Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahiberekidusan — ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahiberekidusan — ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahiberekidusan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

🌷ይህ ቻናል የተከፈተው ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን ዋና አላማውም ምዕመናን በንስሐ ህይወት ተመላልሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድወርሱ የሚያስችል ትምህርት መስጠት ነው፡፡
🌷💚የቅዱሳን ገድላት
🌷💛ስንክሳር
🌷♥ ቅዱሳን ስዕላት
መንፈሳዊ ትምህርቶችና ጽሑፎች
🎤 ስብከቶች ............ይቀርቡበታል፡፡🌎

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-06 16:04:49 @mahiberekidusan
196 viewsKingston Ethiopia, edited  13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:30:07 እንኳን ለሰማእቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሰን፡፡
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የአለምን ክብር በመናቅ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን የታገሰ ስለእግዚአብሔር ሊመሰክር ደሙን ያፈሰሰ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ በከሀድያን ነገስታት ፊት ስለ እግዚአብሔር ለሰባት አመታት የተጋደለ ሶስት ጊዜ ሞቶ የተነሳ ባለገድል ሰማዕት ነው፡፡
በመጨረሻ ዘመኑም ሰማዕትነት ሲቀበል ወደእግዚአብሔር ጸልዮ ሰባውን ነገስታት አስፈጅቷቸዋል፡፡
በዚህም እምነቱ እግዚአብሔር ሰባት አክሊላትን አቀዳጅቶታል፡፡
በስሙ መልካም ስለሚያደርጉት ሁሉ ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል፡፡ ብላቴናዋን ከዘንዶ ያዳናት እኛንም ከሚሠነዘርብን መቅሰፍት ከገሃነም በቃል ኪዳኑ ያድነን፡፡
የፈጣኑ ጊዮርጊስ በረከት ረድኤት ይደርብን፡፡ በጸሎቱ ከመጣው እና ከሚመጣው መቅሰፍት ይሰውረን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡

@mahiberekidusan
510 viewsKingston Ethiopia, edited  09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:28:37 @mahiberekidusan
425 viewsKingston Ethiopia, edited  09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 12:35:23 @mahiberekidusan
745 viewsKingston Ethiopia, edited  09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 21:45:03 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ለአመቱ ያድርሰን ።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
865 viewsKingston Ethiopia, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 21:08:36 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን...........
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ ውድ የማህበረ ቅዱሳን ፕሮግራም ተከታታዮች በዛሬው የትምህርት ክፍል ስለ ጾም እንማማራለን፡፡ የምስጢር ባለቤት እግዚአብሔር ምስጢሩን ይግለጽልን..........

ጾም
ጾም ማለት ለተወሰነ ጊዜ ከምግብና ከውሀ መከልከል ማለት ሲሆን ፍቃደ ስጋን ለፈቃደ ነፍስ ማስገዛት ማለት ነው፡፡
ጾም በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን
ብሉይ ማለት የቆየ የውል ስምምነት ማለት ነው፡፡
ጾም በብሉይ ኪዳን
መከራ ስጋን ለማቅለል ወይም ለማስወገድ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ለምሳሌ፦የነነዌ ህዝብ ከጥፋት ድነዋል፡፡ትንቢተ ዮናስን ያንብቡ
በብሉይ ኪዳን በመጾማቸው የተጠቀሙ አባቶች፦
ለምሳሌ፡ሙሴ 40 መዓልት 40 ሌሊትን ጾሞ ጽላትን ተቀብሏል ፤የኦሪት መጽሐፍትን ጽፏል፡፡
አብርሃም አጋእዝተ ዓለም ስላሴን በእንግድነት ተቀብሎ አስተናግዷል፡
ነቢያት የቃል ስጋ መሆን ትንቢት ተገልጾላቸዋል ፡፡
ንጉስ ዳዊት ከኃጢኣት ድኗል፡፡
የነነዌ ህዝብ ከጥፋት ድነዋል........ወዘተ
ጾም በሐዲስ ኪዳን
በሐዲስ ኪዳን ጾም አጋንንትን ለማውጣት ከመከራ ስጋና ነፍስ ለመዳን ይጾማል፡፡
ማር 9፥29 ሉቃ 6፥21
በሐድስ ኪዳን በመጾም የተጠቀሙ አባቶች፦
ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ ምስጢር ተገልጾላቸዋል
ሐዋርያት ድውያንን መፈወስ፣ለምጻሙን ማንጻት፣አጋንንት ማውጣት ችለዋል፡፡
ሐዋርያት የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትንሳኤ አይተዋል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት በመጾም በመጸለይ የእግዚአብሔርን መንግስት ወርሰዋል፡፡ እኛም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ከጾምን ከጸለይን የቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ቃል ኪዳን ለእኛም ይደረግልናል፡፡ ጾመን ጸልየን ክርስቲያናዊ ስነ ምግባርን ፈጽመን መንግስቱን ለመውረስ ስሙን ለመቀደስ ያብቃን፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሐዋርያት ትንሳኤዋን የገለጸች ለእኛም ምስጢር ጥበብን ትግለጽልን፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ጾሙን የኃጢአት መደምሰሻ የድያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜን፡፡
"እስመ ጾም እማ ለጸሎት""ጾም የጸሎት እናት ነች" ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
768 viewsKingston Ethiopia, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 20:44:19 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

#ሰላም- ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንደምን ናችሁ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ከምትጾማቸው አጽዋማት ውስጥ አንዱ ለሆነው ለጾመ ሐዋርያት ወይም ለሰኔ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡
"እስመ ጾም እማ ለጸሎት" ጾም የጸሎት እናት ነች፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ጾመዋል። በመጾማቸውም የእግዚአብሔር በረከት በላያቸው አድሮባቸው እስከመጨረሻው ዳርቻ ጸንተው የሰማዕትነትን ጽዋ በመቀበል የጽድቅ አክሊል ተቀዳጅተዋል ።
ጾም በረከተ ስጋን በማሰጠት የነፍስን ቁስል የምትፈውስ ሐኪም ነች፡፡ ጾም አጋንንትን የምንዋጋባት መንፈሳዊ ትጥቅ ነች፡፡ በአጠቃላይ ስለ ጾም እናውራ ብንል ወንዞች ቀለም ዕጽዋቶች ብዕር ቢሆኑ ተጽፎ አይዘልቅም፡፡

የጾም ጥቅም
1.የነፍስ ቁስልን ለመፈወስ
2.ከአጋንንት ቁራኝነት ለመላቀቅ
3.የስጋ ፍላጎትን ለመቀነስ
4.ግብረ እንስሳዊነትን ለመከላከል
5.የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ.......,..

በብሉይ ኪዳን በቅዱሳን አባቶቻችን እና እናቶቻችን በሐድስ ኪዳንከ ጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ በመጾም ተዓምቶች በጾም በጸሎት እንደተደረጉ እናት ቤተ ክርስቲያን አስተምራናለች፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም ይህንን የጀመርነውን ጸም ጾመው አልፈዋል ፡፡ ጾመውም መንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸዋል ፡፡ ስለዚህ እኛም ብንጾም በረከተ ስጋ ድህነተ ነፍስ እናገኛለን፡፡
አምላካችን ጾሙን የኃጢአት መደምሰሻ ፣የድያብሎስ ድል መንሻ ፣የመንግስተ ሰማያት መውረሻ ፣የልቦና ማደሻ ያድርግልን፡፡ አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@mahiberekidusan
551 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:08:40 #በዓለ_ጰራቅሊጦስ፤ (#በዓለ_ሃምሳ )

በዓለ ጳራቅሊጦስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላተ እግዚእ አንዱ እንደመኾኑ #ሰኔ 5 #ቅዳሜ_ለእሑድ_አጥቢያ_በኹሉም_ገዳማትና_አድባራት_ይከበራል፤ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሐዋርያትና በመንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል፤ በአዲስ አበባ #በጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያት_መንፈስ_ቅዱስ_/ኋላ/#ጎላ_ሚካኤል_ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ) ና በምሁር አክሊል ፤ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡
#በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤ.ክ ንም ይከበራል ፡ ተጨማሪ ከታች......

፠ ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፥ መጽንዒ (የሚያጸና)፥ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኀጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጕምን ይሰጣል /መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫/፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በኀጢአት ጭቃ የወደቁትንና የሚወድቁትን እንደሚያነጻቸው፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላሉት ኹሉ በፈተናቸውና በመከራቸው ኹሉ እንደሚያበረታቸው (እንደሚያጸናቸው)፤ የሚነዋወፁትን እንደሚያረጋጋቸው፤ ያዘኑትን እንደሚያጽናናቸው፤ የሚደክሙትን እንደሚያበረታቸው፤ የተከዙትንም ሐሴትን እንደሚሰጣቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ጻድቃንን ወደ ተጋድሎ፤ ሰማዕታትን ወደ ደም፣ መነኰሳትን ወደ ገዳም፣ ማኅበረ ክርስቶስን ምዕመናንንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ልቡናቸውን የሚያነሣሣና የሚመራ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ /ዮሐ.፲፮፥፲፪/፡፡

#በዓለ_ሃምሳ_በብሉይ በዓሃምሳ በብሉይ
እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ኃምሳን የሚያከብሩት ስለ ብዙ ምክንያት ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽልም፤
፩ኛ) ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ ምድረ ከነዓን ገብተው ለመዠመርያ ጊዜ እሸት የበሉበትን የሚዘክሩበት ነው፡፡ ዳግመኛም በበረኻ ሳሉ እግዚአብሔር ከሰማያት ኅብስተ መናን አውርዶ፥ ከጭንጫ ውኃን አመንጭቶ እንደመገባቸው ይዘክሩበታል፡፡ በመኾኑም በዚኽ በዓል ቀዳምያት፥ ዐሥራትና በኵራት እያወጡ፣ በየዓመቱ ከሚዘሩት እኽል እሸት (በብዛት ስንዴ) እየበሉ እግዚአብሔርን ስለ ምድር ፍሬ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው፡፡
፪ኛ) እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን ስለተቀበሉበት ይኽን ያስቡበታል፡፡
፫ኛ) እግዚአብሔር ከምድረ ግብጽ በታላላቅ ገቢረ ተአምራት ስላወጣቸው ይኽን ያስቡበታል፡፡

፠ ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ይኽ በዓል እኽል በሚታጨድበት በመከር ወቅት የሚከበር በዓል ነው፡፡ መከር ሲገባ መጀመርያ ከሚሰበስቡት እኽል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ታዝዘው ነበር /ዘጸ. ፳፫፡፲፮/፡፡ በመኾኑም ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሰባት ሳምንታት (፵፱ ቀናት) በየዕለቱ አንድ መስፈርያ እኽል ይሰጡ ነበር፡፡ በ፶ኛው ቀን ደግሞ ሊቀ ካህኑ ከተሰበሰበው እኽል በትልቅ መስፈርያ አድርጎ ካቀረበ በኋላ መሥዋዕተ በግ ይሠዋ ስለነበር ታላቅ በዓል ኾኖ ይከበር ነበር /ዘሌ. ፳፫፥፲-፲፯፣ ዘዳ. ፲፪፥፭-፯/፡፡

#አማናዊ_ትርጓሜ_በሐዲስ ( አማናዊ ትርጓሜ በሐዲስ)
፠ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ድኅነተ ዓለምን በፈጸመበት ዓመት ግን፥ እስራኤል ዘሥጋ ከላይ በገለጥነው መንገድ ከያሉበት ተሰባስበው በዓሉን በኢየሩሳሌም ሲያከበሩ፤ ለእሥራኤል ዘሥጋና ለእሥራኤል ዘነፍስ ብርሃን እንዲኾኑ የመረጣቸው ሐዋርያትም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በደብረ ጽዮን በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰባስበው ነበር /ሉቃ. ፳፬፡፵፱/፡፡ በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜም ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በዚኽም ብሉይና ሐዲስ ተገናኙ፤ ተተካኩ፡፡
፠ የነቢያት ትንቢታቸው፥ የሐዋርያትም ስብከታቸው የኾነው ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በደብረ ታቦር ተራራ እንዳገናኛቸው፥ በዚያም ክብረ መንግሥቱን፥ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጸላቸው የሚታወስ ነው /ማቴ. ፲፮፡፩-፯/፡፡ በምሴተ ኀሙስም በቤተ አልዓኣዛር የብሉይ ፋሲካን እንዳዘጋጁና እርሱም መሥዋዕተ ብሉይን በመሥዋዕተ ሐዲስ እንደተካው የተጻፈ ነው /ማቴ. ፳፮፡፲፯-፳፱/፡፡ በበዓለ ኃምሳ የኾነውም ልክ እንደዚኹ ነው /ሐዋ. ፪/፡፡ ይኽ ኹሉ በኢየሩሳሌም፣ በመዠመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በተሰየመች በቤተ ማርያም (የማርቆስ እናት) ተፈጸመ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለፊተኞችም ለኋለኞችም እናታቸው እንደኾነችም ታወቀ፤ ተረዳ፡፡

፠ ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ ፴፩ ላይ፤ ‹‹ከዕርገቱ ቀን በኋላ ታላቅ በዓል ይደረግ፤ በዚኽች ቀን በሦስተኛው ሰዓት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና እኛም በርሱ ስጦታዎች ተሞላን፤ አዳዲስ ቋንቋም ተናገርን›› በማለት በዓሉን በቤተ ክርስቲያን ልናከብረው እንዲገባ ሥርዐት ሐዋርያት የሠሩልንም ስለዚኹ ነው፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት የታነጸችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኽንኑ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት አንዱ በማድረግ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡

#ርደተ_መንፈስ_ቅዱስ
፠ ጌታችን እንደነገራቸው መቶ ሃያው ቤተ ሰብእ በቤተ ማርያም ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ድረስ ተሰብስበው ነበር፡፡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ውጪ መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚወርድም አያውቁም ነበር /ሐዋ. ፪፥፪/፡፡ ጌታችን ባረገ በዐሥረኛው ቀን ግን እኔና እናንተ እንደምንሰማው ዓይነት ያይደለ፥ ነገር ግን ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፡፡ ያሉበትን ቤት ሞላው፡፡ ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ኾኖ ታያቸው፡፡ በበደልን ጊዜ ከእኛ ርቆ ነበርና አኹን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለታረቅን በኹሉም አደረባቸው: /ማቴ. ፫፡፲፩/፡፡ ኀይል የሚኾናቸው ሀብትን፣ ሀብት የሚኾናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡

#መንፈስ_ቅዱስ
፠ መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሠለስ፥ የሚቀደስ፥ የሚወደስ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ እንደ አብና ወልድ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም መልክዕ፥ ፍጹም አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንጂ ሕጹጽ (ብትን፣ ዝርው) አይደለም፡፡ በተለየ አካላዊ ግብሩም መሥረፅ (መውጣት) ነው፤ መሥረጹም ከአብ ብቻ እንጂ አንዳንዶች (ካቶሊኮችና መካነ ኢየሱሶች) እንደሚሉት ከወልድም ጭምር አይደለም /ዮሐ.፲፭፡፳፮/፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አያሠርጽም፥ አይወልድም፥ አይወለድም፡፡

በባሕርይ፥ በመለኮት፥ በሥልጣን፥ በሕልውና፥ በአገዛዝ፥ ዓለማትን በመፍጠርና በማሳለፍ ከአብና ከወልድ ጋራ የተካከለ ነው /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡ ቀዳሚነትም ኾነ ተቀዳሚነት የሌለው ይልቁንም ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ (ዕሩይ) ነው፡፡ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር፥ ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብ ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ተካክሎ ይህ ነው ለማይባል ዘመን ወደፊት የሚኖር ደኃራዊ ነው፡፡
836 viewsKingston Ethiopia, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 00:33:42 ሁለተኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

ሰላም ውድ የማኀበረ ቅዱሳን ቻናል ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ ። በረድኤት ያልተለየን በቸርነቱ የጠበቀን ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን
#አድስ-ኮርስ ነው እንድትከታተሉ በትህትና እንጠይቃለን ።
__________
ሁለተኛ
ኮርስ

#ነገረ__ሃይማኖት


#ምዕራፍ-፩ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት መግቢያ

#ሃይማኖት_ምንድነው?
ሃይማኖት፦ ሐይመ
ነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተሰደ ሲሆን ትርጉሙ ማመን መታመን ማለት ነው።

ማመን፦ ማመን ማለት በአንድ ስጋ/በእዝነ ስጋ / ጀሮ ሰምቶ፣ በልብ አስቦ በአጠቃላይ በስሜት ህዋሳትም ቢሆን አድምጦ እና ዳሶ ሊመረምሩት የማይቻለውን በእርቀት (እሩቅ በመሆን) እና በርቀት (በረቂቅነት) ያለውን ይሆናል።
ይደረጋል ብሎ መቀበልና እግዚአብሔርን አለ፣ ይኖራል ሁሉን ያዥ፣ ሁሉን ገዥ ነው ብሎ በልብ በረቂቅ መሳልና ማሰብ ሀሳብን በማወቅ ማረጋገጥ፣ መፍቀድ፣ መውደድ፣ መመካት ተስፋ ማድረግ ማለት ነው።

መታመን፦ መታመን ማለት ደግሞ በልብ በረቂቅ ሀሳብ ያመኑትን በአንደበት መመስከር መናገር፣ ወዶና ፈቅዶ በደስታ መቀደስ፣ ማመስገን፣ በግብር መግለፅ መተግበር፣ መስገድ፣ መገዛት፣ መገበር ማለት ነው።
እንዲሁም መታመን ማለት ይሆናል ይደረጋል ብሎ በእምነት የተቀበሉትን እንዲሆን እንዲደረግ፣ እንዲፈፀም ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ማለት ነው።
እነዚህን ሁለቱን ከያዘ ከተገበረ ሀይማኖት አለው ይባላል። (ማር 16፥16 ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል።)

ምላሹ፦ በማመንና በእግዚአብሔር መጠመቅ ነው። ሉቃ 15፥11-32
ልብስ የተባለው ሀይማኖት ነው፣ ቀለበት እሰሩለት የተባለው ቃል ኪዳኑን ነው፣ ለእግሩ ጫማን አጨሙት የተባለው፣ ወንጌልን ስጡት ነው፣ የሰባውን ፍሪዳ እረዱ እና እንብላ ማለቱ ስጋወደሙን ነው። ይህ ልጅ ሙቶ ነበር አሁን ግን ህያው ሁኖል ማለት የሰው ልጅ በህይወት እያለም ይሞታል ማለት ነው። ምክኒያቱ ደግሞ ከሀይማኖት ሲለይ
/ሲወጣ፣ አባት የተባለው እግዚአብሔር አምላክ ነው ከሞትም ወደ ህይወት ተለውጧል ያለው በንስሐ ነው።
~~~~~~~~

#ወስብሐት# _ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan

704 viewsKingston Ethiopia, 21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 10:35:43 የመጀመሪያ ኮርስ -ነገረ ክርስትና
የቀጠለ.....
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

__
#መንፈሳዊ_አገልግሎት
ማንኛውም ስራ አገልግሎት ብለን ል
ጠራው እንችላለን ነገር ግን የሚያስገኙት ዋጋ የተለያየ ነው።
ለምን ቢሉ፦
➀ ጠሪው እግዚአብሔር ነው። (ዮሐ 15፥16)
➁ዋጋው ምድራዊ ብቻ ሳይሆን ሰማያዊም ነው።
➂ በስጋዊ ጥበብ የሚሰራ ሳይሆን በመንፈሳዊ እውቀትና በረድኤተ እግዚአብሔር የሚሰራ ነው።
መንፈሳዊ አገልግሎት እንደስሙ ረቂቅ በሆነው መንፈሳዊ ሀይልና ጥበብ ተሞልተው የሚያገለግሉት ህይወት ነው። አገልጋዩም መንፈሳዊ አገልጋይ ይባላል።

#የመንፈሳዊ_አገልግሎት_መገለጫዎች
ሰማያዊ ዋጋ ታስቦ የሚደረግ ነው
አገልግሎቱ በመንፈሳዊ ጥበብ የሚከናወን ነው
አገልግሎቱ በትህትና የሚደረግ ነው
አገልግሎቱ መስዋዕትነት ያለበት ነው
አገልግሎቱ በፍቅር የሚከናወን ነው
#መንፈሳዊ_አገልግሎት_በ3_ይከፈላል
እራስን ማገልገል
ህዝብን/ምዕመንን ማገልገል
እግዚአብሔርን ማገልገል ናቸው።

#የመንፈሳዊ_አገልግሎት_ተግዳሮቶች
መባከን
ስፋ መቁረጥ
ግዴለሽነት
4️
⃣ ቸልተኝነት
ጊዜአዊነትና ነገ ሟች መሆንን መርሳት

#የመንፈሳዊ_አገልግሎት_ዋጋ
➀ ምድራዊ በረከትን ይሰጣል
➁ ሰማያዊ ወጋ
ን ይሰጣል
➂ ታሪካዊ ህይወትን ያስገኛል

በመጨረሻም፦
#የተማሩትን_በተግባር_መኖር፦
እግዚአብሔር የተማርነውን እንድንኖር ቅዱስ ፍቃዱ ይሁንልን!!
የእግዚአብሔር ፀጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስ ህብረት፣ የእመቤታችን አማላጅነት የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና በረከት በሁላችን ላይ ይሁን አሜንንን
~~~~

#ሼር#ጥያቄ ካላችሁ መጠይቅ ትችላላችሁ
ቀጣይ ትምህርታችን
ነገረ ሐይማኖት~>አዲስ ኮርስ ነው
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan

681 viewsKingston Ethiopia, edited  07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ