Get Mystery Box with random crypto!

የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐

የቴሌግራም ቻናል አርማ masreshameron — የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐
የቴሌግራም ቻናል አርማ masreshameron — የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐
የሰርጥ አድራሻ: @masreshameron
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.71K
የሰርጥ መግለጫ

የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን
SYNAGOGUE OF GOD CHURCH
⛪⭐ የሲኤምሲ"መሪ" አጥቢያ ቤተክርስቲያን ⭐⛪
🌎 WORLD WIDE FAMILY GROUP 🌎
“እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።”
— ኤፌሶን 5፥27

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-09 10:05:46 የሚያዚያ 01/08/2015ዓ.ም እሁድ አምልኮ ጊዜ።
137 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 09:35:30 #በወሩ_የመጀመሪያ_ቀን_ልባርካችሁ።
በጌታ በኢየሱስ ስም ልባርካችሁ፤ እናንተም ሌሎችንም ባርኩ፤ ሚያዚያ 01/08/2015ዓ.ም።

አሜን ባላችሁበት አፍ፥ ባመናችሁበት እምነት ይህ የበረከት ቃል ይፈፀምባችሁ።

እመርቃችኋለሁ እንድትበዙ፣ እንድትኖሩ፣ ፍሬአችሁም በእግዚአብሔር ፊት እንዲኖር እመርቃችኋለሁ፣ እንዲሳካላችሁም እመርቃችኋለሁ።
እግዚአብሔር ፈቃዱን በመፈጸም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይባርካችሁ፣ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ አድብቶ ሊይዝ ከሚፈልግ ስውር ኃጢአት እግዚአብሔር ያድናችሁ በጌታ በኢየሱስ ስም፣ እግርን በመያዝ ወደሚፈለግ እንዳትሔዱ ሊከለክሉ በሚፈልጉ መካከል ባለመያዝ ቀጥሉ፣ ባለመቆም ቀጥሉ፣ በጌታ በኢየሱስ ስም ድል ንሱ፣ አሸንፉ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፣ ክፉዎችን ገንጥሎ ይስጣችሁ፣ ዝጎችን ደርምሶ ያሳልፋችሁ፣ አጥሮችን፤ ቅጥሮችን ያዘልላችሁ፣ እግዚአብሔር ወዳየላችሁ ሰፊ ሜዳ ያውጣችሁ።

እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተልዕኮ ላይ ትጋት ይጨምርላችሁ፣ እግዚአብሔር በከፈተላችሁ በር ላይ ትጋትን ይጨምርላችሁ፣ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ትዳር ላይ፤ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ኑሮ ላይ፤ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ስራ ላይ፤ እግዚአብሔር ነገር ላይ፤ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጸጋ እንድትፈጽሙት በሰጣችሁ አገልግሎት ላይ ትጋትን እንዲጨምርላችሁ እፀልያለሁ። አሉባልታ የማታዩ፣ ፈተና የማያስቆማችሁ፣ ወደቀኝም ወደግራም የማትሉ፣ እስከጫፍ የምትጋደሉ እንድትሆኑ፤ ውስጣችሁ ሳይበርድ እስከጫፍ ስትቀጥሉ ራሳችሁን እንድታገኙ፣ በተግዳሮት መሐል፣ በፈተናዎች መሐል፣ በማይመቹ ሁኔታዎችና ጊዜዎች መካከል በጊዜውም አለጊዜውም እስከጫፍ የምትሔዱ፤ ፈጽሞ የምትጋደሉ እንድትሆኑ በጌታ በኢየሱስ ስም እንደዚህ እፀልያለዉ። ባለመቆም ሒዱ፣ ባለመብረድ ሒዱ፣ እስከጫፍ ትጉ፣ በጌታ በኢየሱስ ስም በዚህ ትጋት ይወቋችሁ፣ ባለመድከም ይወቋችሁ፣ ባለመሰልቸት ይወቋችሁ፣ በመጋደል ይወቋችሁ፣ እስከጫፍ በመሔድ ይወቋችሁ። በኢየሱስ ስም ድካምና ምክንያት የማታመጡ፣ እስከጫፍ የምትሰሩ፣ እስከጫፍ የማታቋርጡ፣ የምትጋደሉ፣ ለተሰጣችሁ ተልዕኮ የምትጨክኑ እንድትሆኑ፣ እግዚአብሔር ትጋትን ይስጣችሁ።

እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ትጋት ፈፃሚ ያድርጋችሁ፣ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እድሜና በሰጣችሁ በየትኛውም እናንተን በሚፈልግ እንቅስቃሴ ዙሪያ የምትፈጽሙበትን ትጋት ይስጣችሁ፣ ለቤተክርስቲያን ትጋትን ይስጣችሁ፣ የማትበርዱ፣ የማትቀዘቅዙና ዳር የምትደርሱ ያድርጋችሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የእግዚአብሔር ኘሮግራም በህይወታችሁ እንዲከናወን እመርቃችኋለሁ። የእግዚአብሔር ደግነት በእናንተ እንዲሆን፣ በእናንተ እንዲፈራ፣ በእናንተ የሚጠበቅ እንዲገኝባችሁ እመርቃችኋለሁ። እግዚአብሔር አሁንም ጎዳናችሁን ያቅና፤ እናንተ የእናንተ አይደላችሁምና እናንተ የእሱ ናችሁና የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ እንደሚል በጌታ በኢየሱስ ስም ከቆያችሁ፤ ከከረማችሁበት አምላክ ምናልባት እንድታድሩ ብቻ ከሰጣችሁ ቦታ፣ እንድትውሉ ካልሰጣችሁ ቦታ ዘግይታችሁ እንኳን ቢሆን በኢየሱስ ስም ወዳለበት ያውጣችሁ።

ከቆያችሁበት ያውጣችሁ፣ ከኖራችሁበት ያውጣችሁ፣ ካደራችሁበት ያውጣችሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚቀጥለውን ለማየት ከነበራችሁበት ያውጣችሁ፣ ከአስተሳሰቦቻችሁ ያውጣችሁ። ልክ ነው ብላችሁ እስከመጨረሻ ከቆማችሁበት ነገር አሁንም ወደሚበልጠውና እርሱ ወዳለበት ልክ ቃሉ እንዲናገር እነርሱ ሁሉ ስለእኔ ይናገራሉና እናንተ ግን ህይወት እንዲሆንላችሁ ወደእኔ ልትመጡ አትወዱምን እንደሚል እየጠቀሱ እንደቀሩ የመጽሐፍትን ቃል እየተናገሩ ከእርሱ እንደቀሩ እንደዛ እንዳትሆኑ፣ እየዘመረ የቀረ፣ እየሰበከ የቀረ፣ በመጽሐፉ ምክንያት celebrate እያደረገ የቀረ ሰው እንዳትሆኑ ልክ ቃሉ እንደሚናገር በጌታ በኢየሱስ ስም ከዛ መውጣት ይሁንላችሁ። እግዚአብሔር ከማይፈለግና ከቆያችሁባቸው፣ ለጊዜው ከሰጣችሁ ቦታ ደግሞ እንደዚያ ቦታ ላይ እንዳትኖሩ እግዚአብሔር መውጣትን ይሰጣችሁ።

በፊታችሁ ይሄዳልና መከተልን ይስጣችሁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድምፁን ያሰማልና ድምፁን መስማት፣ ድምፁን መለየትና የህይወታችሁን መከናወን በምሪት ውስጥ ባለበትና እንዳደረገላችሁ ሁሉ ያለእርሱ የሆነን እንዳታፈሩ፣ ያለእርሱ የሆነ ነገር ስኬት ውስጥ እንዳትገቡና በተሳሳተ መንገድ successful ሆኛለሁ ብላችሁ በተሳሳተ ቦታ ተረጋግታችሁ፣ በተሳሳተ ቦታ ደግሞ እንዳትቆሙ በጌታ በኢየሱስ ስም ስኬታችሁን ባለበት ያድርግላችሁ። እረፍታችሁን ባለበት ያድርግላችሁ፣ ኑሯችሁን ባለበት ያድርግላችሁ። የህይወት በር፣ የአገልግሎት በር፣ የስራ በሮችን በኢየሱስ ስም ይክፈትላችሁ፣ በእርሱ ውጡና ግቡ፣ በእርሱ መሰማሪያን አግኙ። በጌታ በኢየሱስ ስም በዚህ መርቄአችኋለሁ፤ መባረካችሁ ባለበት ይሁንላችሁ፣ ስኬታችሁ እርሱ ባለበት ይሁንላችሁ መውጣት መግባት ይሁንላችሁ። በጌታ በኢየሱስ ስም ይህንን መርቄአችኋለሁ በዚህ ማለዳ፤ የሩቅ ጊዜአችሁን መርቄዋለሁ፣ ሳምንታችሁን መርቄዋለሁ፣ አመታቶቻችሁን መርቄአለሁ፣ እድሜአችሁን፡ ዘመናችሁን በዚህ መርቄአለሁ።

ባለበት ያኑራችሁ፣ በድምፁ ያስተዳድራችሁ፣ በጌታ በኢየሱስ ስም በዚህ መከናወንን አግኙ፣ በዚህ ሙላትን አግኙ፣ በዚህ ደስታን አግኙ፣ በዚህ ማፍራትን አግኙ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በዚህ መርቄአችኋለሁ፤ አሜን። ወዳላችሁ ሂዱ፣ ወዳሳለማችሁ ሂዱ፣ ጨርሱ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተሸናፊ ሳይሆን አሸናፊ፤ አቅም ያጣ ሳይሆን ጉልበታም በመሆን ጨርሱ፣ እግዚአብሔር ጎዳናችሁን ያቅና። እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ዘመናችሁ የጣፈጠ ይሁን፣ እግዚአብሔር እናንተን፤ የምትኖሩባትን ምድር፣ ከተማ፣ የምትሰሩባቸውን ትምህርት ቤቶችና መስሪያ ቤቶች፣ የምትውሉባቸውን ቤቶች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ይባርክ

መልካም ሰንበት። ሚያዚያ 01/08/2015ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።
145 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 11:21:29
191 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 08:36:32
ዘፍጥረት 17፥1-2 (አመት)
"አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር  (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤
ነቀፋም አይኑርብህ፤ በእኔና በአንተ መካከል የተመሠረተውን ኪዳን አጸናለሁ፤ ዘርህንም እጅግ አበዛለሁ።”

እግዚአብሔር ለገባው ቃልም ሆነ ለሚጠይቀው ነገር ሁሉ ኤልሻዳይነቱ መተማመኛ ነው። አቅሙ ሁልጊዜ ተስፋውን ያጅባል።

Genesis 17:1-2
When Abram was ninety-nine years old, the Lord appeared to him and said, “I am God Almighty; walk before me faithfully and be blameless. 2 Then I will make my covenant between me and you and will greatly increase your numbers.”
240 views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 20:29:32
239 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 20:29:09 #በቀጣይ_እግዚአብሔር_የሚለዉ_ምንድነዉ
የፊታችን እሁድ በፍፁም እንዳትቀሩ እንደተባረካችሁ ቆዩ።
አሁን ስላለዉ ሁኔታ ስለኢትዮጵያና ስለመላዉ አለም እግዚአብሔር የሚናገረዉን እንሰማለን፤ ቀጣዩስ ሁኔታ ስለኢትዮጵያና ስለመላዉ አለም እግዚአብሔር ምን ይላል፤ በመጨረሻም ከዉጭ ይልቅ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ባሉ የእፉኝት ልጆች ምክንያት ስደት ይነሳል በሚል የምንማርና የእግዚአብሔርን የትንቢት ድምፅ የምንሰማ ይሆናል።

#ማደግ
የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በዕድገታችሁ ልክ ይገለጣል። የጌታን መልክ በመወለድ ትካፈሉታላችሁ በዕድገት ትገልጡታላችሁ። በጌታ ያልተወለደ ዘሩ እንደማይገኝበት ሁሉ እንዲሁ ያላደረገ ደግሞ መልኩ አይገለጥበትም። እግዚአብሔር በመወለዳችሁ ደስ ይለዋል። በማደጋችሁ ግን ይከብራል። መፅሐፍ ቅዱስ በሉቃስ ወንጌል 15. ላይ እንደሚነገረን የጠፋ ሰዉ ሲገኝ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል ይለናል። በዮሐንስ 15. መሠረት ግን እግዚአብሔር ይከብራል ብሎ ከማደግና ብዙ ፍሬ ከማፍራት ጋር ያይዘዋል።

“ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።”
— ዮሐንስ 15፥8

ስለዚህ መወለዳችሁ ለእግዚአብሔር ደስታ እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም። እግዚአብሔር ከእናንተ ህይወት ክብር የሚያገኘዉ ስትወለዱ ሳይሆን ስታድጉ ነዉ። የክርስትና መለኪያው ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን የልጁ መልክ ነዉ። በእግዚአብሔር ፊት የምትለካዉ ባላችሁ ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን ምን ያህል የልጁን መልክ ገልጣችሁታል በሚለዉ ነዉ። ቅባት የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጣል ዕደገት የልጁን መልክ ይገልጣል። ቅባት በእግዚአብሔር የመቀባት ውጤት ነዉ መልክ ግን ክርስቶስን የመኖር ውጤት ነዉ። የትኛዉም ፀጋና ቅባት ክርስቶስን ለመምሰላችሁ ዋስትና ሊሆናችሁ አይችልም። የልጁን መልክ የሚያመጣዉ የእግዚአብሔርን ህይወት በመኖር የመንፈስ ፍሬን በማፍራት ነዉ። ይህ ደግሞ ራስን እግዚአብሔርን መምሰል በማሰለመድ የሚገኝ ውጤት ነዉ።

“ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7

#ማሳሰቢያ:_ ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተር መያዛችሁን አትዘንጉ።

የቤተክርስቲያኒቱ አድራሻ:- ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጋር ከመድረሳችሁ በፊት ያለዉ ድልድይ ጋር ያለዉ ሲሆን በድልድዩ ወደ ፊጋ በሚወስደዉ መንገድ በስተቀኝ አራተኛዉ መታጠፊያ።

መልካም ለሊት። መጋቢት 28/07/2015 ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።
244 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 10:11:35
#የመጨረሻ_ልጠፋ_ለአዳማ።
ህይወት ድግግሞሽ ለሆነባቸዉና የመጨረሻዉ ዘመን የክብር ሰራዊት ለሚሆኑ ሁሉ።

እግዚአብሔር ለመስማት የሚያስፈልገዉ የተከፈተ ጆሮ ብቻ ሳይሆን የሚታዘዝም ልብ ነዉ። ምክንያቱም እግዚአብሔርን መስማታችሁ የሚረጋገጠዉ በመስማታችሁ ብቻ ሳይሆን የሰማችሁትን በማድረጋችሁም ነዉ።

የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 30/07/2015ዓ.ም አዳማ በሳምንት አንድ ቀን የሚኖረን መሠረታዊ ህይወት ለዋጭ ትምህርት ምዝገባዉ ይጠናቀቃል፥ ያልተመዘገባችሁ ባሉን አራት ቀናት ሙሉ ስማችሁንና ስልካችሁን በዉስጥ መስመር ለመመዝገብ እንድትፅፉልኝ ጥሪዬን አደርሳለሁ። የተመዘገባችሁ ሁሉ የፕሮግራሙ ቀንና ቦታ ተደዉሎ ይነገራችኃል።

#ለመመዝገብ:- ሙሉ ስማችሁን እና ስልካችሁን በዉስጥ መስመር ፃፉልኝ፤ ትምህርቱ የሚጀመርበት ቀንና ቦታ ተደዉሎ ይነገራችኃል።

#ማሳሰቢያ:_ ወደ ትምህርት ቦታ ስትመጡ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተር መያዝ ግዴታ ይሆናል።

መልካም ቀን። መጋቢት 27/07/2015ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።
308 views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 12:51:40 #የመጨረሻ_ልጠፋ_ለአዳማ።
ህይወት ድግግሞሽ ለሆነባቸዉና የመጨረሻዉ ዘመን የክብር ሰራዊት ለሚሆኑ ሁሉ።

እግዚአብሔር ለመስማት የሚያስፈልገዉ የተከፈተ ጆሮ ብቻ ሳይሆን የሚታዘዝም ልብ ነዉ። ምክንያቱም እግዚአብሔርን መስማታችሁ የሚረጋገጠዉ በመስማታችሁ ብቻ ሳይሆን የሰማችሁትን በማድረጋችሁም ነዉ።

የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 30/07/2015ዓ.ም አዳማ በሳምንት አንድ ቀን የሚኖረን መሠረታዊ ህይወት ለዋጭ ትምህርት ምዝገባዉ ይጠናቀቃል፥ ያልተመዘገባችሁ ባሉን አራት ቀናት ሙሉ ስማችሁንና ስልካችሁን በዉስጥ መስመር ለመመዝገብ እንድትፅፉልኝ ጥሪዬን አደርሳለሁ። የተመዘገባችሁ ሁሉ የፕሮግራሙ ቀንና ቦታ ተደዉሎ ይነገራችኃል።

#ለመመዝገብ:- ሙሉ ስማችሁን እና ስልካችሁን በዉስጥ መስመር ፃፉልኝ፤ ትምህርቱ የሚጀመርበት ቀንና ቦታ ተደዉሎ ይነገራችኃል።

#ማሳሰቢያ:_ ወደ ትምህርት ቦታ ስትመጡ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተር መያዝ ግዴታ ይሆናል።

መልካም ቀን። መጋቢት 26/07/2015ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
  — 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።
305 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 18:40:37
አንቺ የተወደድሽ የተባረክሽ ነህ አልምዬ ስለመጣሽ ስላገለገልሽን ተባረኪ።
361 views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 18:40:37 የመጋቢት 24/0/2015ዓ.ም እሁድ አምልኮ ጊዜ
340 views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ