Get Mystery Box with random crypto!

እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተ ነህ ለምን አለ ? ዮሐ 17:3 ሙስሊሞ እና የይሆዋ ምስክሮ | መዓዛ ሠናይ

እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተ ነህ ለምን አለ ? ዮሐ 17:3

ሙስሊሞ እና የይሆዋ ምስክሮች የተባሉ ወገኖቻችን ክርስቶስ አምላክ አይደለም ብለው ከሚያቀርቡት ጥቅስ አንዱ ይሄ ነው ።  ይህን ምዕራፍ ስንመለከት ጌታችን በዚህች ምድር ላይ በስጋው ወራት ሊሰራ ያቀደውን ጨርሶ ወደ ክብሩ ሊሄድ ሊሰቀል ሲል የተናገረው ቃል ነው ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እርሱ ከአብ ጋር እኩል በመሆኑም "እኛ አንድ እንደሆንን "በማለት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ስልጣን እኩል ጌትነት እንዳለው እንረዳለን ። ያላመኑት ግን "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3 የሚለውን በመጥቀስ ጌታ አምላክ እንዳልሆነ አብ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አሕዛብ ይናገራሉ። እስኪ በሌላ ስፍራ ላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እንመልከት ፦

"ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚቻለው ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኀኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ግርማ ኃይልም ስልጣንም ይሁን አሜን " ይላል ይሁዳ 1:25 በዚህ አገላለፅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አምላክ እንደሆነ ተገልፇል ። በሌላም ስፍራ ፦ "ስለዚህ እላችዋለው ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም በሰው ልጅ ላይ ቃል  የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል በመንፈስቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም " ማቴ 12:31 ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ይላል፦

"ብቻህን አምላክ የሆንህ አንተ የላከውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3  ታዲያ ሶስቱም ብቸኛ ከተባሉ የቱን እንምረጥ ? ዳሩ ግን ይህ ለምን እንደተባለ ለኛ ለክርስቲያኖች ግልጥ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እንዳለው ፦ "ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳን የተከደነባቸው ለሚጠፋ ነው " 2ኛ ቆሮ 4:3 ታዲያ ጌታችን ይህን ስለምን ተናገረው ቢሉ የዘላለም ሕይወት የሚገኝባት ሃይማኖት ይህች ናት አንተ የባህርይ አምላክ እንደሆንክ እኔም የባህርይ አምላክ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ቢያውቁ እውነተኛ ሃይማኖች ይህቺ ናት ማለቱ ነው ።  ጌታ በአንዳንድ ቦታ ላይ አምላክ ወይም እግዚአብሔር ብሎ እንደ ሰው መጸለዩ በእውነት የሰውን ባህርይ ባህሪው ማድረጉን ሊያስረዳን ፈልጎ ነው እንጂ በባሕሪው ከአብ የሚያንስ ሆኖ አይደለም

እንደ ሰው አምላኬ ብሎ ባይፀልይ ኖሮ በእርሱ ዘንድ ሰውነት የለም ወይም መለኮት ተስብእትን(ሰውነትን) ውጦ አጥፍቶታል በተባለም ነበር ። ይህ የጌታችን አነጋገር በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ #ለአጽድቆተ\_ትስብእት ተብሎ ይተረጎማል፡ ስለዚህ እነርሱ እንደሚሉት ሳይሆን ጌታችን ስለዚህ ተናገረው እንጂ አምላክ ስላልሆነ አይደለም ። አምላክ ስለመሆኑማ ዮሐንሰ እንዲህ በማለት ገልጾታል ። "እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው " 1ዮሐ5:20 "የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ ዋህድ ነፍስንና ስጋን ነስቶ ሰው ሆነ ባልንም ጊዜ ስለዚህም ነገር ቢሆን እነዚያ እንደሚያምኑ መቀላቀል የለበትም የቃል ባህርይ የስጋን ባህርይ ወደ መሆን አልተለወጠም ሁለት ባህርይ ያለመለወጥ ባለመቀላቀል ጸንተው ይኖራሉ እንጂ " ሃይማኖተ አበው ዘ ኤራቅሊስ

"የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ ሲሆን ሰው ይባላል ፤ ዳግመኛም የአዳም ልጅ ይባላል ሰማያዊ ሲሆን በፈቃዱ ምድራዊ ሆነ ። በመለኮቱ መከራን መቀበል ሳይኖርበት ሰው በመሆኑ መከራ ተቀበለ ፈጽሞ አንዱ በአንዱ ያደረ ነው አይባልምና ለአንዱ ለእግዚአብሔር ልጅ ሁለት አካል ሁለት ገጽ ሁለት ባሕርይ የለውም " ሃይማኖተ አበው ዘ አትናቴዮስ ስለዚህ ክርስቶስ ፍፁም ሰው የሆነ ፍፁም አምላክ ነው አምላኬ ሲል ብትሰሙት በተዋሀደው ስጋ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል ነው
https://t.me/meazasenay