Get Mystery Box with random crypto!

መዓዛ ሠናይ

የቴሌግራም ቻናል አርማ meazasenay — መዓዛ ሠናይ
የቴሌግራም ቻናል አርማ meazasenay — መዓዛ ሠናይ
የሰርጥ አድራሻ: @meazasenay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.95K
የሰርጥ መግለጫ

☞ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እንወቅ
☞እንረዳ
☞እንማማር
♥♥♥♥♥♥
ለበለጠ መረጃ @Tadi16 ላይ ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን፡፡

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-02 07:44:42 * ነገረ ማርያም ( ክፍል 6)
* የወይን ሐረግ *
የሕይወት መብል የሕይወት መጠጥ ጌታችንን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና ወልዳ ያስገኘችልን እመቤታችን የእስራኤል ልጆች በተሸከሟት የወይን ሐረግ ትመሰላለች ። ይኸውም እግዚአብሔር ለሙሴ የሚያወርሳቸውን ምድረ ርስትን ይሰልሉ ዘንድ ከ12 ነገደ እስራኤል አውጣጥቶ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ከፍሬዋም እንዲያመጡ አዝዞ ሰደዳቸው ። ከእነርሱ መኻከል ኢያሱና ካሌብ ይገኛሉ ። እነሱም ምድሪቱን በመላ ሲሰልሉ ሰንብተው ሲመለሱ ከወይኑ ሐረግ ዘለላውን ከስንዴ ዛላውን ቆርጠው ፣ በባጢ (በቀፎ) አድርገው ከሮማን ከበለስ ጨምረው ስድስቱ በፊት ስድስቱ በኀላ ሁነው የሳንሳ ተሸክመው መጡ ፤ የእስራኤል ልጆች የወይን ሀረግ ስለቆረጡበት ያን ቦታ የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠርተውታል ። ይኸውም ምሳሌ ነው ። ሐረግ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ፍሬ የሕይወት ፍሬ የክርስቶስ አምሳል ነው ። በፊት ያሉት የነብያት ምሳሌ ናቸው ። ይኽም በፊት ያሉት የወይን ሐረጉን ተሸክመዋል ኾኖም ግን የተሸከሙትን እንዳያዩ ነብያትም የሕይወት ፍሬ አምላክ ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት ቢናገሩም ወርዶ ተወልዶ አላዩም ። በሃላ ያሉት የሀዋሪያት ምሳሌ ናቸው ። ይኸውም የተሸከሙትን የወይን ሐረግ ያዩታል ። ሀዋሪያትም ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ አይተውታልና ።ጌታ በወንጌል ( የእናንተ ግን አይኖቻቹ ስለሚያዩ ዦሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው፡ እውነት እላችኀለው ብዙዎችነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም ፡ የምትሰሙትን ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም ) ያለው ለዚ ነው ።በመሆኑም ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰጠን የርኁባን ምግብ የተጠሙት መጠጥ የሕይወት ወይን ክርስቶስን ያገኘንባት አማናዊት ሐረግ እሷ ብቻ ናትና ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ( ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን እውነተኛ የፅድቅ መብልን እና የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና ።ያላት አባ ጊዮርጊስም ( የእስራኤል ልጆች ፍሬን ከውስጡ ቆርጠው በመሎጊያ (በባጢ ቀፎ ) የተሸከሙላት የወይን ሐረግ አንቺ ነሽ ፡ ይኸውም የድንግልናሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ያላት ።
https://t.me/meazasenay
493 views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 12:10:00
በማርያም ይሄን መልክት አዳምጡት

https://youtube.com/channel/UCxkJ20_IgJMj1yYZzL0hEVg

ሼር አድርጉት
582 views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ