ ሁሉም ተፈቱ፡፡ ቅዱስ ቶማስ ግን የተጣለበት ቦታ፤ በሕይወት ያለም ስላልመሠላቸው አላወጡትም ነበር፤ ነገር ግን ይህን አዋጅ ትመግበው የነበረችው ሴት ሰምታ ነበርና ወደ ካህናቱ ዘንድ ሄዳ ስለ ቅዱስ ቶማስ ሃያ ሁለት ዓመት በዚያ ስለመኖሩ ነገረቻቸው ቦታውንም አመለከተቻቸው እነርሱም ባገኙት ጊዜ አንስተው ተሸከሙት እየዘመሩና እያመሰገኑም ወደ ቤተ ክርስቲያን አደረሱት በቤተ መቅደስ ፊት ለፊት በወንበሩ ላይ አስቀመጡት ምእመናንም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ ከርሱ ይባረኩና የተቆረጡ ሕዋሳቱንም ይሳለሙ ነበር፡፡ ከቦታ ቦታ ይዘዋወር የነበረውም በቅርጫት ኹኖ በዘህያ ላይ ተጭኖ ነው፡፡

ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ የከበሩ ፫፻፲፰ ኤጲስ ቆጶሳትን (ሠለስቱ ምዕት) የአንድነት ጕባኤን በኒቂያ አገር በሰበሰበ ጊዜ ይህ አባት (ቅዱስ ቶማስ) ከሠለስቱ ምዕት አንዱ ነበር፤ ወደ ኒቅያ ጕባኤ በቅርጫት ሁኖ በአህያ ተጭኖ እየሄደ መሆኑን አርዮሳውያን ሲሰሙ፤ ቶማስማ በጕባኤው ከተገኘ ተከራክሮ ይረታናል አንችለውም በማለት መንገድ ላይ ባደረበት ይዘውት ይጓዙት የነበሩትን አህዮች በጨለማ በሰይፍ መተዋቸዋል፤ ነገር ግን ሌሊት ሊነጋጋ ሲል ለመንገድ ሲነሱ ቶማስ በተዓምራት አግልጋይ ረድኡን የተቆረጡትን የአህያዎቹን አንገታቸውን ከሰውነታቸው አጋጥመው ይነሳሉ ብሎ ሲያዘው የአንዱን አህያ ከሌላኛው አህያ ቢያጋጥመውም ቅሉ አህዮቹ ሕይወት አግኝተው ጕባኤ ኒቅያ አድርሰውታል፤ በዚያም አርዮስን መልስ እስኪያጣ ድረስ በጽናት ሲከራከረውና መልስ ሲያሳጠው የጕባኤው ሊቀ መንበር ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እስኪደነቅ ድረስ በማየቱ ሃይመኖትስ የእነ ቶማስ ዘመርዓስ ነች ብሎ አጽንቶ ወስኗል፡፡ በጕባኤውም አርዮስን ተከራክረው ከረቱ በኋላ አውግዘው ለይተውታል፤ ከዚህ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራቸውና እንደመራቸው የሃይማኖትን ትምህርት በአንደበታቸው ተናገሩ፤ ሕግና ሥርዐትን ሥጋዊና፤ መንፈሳዊ ፍርድንም ሰሩ። ቅዱስ ቶማስ ወደ መንበረ ሢመቱ ከተመለሰ በኋላ ካህናቱና መንጋዎቹን ሁሉ ሰብስቦ አነበበላቸው እርሱንም እንዲያስተውሉት እንዲጠበቁትም በመጠበቅም እንዲጸኑ አዘዛቸው፡፡ ይህ አባት ለ፵ ዓመት ያህል በሢመቱ አገልግሎ በነሐሴ ፳፬ ቀን አርፋል፡

በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
፠፠፠
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
1.1K views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:52:39
882 views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ