2022-05-28 08:38:53
የመጀመሪያ ኮርስ -ነገረ ክርስትና
የቀጠለ........
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን
#በቅድመ_ግቢ_ህይወት፦ ተማሪዎች ወደ ኮሌጅ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት የተለያየ ህይወት እንደሚኖራቸው አያጠራጥርም።
ለአብነት ያህልም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሲያገለግሉና ሲሳተፉ የነበሩ በካሀናት አሰልጣኝነት ስልጠና የወሰዱ፣ በሰርክ ጉባኤ ሲማሩ የነበሩ ነገር ግን የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ያልሆኑ ሌሎች ደግሞ ለበአለ ጥምቀት፣ ለቀብር ከመሆድአቸው በቀር ወደ ቤተክርስቲያን ቀርበው ማያውቁ አሉ። ሀይማኖታቸውን ቢጠይቃቸውም ያማያብራሩ አሉ።
#በብሔር፦ ሀገራችን የብዙ ብዙ ብሔረሰቦች መኖሪያ መሆኗ ገቢዎችንም በዚህ ስብጥር እንዲያሸበርቁ አድርጓቸዋል። ተማሪዎች በአንድ ግቢ ውስጥ ሁነው ከነሱ ውጭ ስለሆኑ ብሔረሰቦች የማወቅ እድል ብቻ ሳይሆን የመተዋወቅና በአንድነት በፍቅር የመኖር እድል ማግኘታቸው የኑሮአቸውን ውበት ያደምቀዋል። (ዮሐ 15፥1-5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ)
#በባህል፦ ከላይ የተለያየ ብሔር እንዳሉ ተመልክተናል እያንዳንዱ ብሔረሰብ ደግሞ የራሱ የሆነ ነገር ሊኖረው እንደሚችል የታመነ ነው። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት በመሆኗ እና ባህሏ ከቅዱሳን መፅሐፍትና ከቅዱሳን ኑሮ የተቀዳ ቢሆንም ከአካባቢ አካባቢ፣ ከብሔረሰብ ብሔረሰብ የሚለያይ ነገር አይጠፋም።
ይሁን እንጂ አንድ ተማሪ ከብሔረሰቡ እና ከአካባቢው ያመጣውን ባህል ግቢ ውስጥ እንደፈጠረው ስናስብ እንሳሳታለን።
ይህ የባሀል ስብጥር ጎጅ የሚሆንበትን በሁለት መንገድ ከፍለን እናየዋለን፦
ሀ/ #የኔ_ባህል_ከሌላው_ይበልጣል ብለን መሰብ የሌላውን መናቅና መጥላት ስንጀምር
ለ/ #በባህላችን ታርቀን ለክርስትና ህይወት እንዳንታዘዝ ስናማፅ እና ከፅድቅ ህይወት ስንከለከል ነው።
ከእነዚህ ሁለት ወጥመዶች ካመለጥን የህብረተሰብና የባህል ስብጥር በአንድ የአትክልት ቦታ እንደሚጎበኙ አንድነት እንዳላቸው አበቦች የሚያስጌጠን፣ የሚያስውበን አምላካዊ ስጦታ መንፈሳዊ አንድነት ነው። (መክ 12፥1 የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ...)
#በጠባይ፦ ሰው በመልክ።፣ በቁመት፣ በገፅ እንደሚለያይ በጠባይም ይለያያል። ከባህሪው ስንል ከአራቱ ባህርያተ ስጋ እና ከሶስቱ ባህርያተ ነብስ ነው በእነዚህም እድሚያቸው የተለያየ ፀባይ ይኖራቸዋል። ይህ የፀባይ ስብጥር መኖሩ አይቀሬ ነው።
#በእውቀት፦ ይህ ደግሞ ሰው በቁመቱ እነደሚበላለጥ ሁሉ በእውቀቱ በሚያደርገው ጥረት እንዲሁም ሊያውቀው በሚፈልገው ት/ት ይለያያል። ከዚህም የተነሳ ለያንዳንዱ ትምህርትም የተለያየ የሆነ አስተሳሰብ ይፈጥርበታል። መምህሩ የትምህርት ጓደኞቹም እንዲሁ ይህ ስብጥርም ከፍላጎትና ከፀጋ ልዩነት መሆኑን ካልተገነዘብን መናናቅም መጣላትም ስለሚፈጥር በእውቀት በሚማሩት ትምህርት አይነት መሰባጠሩን ጥቅም በውል መረዳት እና መገንዘብ ያስፈልጋል።
#በገንዘብ_አቅም፦ አገራችን ውስጥ ያሉት ባለፀጎች ከሌሎች አገራት ባለፀጎች ጋር የሚወዳደሩ ሊሆኑ ይችላሉ።
ይሁን እንጅ በአገራችን እይታ ባለ ፀጎች አሉ፣ ድሆዎችም አሉ፣ መካከለኛ ኑዋሪዎችም አሉ። እኛ ተማሪዎችም የነዚህ ሰዎች ልጆች ነነ። በመሆኑም የተለያየ አኗኗር ለምደው የመጡ መሆናቸው የታወቀ ነው። ወላጆችም የቀደመ አኗኗራቸውን በመገንዘብ የሚያደርጉት ክትትል ይለያያል። የደብተርና የብዕር/የስክርቢቶ መግዣ የለለውና በግሉ መመገብ እሰከ ሚችል ድረስ አቅም ያላቸው ተማሪዎች አሉ። ይህንም ስብጥር ከተጠቀሙበት ልዩ ጥቅም አለው።
ሀ/ ከሌላው ጋር በፍቅር መኖር የጎደለውን በመሙላት የሚረዳዱበትና ከተዋወቁበት ጊዜ አንስቶ አንዱ ከሌላው እውነተኛ ወንድምነት የሚመሰርቱበት በመሆኑ ነው።
ለ/ ሰው እንደ ጎረቤቱ ሳይሆን እንደ ቤቱ መኖር እንደሚችል ትልቅ ልምድና ልበ ሙሉነት የሚያዳብርበት ጊዜ ነው። (በቃኝ ከማለት ጋር እግዚአብሔርን ማምለክ ታላቅ ክብር ነው)። ወደ አለም የመጣሁት ነገር የለም የምወስደውም ነገር የለም 1ኛ ጢሞ 6፥6-8
''ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ፊል 4፥11"
#በቦታ፦ ግቢ ውስጥ አዲሱ ስብጥራችን ከለመድነው በተለየ ሁኔታ የቦታ ስብጥር አለ።
በግቢ ውስጥ የቤተ መፅሐፍት፣ የኳስ ሜዳ ለሌሎችም የተለያየ ቦታዎች በህይወታችን ላይ ድርሻ አላቸው።
የቤተ መፅሐፍትን ፀጥታ የለመደና የኳስ ሜዳ የድጋፍ ጭሆትን የለመደ ሰው አንድ ቦታ ማውራት ይቸገራሉ። እንደ መዝናኛ ቦታ ደግሞ ዳማ፣ የጠረፔዛ ቴንስ፣ ፑል የሚያዘወትር ሰው አለ በሌሎችም ቦታዎች እንዲሁ ሌላው ደግሞ በእነዚህ የመሳሰሉ ጎጅ ቦታዎችና ሁኔታዎች መጠበቅ ይገባል። "ወንድሞቻችን ሆይ እውነትን ሁሉ፣ ቅንነትን ሁሉ፣ ፅድቅንም ሁሉ፣ ንፁህነትንም ሁሉ፣ ፍቅርንም ሁሉ፣ በጎነትይም ሁሉ ምስጋናንም ቢሆን አነዚህን ሁሉ አስቡ (ፊል 4፥8-9)
የግቢ ጉባኤ አባላት ባልሆነው ነገር መልካም ወሬ በለለበት ቦታ ከመገኘት መጠበቅ ይኖርባችኋል ሲል ነው።
ቀጣይ ትምህርታችን
#ግሎባላይዜሽን
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!
#ሼር-በማድረግ ቃሉን ለምዕመናን ያዳርሱ
@mahiberekidusan
⓬
684 viewsKingston Ethiopia, 05:38