Get Mystery Box with random crypto!

መዓዛ ሠናይ

የቴሌግራም ቻናል አርማ meazasenay — መዓዛ ሠናይ
የቴሌግራም ቻናል አርማ meazasenay — መዓዛ ሠናይ
የሰርጥ አድራሻ: @meazasenay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.95K
የሰርጥ መግለጫ

☞ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እንወቅ
☞እንረዳ
☞እንማማር
♥♥♥♥♥♥
ለበለጠ መረጃ @Tadi16 ላይ ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን፡፡

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-20 12:25:25 የወጣቶች ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት)

በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ
#ክፍል_1

ሕልመ ሌሊት ምንድነው ?

በዐፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መስራትም ይጀምራል ። በዚህ ጊዜ ከኀፍረተ አካል ዘርዐ ብእሲ (የወንድ ዘር ) ይወጣል ። ወንድና ሴት ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ሴቲቱ ማኀፀን በመግባት ፅንስ እንዲፈጠር የሚያደርገው ይህ ፈሳሽ ንጥረ ነገር ነው ። ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚወጣቸው በተለያየ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው ። ይህ ሲሆን በሳይንስ እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል ። የዚህ አይነቱን ሕልም መፅሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ #ሕልመ_ጽምረት በሌላ ቦታ ደግሞ #መስቆርርተ_ሕልም ሲለው ይገኛል። ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ #ዝንየት መታኝ ወይም #ሕልመ_ሌሊት አገኘኝ ይላል

ሕልመ ሌሊት ኃጢአት ነውን ?

በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሰት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ ።ስለዚህ ሕልመ ለሊትን በጥቅሉ ኃጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም ። እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በጥቂቱ ለማየት ያህል

ሀ. አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፋኛ ይዋጓቸዋል ። የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን አያሸልቡም ። ያንቀላፋው ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን አይጠብቁም ። አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፋ ክፋ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል ። አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት ግንኙነት ሲያደርጉ በምትሐት ያሳዩታል። በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈፅም ያድራል ። መፅሐፈ መነኮሳት "ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፋ ሐሳብ በማሳሰብና በማሰራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል " ይላል። በዚህ ጊዜ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ፣ ከመፀፀትና ከመቆጨት ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም ከሆነ ፤ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል ፣ የሚዳራ ፣ የሚዛለል ፣ ወደ ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህን ነገሮች ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት በሕልሙ በፈፀማቸው ጊዜ በተግባር እንደ ፈፀማቸው ይቆጠራል ።ሌላው ከሥራ ብዛት ሕልም እንዲታይ ጠቢቡ ሰሎሞን[ " ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል " በማለት የተናገረው ያስረዳል (መክ5:3) እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሰት ይችላል። ክፋ ምኞት በሕልምም ማርከሱ አይቀርም ። ሐዋርያው ይሁዳ " እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ " ያለው ለዚህ ይጠቀሳል ። (ይሁዳ 1:8) እንደሚታወቀው ነፍስ አትተኛም ። ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው ብላ ማመካኘት አትችልም ። ነፍስ በረከሰ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የምትችለው ሥጋ ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው ። ሌላው ሕልመ ለሊትን እንደ ኀጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው ። ጾም ለፅድቅ ስራ ሁሉ መሰረት እንደሆነው እንደዚሁም አብዝቶ መመገብ የኀጢአት ሁሉ መሰረት ነው ። "እህል ጉልበትን ያጠነክራል ተብሏልና ።ሰው ሁሉ ለቁመተ ስጋ ያህል ብቻ መመገብ ያሻዋል ። ከዛ ውጭ ግን አብዝቶ መመገብ "ሆዳቸው አምላካቸው " እንደ ተባለው ለህልመ ለሊት ያጋልጠናል ።
... ይቀጥላል ...
https://t.me/meazasenay
555 views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 08:16:43 ሕይወተ ወራዙት / የወጣቶች ሕይወት
(በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ)

መግቢያ

ወጣቶችና ፆሮቻቸው (የወጣቶች ፈተና
በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሰረት ምእመናን በ#5 መደብ ይመደባሉ ። ይህም መደብ "ፆታ ምዕመናን "ይባላል ። 5ቱ ፆታ ምዕመናን የሚባሉት ካህናት ፣ መነኮሳት ፣ አዕሩግ (አረጋውያን) ፣ ወራዙት (ወጣት ወንዶች ) እና አንስት (ሴት ወጣቶች) ናቸው ። አምስቱም ፆታ ምእመናን በየራሳቸው የሚቸገሩበት ዓቢይ ፈተና አለ

"ፆር " በመባል የሚታወቀው ይህ ዓቢይ ፈተና ነው ።የካህናት ፆራቸው ትዝህርት (ትዕቢት) ነው ፤ የመነኮሳት ፆር ስስት ሲሆን ፤ የአረጋውያን ፆራቸው ደግሞ ፍቅረ ንዋይ ነው ። ቀሪዎቹ ወጣት ወንዶች ሲሆኑ ዐቢይ ፆራቸው ዝሙት ነው ። የወጣት ሴቶች ዓቢይ ፆር ደግሞ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥን መውደድ ) ነው ። ይህ ማለት ግን ዋና ዋና ፈተናቸውን አንጓሎ ለመናገር ነው እንጂ እያንዳንዱ ፆታ ምዕመን የሚፈተነው በአንድ ነገር ብቻ ነው ማለት አይደለም ።" ሰውነቱ በደዌ የተጠቃን ሰው ጉንፋን እንኳን እንደሚያይልበት " እንዲሁ በዋና ፈተናው ድል የተደረገ ምዕመን ሌሎች ጥቃቅን ፈተናዎች ይረባረቡበታል

ነገር ግን ዋናውን ፆሩን ድል ካደረገ የሚመጡበትን ሌሎች ፈተናዎች በቀላሉ ድል ለማድረግ ይቻለዋል ። ወጣቶች ልዩ ልዩ ፆር (ፈተና) እንዳለባቸው ነገር ግን ዕድሜያቸው እየገፋ በመጣ ቁጥር ወጣትነታቸው ሲያልፍ የወጣትነት ፈተናቸውን አብሮ እንደሚያልፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ተናግሯል ። "ሥጋን ንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለት እንደዚሁ ነፍስም በወጣትነት ወራት በደዌ ኀጢአት ትያዛለች

ትዕቢተኛነት ፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት ፣ በፆታ መፈላለግና ይህን የመሳሰለ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርበታል ። የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋ ፈፅሞ ከሰውነት ይርቃል " ብሏል ። ስለዚህ ወጣትነታችንን በጥበብ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ልናሳልፍ ይገባል ። የዚህ ፅሁፍ አላማም ፈተናዎቹን አውቀን እንዴት ማለፍ እንዳለብን መንገድ ማመላከት ነው ።

... ይቀጥላል ...
https://t.me/meazasenay
506 views05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 08:12:30 ልጁም ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ለምን አለ ? 1ኛ ቆሮ 15:24

ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልዕክት ለምን እንደፃፈው ከመመልከታችን በፊት እስኪ የሚከተለውን ጥቅስ እንመልከት ፦ "በሚድኑትና በሚጠፋት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና ለነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለነዚያ ለህይወት ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን ለዚህም ነገር የሚበቃ ማነው ? የእግዚአብሔርን ቃላት ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎች አይደለንምና በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን " 2ቆሮ 2:9 ታዲያ ይህንን አባባል ማለትም ለምን ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል አለ ሲባል ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ስለሆነ አልያም አምላክ ስላልሆነ አይደለም

ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እርሱ ከሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስ ፊት ሳይታይ ፣ ተራሮች ሳይቆሙ፣ የአየር ርዝመት ሳይከፈት በባሕርይ የነበረ ነው " እንዳለው እርሱ ከሁሉ በፊት የነበረ አምላክ ነው ። አንድ ሃይማኖት ሃይማኖት አለኝ የሚልና ስለአለበት ሃይማኖት እውቀት አለኝ የሚል ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመምዘዝ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም እያሉ ከመቃዠቱ በፊት ለምን እንደተነገረ ማወቅ አለበት

ጥቅሱ ከላይ ስለሞት እየተናገረ መምጣቱን እንረዳለን ። የሁዋላ ጠላት የተባለው ሞት ነው ። ሞት ሁሉን ገዝቶአልና ነገር ግን ሁሉን ካስገዛለት ከወልድ(ከክርስቶስ) ሞት እንደሚያንስ ይታወቃልና ከሞት ስልጣን የክርስቶስ ስልጣነ መለኮት ይበልጣልና ። ሞት በሰው ልጆች ላይም እንዲሰለጥን ያደረገው ባለቤቱ ወልድ ነውና ። በዕለተ ምፅአት ሁሉ በተገዛለት ጊዜ (ለሞት) ያን ጊዜ ወልድም ሁሉን ላስገዛለት ለሞት ተገዝቷል ። መቼ ? በዕለተ ዓርብ ። ስለዚህ የዕለተ ዓርብን ሞቱን መናገሩ ነው ። በዕለተ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው በገዛ ፍቃዱ ለይቷልና ሞት ለ3 መዓልትና ለ3 ለሊት ጌታን በቁጥጥር ስር አድርጎ ነበርና ይህም የጌታ ፍቃድ ስለሆነ እንጂ እንደ ሌሎች ሳይወድ በግድ አይደለም ። ስለዚህ ጥቅሱ #ክርስቶስ_ገዢ_አምላክ_ኖሮት_ይገዛል_ማለት #ሳይሆን_ለሞቱ_የተነገረ_ነው

"ከግርማው የተነሳ የሞት ደጆች ይከፈታሉ የሲኦል በሮችም ባዩት ጊዜ ይደነግጣሉ ከሰማይ በታች ያለውም ስፋቱን ከሰማይ በላይ የሚሆነውንም እርሱ ያውቃል " ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሃይማኖተ አበው

"የአንተን ስም ሰምቶ ሞት ይደንግጥ ቀላያትም ይሰንጠቁ ፣ ጠላትም ይረገጥ የጥፋት መንፈስ ይንቀጥቀጥ ከይሲም ይወገድ ፣ አለማመንም ይራቅ ወንጀለኛም ይቸገር ቁጣ ጸጥ ይበል ቅናት ጥቅም አያግኝ ፣ ኃጢአትን የሚያዘወትር ይገሰጽ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ ድካም ይወገድ ሐሰተኛ ይጣል ፣ መርዝ ያላቸው የፍጥረቶች ወገን ሁሉ ይበተኑ ። " ቅዳሴ እግዚእ
https://t.me/meazasenay
497 views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:33:31 ያችን ሰዓት ልጅም(ወልድም) ቢሆን ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም ለምን አለ ? ማቴ 24:36

ይህንን ጥቅስ በመጥቀስ አምላክ ቢሆን ሁሉን ያውቅ ነበር ይላሉ። በመሰረቱ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን እርሱ ባያውቀው ኖሮ ምልክቱን ባልነገራቸው ነበር የተናገራቸው ምልክቶች በሙሉ ማወቁን የሚያሳዩን ናቸው። "ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው " ይላል ሮሜ9:5 ከሁሉ በላይ ከሆነ ደግሞ ማንም ከእርሱ በላይ የለም ። "ያለውና የነበረው ፣ ፊተኛውና መጨረሻው እርሱ ነውና '' ራዕ 1:9 ነገር ግን ይህንን ቃል ለምን ተናገረው ቢሉ ስለ ብዙ ምክንያት ተናግሮታል

#1ኛ.ፍጹም ሥጋ መዋሀዱን ሲያጠይቅ ነው ሥጋ ደግሞ በራሱ እውቀት የለውምና

#2ኛ.ወዲያው የሚመጣበትን ቀን ቢነግራቸው እንዳይደነግጡ ፈልጎ የምነግራችሁ ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም አላቸው

#3ኛ.በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች 120 ዓመታት የንስሐ ዘመን ቢሰጣቸው 100 ዓመት በልተን ጠጥተን ፣ ጨፍረን ፣ 20 ዓመት ሲቀረን ንስሐ እንገባለን ብለው እርኩሰትን ስለፈፀሙ በመሐል ከሀጢአታቸው የተነሳ በንፍር ውሃ ተጥለቅልቀው ጠፍተዋልና አሁንም በዚህ ዓመት በዚህ ወር እመጣለው ቢላቸው ሰንፈው ንስሐ ሳይገቡ ገና ነው እያሉ እንዳይሞቱ የሚመጣበትን ቀን መች እንደሆነ አልተናገረም " ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ ቤቱም ሊቆፍር ባልተወው ነበር ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ የሰው ልጅ በማታስቡበት ጊዜ ይመጣልና"ማቴ 24:43

#4ኛ.ሌላው ጌታ ይህንን ቃል የተናገረው ዓለምንና ጊዜያትን ሁሉ የፈጠረና በሁዋላም ሊያሳልፋቸው የሚችል ፈጣሪ ብቻ ሁሉን የማወቅ ስልጣን እንዳለው ሊገልጽልን አስቦ ነው። ጌታም ከአብ ጋር አንድ ስለሆነና የአብ የሆነው ሁሉ እውቀትም ስልጣንም የእርሱ ስለሆነ ስለዚያች ቀን እርሱም ያውቃል ምክንያቱም ወልድ በመለኮቱ ከአብ ጋር እኩል ነውና (ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ)

እንግዲህ ክርስቶስ ሁሉን እያወቀ ራሱን ከአብ ለይቶ ያችን ቀን እንደማያውቅ የተናገረበት ምክንያት እርሱ ከአብ ተለይቶ ማለትም ወልድ በተለየ አካሉ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረ አላዋቂ ሥጋን እንደተዋሀደ ለማስረዳት ነው ። ይህም ማለት ክርስቶስ ፍጹም ሰው በመሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ወገናዊነቱን ያመለክተናል ፤ ከእኛ ጋር ያለውን ዝምድና ይገልጽልናል እርሱ ሰው ሆኗልና የሰው ልጅም ተብሏልና ። ክርስቶስ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ በመሆኑ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ ሲሆን በሰውነቱ (ስጋን በመዋሀዱ) ከሰዎች ጋር አንድ ሆኗል ። ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ ዳግማዊ አዳም ተብሏል ። ም/ቱም የአዳምን ስጋና ነፍስ ተዋህዷልና

የምድር ስርዓት ይሻራል ፍጥረት ሁሉ አንድ መንጋ ይሆናሉ ፣ በአንድ እረኛ ይሰማራሉ ስለጌታችን መምጣት ከቅዱሳት መጽሐፍት እንደተማርነው ጊዜውንና ሰዓቱን የሚያውቅ ከፍጡር ወገን ከቶ አይገኝም ሆኖም ቅዱሳት መጽሐፍት እንደነገሩን መምጣቱ የማይቀር ነው እስከዛ የድህነት ስራ መስራትና ወንጌልንም ለዓለም መስበክ ያስፈልጋል "እነሆ በቶሎ እመጣለው ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ሁዋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ "ራዕ 22:12
https://t.me/meazasenay
529 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:32:00 ዮሴፍ ለምን እጮኛዋ ተባለ ?

እጮኛ የሚለው ቃልና ፍቺ ለሚያባት ሴት ብቻ የተሰጠ ሳይሆን በጠባቂነትም ላለ ይሰጣል። መናፍቃን እጮኛዋ የሚለውን ቃል በመያዝ ዮሴፍ ድንግልን እንዳገባትና ከሷም ልጅ እንደወለደ ይናገሩ (እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣቸው) ነገር ግን እንደዛ አይደለም እስቲ ድንግል ማርያም የዮሴፍ እጮኛ የተባለችበትን ምክንያቶች እንመልከት፦

#1ኛ. የዳዊት ልጅ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው ። ምክንያቱም በሴት ትውልዱ ቢቆጠር አይሁድ አይቀበሉም ማቴዎስ ትውልዱን የፃፈው በዮሴፍ ነው ። ለዚህም ነው መልዐኩ "ዮሴፍ ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት በአሰበ ጊዜ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ "ያለው ማቴ1:10 ለባልነት ቢሆን ኖሮ ግን በስውር ሊተዋት ፈጽሞ አያስብም ነበር። እዛው ም 1:16 ላይ ስንሔድ በኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ ውስጥ ተፅፎ የምናገኘው ዮሴፍን እንጂ ማርያምን አይደለም ።

#2ኛ.እንዲጠብቃት ነው ለዚህም ነው መልዐኩ ዮሴፍ ትቷት እንዳይሄድ የተናገረው

#3ኛ.እንዲያገለግላት ነው ። በስደቷ ጊዜ ይዞ እንዲሄድ የታዘዘው ዮሴፍ ነውና ። ለሚስትነት ታጭታ ቢሆን ግን ከወለደች ቡሃላ ለዮሴፍ ሚስትህን ይዘህ ሂድ ይለዋል እንጂ ሕፃኑንና እናቱን ብሎ አይናገረውም ነበር ። እንደውም ከወለደች ቡሃላ ዮሴፍን እጮኛህንም ይዘህ ሂድ ሲለው አንመለከትም ። ለዚህም ነው እንዲያገለግላት በእጮኝነት የተሰጠው ማቴ2:13

#4ኛ.እርሷ ከሰው ዘር ከሰው ወገን መሆኗ ይታወቅ ዘንድ ነው ። መጽሐፍ ቅዱስም "የአብርሃም ዘር ይዞአል "ያለው ለዚ ነው ዕብ 2:15 ምክንያቱም እርሷን ኃይለ አርያማዊት ክርስቶስን መልዐክ ብለው የሚነሱ መናፍቃን አሉና ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንዴት ትወልዳለች እንዳይሉ

#5ኛ.በዘፀ 5:23 መሰረት "ሴት ወንድ ካጠገቧ ሳይኖር ፀንሳ ብትገኝ ተወግራ ትገደል " የሚል ሕግ አይሁዳውያን ስላላቸው ተወግራ እንዳትገደል ነው ። እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች እጮኛ አሰኝተዋታል እንጂ እጮኛነቱ ለመገናኘት ለባልና ለሚስት ግንኙነት አይደለም ።

https://t.me/meazasenay
476 views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 09:22:29 አፅናኝ የተባለው ማነው ?

ሙስሊም ወንድሞቻችን ይህንን ጥቅስ ከመፅሐፍ ቅዱስ በመውሰድ አፅናኝ የተባለው ነብይ (ነብዩ መሀመድ) እንጂ መንፈስቅዱስ አይደለም ይላሉ። በመሰረቱ እነሱ አሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አላለም ። ጌታም ነብይ እልክላቹዋለው አላለም ። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀበልን ሁሉን ነገረን አሉ እንጂ ነቢይ ተላከልን አላሉም ። ታዲያ ጌታችን እልክላቹዋለው ያለው ማንን ነው ? ከተባለ ያለ ምንም ጥርጥር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው

ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ በግልጽ አስቀምጦታል የተስፋውም ፍፃሜ እንዲህ ነበር ፦ "በዓለ ሀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉ በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ ተቀምጠውም የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር "የሐዋ 2:1-4 ታዲያ ከየት መጥቶ ነው መንፈስ ቅዱስ ነቢይ የሚሆነው ? በጭራሽ ነቢይ አይደለም

ያልተባለን ማውራት ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚሉት አበው ይህንን ትምህርት ሐዋርያትም ፣ ነብያትም፣ ሊቃውንትም አላስተማሩም። መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነበር ። እርሱም ከሐዋርያት ጋር በፆም በፀሎት የተጉ 120ዎቹን ቤተሰብ በመወከል ከተለያየ አገራት በበዓሉ ላይ ለመገኘት ለመጡት ሰዎች ልብን የሚነካ መንፈሳዊ ክፍተትን የሚሞላ ፣ ጥያቄን የሚመልስ ንግግር አደረገላቸው። የንግግሩ ዋና ማዕከል ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የንግግሩ ርዕስ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነበር ። ፈሪና ከሀዲ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቅ ድፍረትን ተሞልቶ የመጀመሪያውን የምስራች አወጀ ከዚያም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 3000 ሰዎች ያለ ምንም የጦር መሳሪያ ኃይል ወዲያው ለወንጌል ተሸነፋ

የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶክ ፍቅሩ ፣ ሞቱ፣ ትንሳኤው ፣ ለሰው ልጆች ያደረገውን ቤዛነት ሲሰሙ በወንጌል አምነው ተጠመቁ የሐዋ 2:41 ይህ ይላካል የተባለው የአጽናኙ የመንፈስ ቅዱስ ጅማሬ ነበር ። ከዚህም የተነሳ የጥበበኞች ጥበበኛ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ ሐዋርያትም ዳግመኛ ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ መስበክ እንደማይቻላቸው ያውቃልና በሰናኦር ሜዳ የተበተኑትን የዓለም ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ውስጥ ሰብስቦ ያኖር ዘንድ የጽድቅ መንፈስ ጰራቅሊጦስ ተላከ

መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች በየራሳቸው ቋንቋ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ከሰሙ በዋላ ደቀ መዛኑርቱን ሰክረው ነው እንጂ ይህ ያልተለመደ ምንድነው ? እያሉ በመደነቅ ማጉረምረም ጀመሩ ። ጴጥሮስም "ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ 3:00 ነውና ነገር ግን በነብዩ ኢዩኤል የተባለው ነው " የሐዋ 2:14 በማለት አስረዳቸው ። ከጠዋቱ 3:00 መጠጥ አይጠጣም ነበርና ከሐዋርያው ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የምንረዳው ወይም የምንማረው እንደ መሰለን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ከአተረጓጎም ስርዓት ውጪ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን ነብይ ነው ብሎ መገመትና መተርጎም አግባብ አይደለም ። እንደመሰለን መተርጎም አላዋቂነት ነው 1ጴጥ 4:11
https://t.me/meazasenay
495 views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:56:16 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተ ነህ ለምን አለ ? ዮሐ 17:3

ሙስሊሞ እና የይሆዋ ምስክሮች የተባሉ ወገኖቻችን ክርስቶስ አምላክ አይደለም ብለው ከሚያቀርቡት ጥቅስ አንዱ ይሄ ነው ።  ይህን ምዕራፍ ስንመለከት ጌታችን በዚህች ምድር ላይ በስጋው ወራት ሊሰራ ያቀደውን ጨርሶ ወደ ክብሩ ሊሄድ ሊሰቀል ሲል የተናገረው ቃል ነው ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እርሱ ከአብ ጋር እኩል በመሆኑም "እኛ አንድ እንደሆንን "በማለት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ስልጣን እኩል ጌትነት እንዳለው እንረዳለን ። ያላመኑት ግን "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3 የሚለውን በመጥቀስ ጌታ አምላክ እንዳልሆነ አብ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አሕዛብ ይናገራሉ። እስኪ በሌላ ስፍራ ላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እንመልከት ፦

"ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚቻለው ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኀኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ግርማ ኃይልም ስልጣንም ይሁን አሜን " ይላል ይሁዳ 1:25 በዚህ አገላለፅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አምላክ እንደሆነ ተገልፇል ። በሌላም ስፍራ ፦ "ስለዚህ እላችዋለው ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም በሰው ልጅ ላይ ቃል  የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል በመንፈስቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም " ማቴ 12:31 ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ይላል፦

"ብቻህን አምላክ የሆንህ አንተ የላከውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3  ታዲያ ሶስቱም ብቸኛ ከተባሉ የቱን እንምረጥ ? ዳሩ ግን ይህ ለምን እንደተባለ ለኛ ለክርስቲያኖች ግልጥ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እንዳለው ፦ "ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳን የተከደነባቸው ለሚጠፋ ነው " 2ኛ ቆሮ 4:3 ታዲያ ጌታችን ይህን ስለምን ተናገረው ቢሉ የዘላለም ሕይወት የሚገኝባት ሃይማኖት ይህች ናት አንተ የባህርይ አምላክ እንደሆንክ እኔም የባህርይ አምላክ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ቢያውቁ እውነተኛ ሃይማኖች ይህቺ ናት ማለቱ ነው ።  ጌታ በአንዳንድ ቦታ ላይ አምላክ ወይም እግዚአብሔር ብሎ እንደ ሰው መጸለዩ በእውነት የሰውን ባህርይ ባህሪው ማድረጉን ሊያስረዳን ፈልጎ ነው እንጂ በባሕሪው ከአብ የሚያንስ ሆኖ አይደለም

እንደ ሰው አምላኬ ብሎ ባይፀልይ ኖሮ በእርሱ ዘንድ ሰውነት የለም ወይም መለኮት ተስብእትን(ሰውነትን) ውጦ አጥፍቶታል በተባለም ነበር ። ይህ የጌታችን አነጋገር በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ #ለአጽድቆተ\_ትስብእት ተብሎ ይተረጎማል፡ ስለዚህ እነርሱ እንደሚሉት ሳይሆን ጌታችን ስለዚህ ተናገረው እንጂ አምላክ ስላልሆነ አይደለም ። አምላክ ስለመሆኑማ ዮሐንሰ እንዲህ በማለት ገልጾታል ። "እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው " 1ዮሐ5:20 "የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ ዋህድ ነፍስንና ስጋን ነስቶ ሰው ሆነ ባልንም ጊዜ ስለዚህም ነገር ቢሆን እነዚያ እንደሚያምኑ መቀላቀል የለበትም የቃል ባህርይ የስጋን ባህርይ ወደ መሆን አልተለወጠም ሁለት ባህርይ ያለመለወጥ ባለመቀላቀል ጸንተው ይኖራሉ እንጂ " ሃይማኖተ አበው ዘ ኤራቅሊስ

"የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ ሲሆን ሰው ይባላል ፤ ዳግመኛም የአዳም ልጅ ይባላል ሰማያዊ ሲሆን በፈቃዱ ምድራዊ ሆነ ። በመለኮቱ መከራን መቀበል ሳይኖርበት ሰው በመሆኑ መከራ ተቀበለ ፈጽሞ አንዱ በአንዱ ያደረ ነው አይባልምና ለአንዱ ለእግዚአብሔር ልጅ ሁለት አካል ሁለት ገጽ ሁለት ባሕርይ የለውም " ሃይማኖተ አበው ዘ አትናቴዮስ ስለዚህ ክርስቶስ ፍፁም ሰው የሆነ ፍፁም አምላክ ነው አምላኬ ሲል ብትሰሙት በተዋሀደው ስጋ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል ነው
https://t.me/meazasenay
581 views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:10:47 #ስለኛ_የሚማልደው_ለምን_አለ ?

መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ አድርገው ከሚያቀርቡበት ውስጥ አንዱ ጥቅስ ይሄ ነው ፦ "የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው ? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞም ስለኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው " ሮሜ 8:34 ከላይ እንደ ተገለጠው #ኮነነ የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ፈረደ ገዛ ማለት ነው ። የሚኮንን ማነው ? ሲል የሚገዛ የሚፈርድ ማነው ? ማለት ነው ። ምላሹም በጥቅሱ እንደተገለጸው #ክርስቶስ\_ኢየሱስ ነው ። መጻሕፍት እንደሚመሰክሩት እኛም እንደምናምነው መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው አስታራቂ መሆኑ አማላጅ አያሰኘውም አይደለምም

የእርሱ የማስታረቅ ስራ ከአማላጅነት ጋር የሚነጻጸር አይደለም ። ሁልጊዜ ስለ ክርስቶስ ስናስብ ከአብና ከመንፈስቅዱስ ጋር ያለውን አንድነት መዘንጋት የለብንም ። እንግዲህ ይሄ ጥቅስ መናፍቃን እንደሚሉት የክርስቶስን አማላጅነት የሚገልጥ ሳይሆን የክርስቶስን ፈራጅነት የሚያሳይ ነው ። ጌታችን ኃጢአትን ይቅር የሚል ፣ በደልን የሚደመስስ ፣ ምሕረትን የሚሰጥ ከራሱ ጋር ያስታረቀን አስታራቂያችን ፣ የታረቅንበት መታረቂያችን ፣ የታረቅንበት ታራቂያችን ነው እንጂ አማላጃችን አይደለም ። " እርሱ ክርስቶስ ገዢ ነው ፈራጅ ነው " ሮሜ 14:10 እንግዲህ ጌታ ፈራጅ ከሆነ እንዴት አማላጅ ሊሆን ይችላል ? ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ መባሉ እግዚአብሔር ስለሆነ ሲሆን እግዚአብሔር ከሆነ እንዴትና ከማን ይማልዳል ? #ቀኝ የሚለው ቃል ሥልጣንን፣ ክብርን፣ ሃይልን የሚያሳይ ነው

ከአብ ጋር ያማልደናል እንዳንልም "እኔና አብ አንድ ነን "ዮሐ10:30 ብሏል ። ታዲያ ስለኛ የሚማልደው የሚለው እንዴት ነው ቢሉ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠነቀቀው ከዘይቤ ይልቅ ለምስጢር ነው ። ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ የሚማልደው ሲል ጌታችን ከመወለዱ ከ700 ዓመት በፊት የነበረው ኢሳያስ ደግሞ ስለ አመፀኞች ማለደ ብሎአል ። ኢሳ 53:12 ኢሳያስ ገና ወደ ፊት የሚፈፀመውን እንደተፈፀመ አድርጎ ሲናገር ጳውሎስ ደግሞ የተፈፀመውን ገና ወደፊት እንደሚፈፀም አርጎ ተናገረ። ያውም በቃላት ሳይሆን እራሱን አሳልፎ በመስጠት አንዴ ለዘላለም የተፈፀመ ስለሆነ ማለደ ብሎ ደመደመው "ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይሄን አንድ ጊዜ ፈፅሞ አድርጓልና " ዕብ7:27 ይህም በመስቀሉ ከራሱ ጋር ከባህርይ አባቱ ከአብ ጋር ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሱ ቤዛነት ፣ በሱ ካሳነት ለዘልዓለም መዳናችንን ለመግለፅ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት እሱ ከአብ አንሶ ስለኛ ምህረትና ይቅርታ የሚጠይቅ አማላጅ አይደለም

በሌላ መልኩ ደግሞ ከ1938 ዓ.ም የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለኛ #ይፈርዳል በማለት ነበር የተቀመጠው ። በ1980 የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለኛ #የሚማልደው ይላል ። የ1938 ፈረደ የሚለውን ኀላ ቀላል አማርኛ በማለት ማለደ ተብሎ ሆን ተብሎ የተቀየረ ነው

እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8:34 ያሰፈረውን ፍሬ ሃሳብ ለመረዳት እስቲ ኢየሱስ አማላጅ ነው ለሚሉት ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ የሚያጸድቅ መኮነን አይችልም ? የሚኮንንስ ለማጽደቅ ምን ይሳነዋል ? በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጥስ የሚችል ማነው ? ክርስቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ እኛን የሚያድንበት ስልጣን አጥቶ ነው ስለኛ የሚማልደው ? ክርስቶስ ሁሉን የሚችል ኤልሻዳይ ነው ። ለሰውም እንደየስራው መክፈል የሚቻለው ፤ የሁሉ ዋጋ በእጁ ያለ የሚተካከለው የሌለ ባለ ጸጋ እውነተኛ ፈራጅ ዳኛም ነው ። እስቲ በመጽሐፍ ጥቅስ እናስደግፈው "እነሆ በቶሎ እመጣለው ለእያንዳንዱም እንደ ስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ " ራዕ 22:12 ሌላ እንጨምር "እነሆ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደሞዙም በፊቱ ነው "ኢሳ 40:10 ክርስቶስ ፈራጅ ከሆነ ታዲያ የሚለምን የሚያማልድ ማነው ? ከተባለ ከተለማኙ ጋር በቅርብ የሚተዋወቅ እውነቱን ለማስረዳት ይቅርታን ሊያሰጥ የታመነ ከተማላጁም ባለሟልነትን ያገኘ ነው ። ይሄንንም ስራ የሚሰሩት ከእግዚአብሔር በጸጋ የከበሩ ቅዱሳን ናቸው
https://t.me/meazasenay
554 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 12:28:41 # ክርስትና_ስም_ለምን_አስፈለገ ?
❖የክርስትና ስም ለምን ያስፈልጋል?❖
ጥቂት የማንባል ሰዎች ከነ መሰየሙም የክርስትና ስማችንንም የማናስታውስ ልንኖር እንችላለን፡፡ የክርስትና ስም አንድ የሚጠመቅ ሰው በሚያጠምቀው ካህን የሚሰጠው ወይም የሚጸድቅለት ስያሜ ነው፡፡ ይህንን ስም ቤ/ክ ዝም ብላ ለህጻናቱ የምትለጥፍ የሚመስላቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ በጥምቀት ግዜ ቤ/ክን ልጆቿን ስትቀበል እንዲሁ አይደለም ተገቢ ስም አውጥታ ከመንፈስ ቅዱስ በጥምቀት ዳግመኛ ወልዳ ቅበዐ ሜሮን ቀብታ የሚንከባከብ የክርስትና አባት እናት ሰይማ በመስቀሉ ቃል አስገብታ ቅዱስ ስጋና ደሙን መግባ ነው፡፡ የክርስትና ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ክርስቲያናዊ ትውፊት አለው፡፡ ብዙ ነብያት እና ቅዱሳን ካላቸው መጠሪያ ሰም በተጨማሪ እራሱ አምላካችን አዳዲስ ስም ሲያወጣላቸው እናያለን ለምሳሌ፡-
አብራምን ☞ አብርሃም
ያይቆብን ☞ እስራኤል
ስምዖንንን ☞ ጴጥሮስ
ሳኦልን ☞ ጳውሎስ እያለ ሲጠራቸው ለምን በአዲስ ስም መጥራት እንደፈለገ አንዳች ነገር ልንገነዘብ ይገባል፡፡
✞ # ዓላማውስ ምንድን ነው?
1. #ቋሚ የቅዱሳን መታሰቢያ እንዲሆን፡- በት.ኢሳ 56:5 አምላክ ለቅዱሳን የማይጠፋ ስም እና የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሰጣቸው እናነባለን፡፡ስለዚህ በተለያዩ ቅዱሳን ላይ የነበረውን ፀጋ እና በረከት ለመካፈልና እንዲሁም እንደነሱ የበረታን እንድንሆን በስማቸው እንሰየማለን የጌታችንንም ስሙን ዘርፍ በማድረግ እንዲሁ እንጠቀምበታለን፡፡
2. #ለተጠማቂውም በረከት እንዲሆንለት፡-
በምሳ 10:6 የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ይላል፡፡ ስለዚህ በስማቸው በመሰየም ከላይ እንደገለጽነው መታሰቢያቸውን እና በረከታቸውን ለመካፈል ሲረዳን ይህን ጸጋ ለማግኘት በቅዱሳን ስም በመሰየም የክርስትና ስም ይወጣልናል፡፡
3. #መጠሪያ ስም ነው፡-
በቀድሞው ስርአት የክርስትና ስም ለሁልጊዜውም መጠሪያ ነበር፡፡ ከግራኝ መሐመድ መነሳት አስቀድሞ የነበሩ ምዕመናን በክርስትና ስማቸው ነበር የሚጠሩት፡፡ነገር ግን መከራው ሲበዛባቸው ከርስታቸው ላለመሰደድ ሲሉ ተለዋጭ ስም በማውጣት መጠቀም ጀመሩ ከዛን ግዜ ጀምሮ ይህ ነገር እየተስፋፋ መጥቶ ከነ ጭራሹ ለመለወጥ በቃ፡፡
☞ #የማይገባ የክርስትና ስም
በአምላክ ስም በቀጥታ መጠራት አይገባም ለምሳሌ፡- አማኑኤል፣ኤልሻዳይ፣ኢየሱስ እነዚህ ስሞች ለሠው ልጆች መጠናችን ስላልሆኑ መጠቀም የለብንም፡፡ በዚህ ምትክ ገብረ አምላክ፣ሣህለ ሥላሴ፣ፍቅርተ ክርስቶስ ፣ዘአማኑኤል በማለት መሰየም ይቻላል፡፡
☞በቅዱሳንም ስም በቀጥታም ሆነ ዘርፍ እየተደረለት መሰየም ይቻላል፡፡
ለምሳሌ፡- ዘማርያም፣ዘሚካኤል፣አጸደ ማርያም፣ ተክለ ሐይማኖት ወዘተ...
ስለዚህ ስርአቱን በመጠቀም ከሚገኘው በረከት ተሳታፊዎች እንድንሆን አምላክ ይርዳን፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን፫
https://t.me/meazasenay
474 views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 08:39:11 ነገረ ማርያም ክፍል 7
* የሱፍ አበባ *
ጠቢቡ ሰለሞን በማህ 2:1 ላይ የቅድስት ድንግል ማርያምን ንፅህና በሱፍ አበባ መስሎ ሲያስተምር ( እኔ የዱር ፅጌሬዳ ፣ የቆላም የሱፍ አበባ ነኝ ፣ በእሾህ መሀከል እንዳለ የሱፍ አበባ እንዲሁ ወዳጄ በቆነዣዥት መኻከል ነሽ ) .በማለት የተናገረውን ምሳሌያዊ ኃይለ ቃል ሊቁ በድርሰቱ ላይ ፦ በእሾህ መሀከል እንዳለ የሱፍ አበባ አምላክን እመቤታችን ሆይ አንቺም እንደ እሷ ነሽ በማለት ተርጉሟታል። ይኸውም ይቺ የሱፍ አበባ እሾህ ዙሪያዋም ከቧት ሳለ በሾህ መሀከል እንደምታብብ እንደምታፈራ ቅድስት ድንግል ማርያምም ኀጢአት እንደ እሾህ በከበባቸው በአይሁድ መሀከል ሳለች ብቻዋን ከማሰብ ፣ ከመናገር እና ከመስራት ከሀጢአት ተጠብቃ በሃይማኖት በምግባር በንፅህና በቅድስና በድንግልና ፀንታ የህይወት ፍሬ ክርስቶስን አብባ አፍርታ ተገኝታለችና ነው ።ኢትዮጵያዊዉ የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ይሄንን በአርጋኖን መፅሀፋ ሲተረጉመው ( በሱፍ ዕንጨት እመስልሻለው ፤ የሱፍ አበባ በእሾህ የተከበበ ነውና ፤አንቺም ከዳዊት ግንድ (ባህርይ ) የተገኘች የንፅህት አበባ ቅንጣት ሆነሽ ሳለ ፤ በጉስቅልናቸው የሚመኩ አንገታቸውን የሚያደነድኑ በዐይኖቻቸው የሚጠቃቀሱ በእግሮቻቸው የሚያሸበሽቡ የልብሶቻቸውን ዘርፎች የሚጎትቱ የሚዘፍኑትን የቆነዣዥት አለቆች የሚሆኑ የፅዮንን ልጆች እግዚአብሔር ያዋርዳቸዋል ያጎሳቁላቸዋል ብሎ ኢሳያስ ትንቢት እንደተናገረባቸው አንቺም አንገተ ደንዳኖች በሚሆኑ በዕብራዊያን ቆነዣዥት መካከል እንደተቀመጥሽ በማለት ግዙፋነ ክሳድ በሆኑ ኀጢአት እንደ እሾህ በከበባቸው በአይሁድ ልጆች መሀከል ሳለች ርሷ ብቻ በንፅህና በቅድስና ፀንታ የመገኘቷን ሚስጥር ተናግሮታል ። ሊቁ አባ ሕርያቆስም ከዚህ በመነሳት በቅዳሴው ላይ ( ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፋ እንደ ዕብራዊያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም ፤ በንፅህና በቅድስና በቤተመቅደስ ኖርሽ እንጂ ) በማለት ኃጢአትን በመስራት ይኖሩ ከነበሩ ዕብራዊያት ሴቶች ልጆች ተለይታ በቤተ መቅደስ ማደጓን አስተምሯል ። ሊቁ አባ ፅጌ ድንግልም ( በእሾኾች አይሁድ መኻከል የደጋ ያይደለ የቆላ የሱፍ አበባን ያበብሽና ልማድሽ መራራት የኾነ የመዳን ምልክት ማርያም ፤ ብርቱ ከኾነ ከጭንቅ የቅጣት ፍርድ ታማኝሽን አድኚኝ ፣ በአንቺ መታመኔ ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ) በማለት በሱፍ አበባ መመሰሏን ተነግሯል ።
https://t.me/meazasenay
499 views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ