Get Mystery Box with random crypto!

፮. #መካነ_ሥላሴ_ደቡብ_ወሎ_ወረኢሉ፤ (በ1500ዓ.ም. በዐፄ ናዖድ የተመሠረተና በልጁ በዐፄ ልብ | Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

፮. #መካነ_ሥላሴ_ደቡብ_ወሎ_ወረኢሉ፤ (በ1500ዓ.ም. በዐፄ ናዖድ የተመሠረተና በልጁ በዐፄ ልብነ ድንግል ሥራው የተጠናቀቀ፤ ባለ 16 መንበር፥ በዕንቊና በወርቅ የታነጸ የነበረ፤ /ኋላ በግራኝ የፈረሰ/፤ ነገር ግን ጽላቱ በዐፄ ምኒልክ ዳግማዊ ወደ አ.አ. መጥቶ ቀድሞ 4 ኪሎ መካነ ሥላሴ አሁን መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ በመባል የሚጠራ)፤ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና ወሎ መካነ ሥላሴ ላይ በቀድሞው ቅርጹ በባለ 16 መንበር ተደርጎ 2009 ዓ.ም. አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በመገንባት ላይ ይገኛል፤ (ለሕንፀታ ቤቱ ሁላችንንም ያብቃን)፡፡
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ወረኢሉ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወረኢሉ፡፡
፯. #ፀዓዳ_አምባ_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል_ገዳም፤ (በ1669 ዓ.ም. የተገደመ፤ መሄጃ መንገዱ እጅግ አስደናቂና በ2ቱም በኩል ገደል የኾነ)
አድራሻ፤ ኤርትራ፥ ዞባ አንሰባ፥ ከረን፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ (በአውሮፕላን)→ ኤርትራ → ከረን → /25ኪ.ሜ/ ፀዓዳ አምባ፡፡
፰. #ጎንደር_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በጥር 26 ቀን 1683 ዓ.ም. በዐፄ አድያም ሰገድ የታነጸ፤ በጎንደር ከተማና ዙሪያ ከሚገኙ 44ቱ ታቦታተ ጎንደር በአሠራሩ ልዩ የኾነ፤ በ1880ዎቹ ድርቡሽ ጎንደር ከተማን ሲያጠፋ ከ44ት አብያተ ክርስቲያናት በተአምራት ሳይቃጣል የቀረ፤ የታላላቅ ሊቃውንት /የእነ ሊቁ ክፍለ ማርያም/ መፍለቂያ፡፡
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፱. #ናርጋ_ሥላሴ_ገዳም፤ (በጣና ሐይቅ ላይ ካሉ ደሴቶች ትልቁ በሆነው በደቅ(7ት ደብር ሃገር) ደሴት ከሚገኙ 7 ገዳማት አንዱ)፡፡ (በአፄ በካፋ ባለቤት በበእቴጌ ምንትዋብ /1730-1755 ዓ.ም./ የተሠራ፤ ግድግዳዎቹ በሚያስደንቁና ልቡናና መንፈስን በሚመስጡ ሥዕላት ያሸበረቁ፡፡)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጣና ሐይቅ (ከባሕር ዳር ከተማ ሰሜናዊ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ /በጀልባ 3 ሰዓት/፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባህር ዳር/ጎንደር → በጀልባ/በታንኳ/ /በመርከብ/ ናርጋ ሥላሴ፡፡
፲. #ጨለቆት_ሥላሴ_ትግራይ፤ መቀለ አጠገብ፡፡ (በ1787 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲኾን ተካዩ ደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ክፍለ ኢየሱስ ሃገረ ገዢ ናቸው) (የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያ ነው፤ ለአብነትም በዐፄ ዮሐንስ /1864 – 1881ዓ.ም./ ዘመነ መንግሥት አራት ጳጳሳትን እንዲያመጡ ከተላኩት መካከል አንዱ ሊቅ አለቃ ዐሥራት ዘውጉ ዘጨለቆት ሥላሴ ናቸው፡፡) (የእንግሊዝ ጦር ዐፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ ሰብስቦት የነበረውን ዘርፈው ሲወስዱ የበዛባቸውን ለዚህ ደብር ሰጥተው ሄደዋል፡፡)
አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ እንደርታ አውራጃ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ /እንደርታ/፡፡
፲፩. #ሐረር_ሐድሬ_ጥቆ_መካነ_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት፥ ሐረር ከተማ፥ ሐድሬ ጥቆ ወረዳ፤ (በዐፄ ኀይለ ሥላሴ በ1941-43 ዓ.ም. የተሠራ)
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐረር፡፡
፲፪. #ድሬዳዋ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ድሬዳዋ ሃገረ ስብከት፥ ድሬዳዋ፥ ሳቢያን ሰባተኛ ሰፈር፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ድሬዳዋ፡፡
፲፫. #ኤረር_በዓታ_ወቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምሥራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ አድአ ወረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ዘይት → ኤረር፡፡
፲፬. #ሰንዳፋ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት፥ ሰንዳፋ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ሰንዳፋ፡፡
፲፭. #ሱልልታ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት፥ ሱልልታ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ (ከፒያሳ /አዲሱ ገበያ/ → ሱልልታ፡፡
፲፮. #ጫንጮ_ሞዬ_ጋጆ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት፥ ጫንጮ፥ ሞዬ ጋጆ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ (ከፒያሳ /አዲሱ ገበያ/ → ጫንጮ → ሞዬ ጋጆ፡፡
፲፯. #ሚዳ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መርሐ ቤቴ፥ ሚዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ሚዳ /መርሐ ቤቴ/፡፡
፲፰. #ደሴ_ደብረ_ቤቴል_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደሴ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ፡፡
፲፱. #እንጂባራ (ኮሶ በር)_መንበረ_ፀባዖት_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ እንጂባራ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → እንጂባራ፡፡
፳. #ባሕር_ዳር_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ባሕር ዳር ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳራ /ቀበሌ 07/፡፡
፳፩. #ጎንደር_አዘዞ_መናኸሪያ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ አዘዞ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንድረ /አዘዞ/፡፡
፳፪. #ናዝሬት_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምሥራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ናዝሬት /አዳማ/፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት /አዳማ/፡፡
፳፫. #ቡታጅራ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ቡታጅራ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ቡታጅራ፡፡
፳፬. #ጉብርየ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ጉብርየ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ጉብርየ፡፡
፳፭. #ሐዋሳ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሲዳማ ሐዋሳ ሃገረ ስብከት፥ ሐዋሳ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐዋሳ፡፡
፳፮. #ቦረዳ_ዳግማዊ_ዮርዳኖስ_ቅድስት_ሥላሴና_ሚካኤል፤
አድራሻ፤ ጋሞ ጎፋ ሃገረ ስብከት፥ ቦረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ቦረዳ፡፡
፳፯. #ምሥራቅ_ሐረርጌ_ፈዲስ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት፥ ፈዲስ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ፈዲስ፡፡
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከበርባቸው_ #፬ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #አሜሪካ_ሲያትል_መንበረ_ፀባኦት_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ዋሽንግተን ዲሲ ሃገረ ስብከት፥ ዋሽንግተን ስቴት ሲያትል (ፌደራል ዌይ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ጀርመን ሐሚልተን፡፡
፪. #አሜሪካ_ሚኒሶታ_ጽርሐ_አርያም_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ሚኒሶታ ሃገረ ስብከት፥ ሚኒሶታ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → አሜሪካ /ሚኒሶታ/፡፡
፫. #ጀርመን_ሐሚልተን_ኦንታርዮ_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ጀርመን ሐሚልተን ሃገረ ስብከት፥ 420 Aberdeen Ave. Hamilton, ON L8P 2R5፥ ሞዬ ጋጆ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ጀርመን ሐሚልተን፡፡
፬. #ሮም_ደብረ_ከነዓን_ቅድስት_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ኢጣሊያና አካባቢው ሃገረ ስብከት፥ ሮም፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ኢጣሊያ /ሮም/፡፡አቅጣጫ ከ በኢ.ቦ ዋሊ ገጽ
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ