Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahiberekidusan — ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahiberekidusan — ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahiberekidusan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

🌷ይህ ቻናል የተከፈተው ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን ዋና አላማውም ምዕመናን በንስሐ ህይወት ተመላልሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድወርሱ የሚያስችል ትምህርት መስጠት ነው፡፡
🌷💚የቅዱሳን ገድላት
🌷💛ስንክሳር
🌷♥ ቅዱሳን ስዕላት
መንፈሳዊ ትምህርቶችና ጽሑፎች
🎤 ስብከቶች ............ይቀርቡበታል፡፡🌎

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-15 20:44:12 የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር-ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
773 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:44:12 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር-ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekiduaan
753 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:44:12 የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር-ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
760 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:44:12 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
780 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:44:12 ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች እንደት ከረማችሁ ። ሱባኤ እንዴት ነው። በርቱ አይዟችሁ። ተቀሳቀሱ እንዳትለያዩ። ይህንን ክፉ ጊዜ ማለፍ የሚቻለው ወደ እግዚአብሔር በመጮህና በመደጋገፍ ነው

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
395 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:44:11 የእሁድ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር-ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
387 viewsKingston Ethiopia, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:28:33 #በስመ-አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን
​​#ነሃሴ_7
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

#ቁጽረታ_(ጽንሰታ)ለማርያም

ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል።

#ስለ\ምን_ነው_ቢሉ :- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ።

"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" - "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)

ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል።

የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር።

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም።

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች።

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ።

እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ።

በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች።
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" - "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም)

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
625 viewsKingston Ethiopia, 07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:23:25 ′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

የቀጠለ .......

__________
#የዕለተ_ማክሰኞ__ሥነ_ፍጥረታት
ሰሉስ ሰለሰ ሶስት አደረገ ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሆኖ ለፍጥረት ሶስተኛ ቀን ማለት ነው።
የተፈጠሩት ፍጥረታትም 3 ናቸው።
, በጣት የሚለቀሙ አትክልት
, በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት
, በምሣር የሚቆረጡ ዕፀዋት ናቸው።
(ዘፍ 1፥9-13)
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ይህ ቀን እግዚአብሔር ከአፈር ጋር ተቀላቅሎ የነበረውን ውሃ በምድር ዙርያ ከወሰነው በኋላ ፤ የመሬት ገጽ የታየበት እና ሰማይና ምድር ዛሬ በምናየው ሁኔታ የተዘጋጁት ፤ ምድርም የዛሬ ቅርጿን የያዘችበት ብሩህ ዕለት (ቀን) ነው። እሑድ የተፈጠሩት ፍጥረታት (ሃያውን ዓለማት)  በየቦታቸው የተከናወኑትም በዚሁ ቀን ነው ። ሃያው ዓለማት የሚባሉትም።

-->ዓለማተ መሬት 5 የጋራ ስማቸው ዱዳሌብ

-->ዓለማተ ማይ 4 የጋራ ስማቸው ናጌብ

-->ዓለማተ እሳት 9 የጋራ ስማቸው ኮሬብ

-->ዓለማተ ነፋስ 2  የጋራ ስማቸው አዜብ ናቸው

ገሐነመ እሳት፣ ሲኦል እና ገነት፣ ብሔረ ህያዋን፣ ብሔረ ብፁዓን ተብለው የተሰየሙት በዚህ ቀን ነው።
እግዚአብሔር አስቀድሞ እነዚህን ዓለማት በየቦታቸው ካዘጋጀ በኋላ በመሬት ላይ ሶስት ፍጥረታትን ብቻ ፈጥሯል።

እነዚህም፦
በእጅ የሚለቀሙ:--አትክልት (በመሬት ውስጥ የሚያፈሩ እንደ ካሮት ድንች …)

በማጭድ የሚታጨዱ:--አዝርዕት (የአገዳ እህሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ጤፍ …)

በመጥረቢያ የሚቆረጡ:--ዕፀዋት (የዛፍ ዓይነቶች እንደ ዋርካ ወይራ ሾላ…) የመሳሰሉት ናቸው።

የተፈጠሩትም ከአራቱ ባህርያት ነው።
ከመሬት እንደ መፈጠራቸው ሲጣሉ አፈር ይሆናሉ።

ከውሃ እንደ መፈጠራቸው በውስጣቸው ፈሳሽ አላቸው።

ከእሳት እንደመፈጠራቸው ይቃጠላሉ።

ከነፋስ እንደመፈጠራቸው አየር (ነፋስ) ያስገባሉ ያስወጣሉ።

ከአራቱ ባህርያት አንዱ ከተጓደለ ግን ይደርቃሉ እነዚህም የምድር ጌጦች ሲሆኑ ሰውም ለምግቡም ሆነ ለሚፈልገው አገልግሎት ይጠቀምባቸዋል።
~~~~~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ሕያው አለማት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan


❸❻
489 viewsKingston Ethiopia, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 10:28:09 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

የቀጠለ......
__
#የዕለተ_ሰኞ__ሥነ_ፍጥረታት
በሁለተኛው ቀ
ን 1 ፍጥረት ብቻ ነው የተፈጠረ ውሀ ተከፈለ እንጅ የተፈጠረ እሑድ ነው።

#ጠፈር
እሑድ ማታ ለሰኞ አጥቢያ እግዚአብሔር በውሃ መካካል ጠፈር ይፈጠር አለ በውቂያኖስና በሐኖስ መካከል ድንበር ይለይ ዘንድ እንዳለውም ሆነ።
ጠፈር ማለት ኃያል ጽንዕ ማለት ነው ለሐኖስ ኃይል ጽንዕ ነውና አንድም በምድር ለሚኖሩ ቤት ማለት ነው ለሰው ለአራዊት ለፍጥረታት ሁሉ መኖርያ ነውና፡፡
ሥዕለ ማይ ማለት ነው፡፡

ጠፈርንም በሰማያዊ ቀለም አምሳል ፈጥሮታል እጅግም ቢበራ ዓይን ይበዘብዝ ነበርና እጅግም ጨለማ ቢሆን ለዓይን ይከብድ ነበርና በሰማያዊ ቀለም አምሳል ፈጥሮታል፡፡

ዕለተ ሰኞ ቀን በመጀመሪያ ሰዓተ ሌሊት ውሃ ከምድር ጀምሮ እስከ ብሩህ ሰማይ ድረስ ሞልቶ አድሮ ነበርና ያንን ለሦስት ከፈለው፡፡

--> አንዱን እጅ ውሃ ከጠፈር በላይ ተሰቀለ ስሙንም ሀኖስ አለው።
--> ሁለተኛው እጅ ውሃ ደግሞ ለምድር ምንጣፍ ሆነ
--> ሶስተኛው እጅ ውሃ እንደ መቀነት ተጠምጥሞ በምድር ዳርቻ ዙሪያውን ቆመ ስሙንም ውቅያኖስ አለው።


ጠፈር ለምን ተፈጠረ?
ጠፈርን እግዚአብሔር የፈጠረበት ምክንያት በዕለተ ረቡዕ ለሚፈጥራቸው ፍጥረታት ማደሪያ መመላለሻ ይሆን ዘንድ ነው፡፡

እመቤታችንና ዕለተ ሰኞ
በሰኞ ዕለት የብርሃን ማኅደር የኾነው ጠፈር ተገኝቷል /ዘፍ.1፡6-7/፡፡ ከእመቤታችንም ብርሃን ክርስቶስ ተገኝቷልና እመቤታችን በዕለተ ሰኞም ትመሰላለች /ዮሐ.1፡5-9፣ ውዳሴ ማርያም ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው፣ ንባቡና ትርጓሜው፣ ገጽ 15-17/፡፡
~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
የሰኞ ሥነ ፍጥረታት
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan



❸❺
480 viewsKingston Ethiopia, 07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 15:53:31 ′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′

ከባለፈው የቀጠለ......
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

__
#ኤረር
በአስራ አ
ንደኛው ሰዓት ለሊት በኤረር ያለትን/የቀሩትን መላእክት ልክ እንደ ራማ በነገድ 30 በአለቃ 3 አድርጎ አስፈሮአቸዋል።

ሀ, በመጀመሪያው ከተማ 10ን ነገድ መኳንንት (መዝ 3፥24 እስከ 6፥10) በማለት ሰዳክያል የተባለውን መላእክ አለቃ አድርጎላቸው አስፍሮአቸዋል።
የስላሴ ቀስተኞች ናቸው። ማቴ 24፥31

ተራራ የሚንድ ድንጋይ የሚሰነጥቅ የእሳት ፍላፃ የእሳት ቀስት ይዘው ሰውን ሁሉ ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ የሚጠብቁ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በትንሣኤ ዘጉባኤ የሰውን ሁሉ አጥንት የሚሰበስቡና ምድርን ለምጽአት እንዲያዘጋጁ የሚላኩ ናቸው፡፡

ለ, በኤረር በሁለተኛው ከተማ አስሩን ነገድ ሊቃናት በማለ አለቃቸው ይሆን ዘንድ ሰላታኤል የተባለውን መላእክ ሾሞታል።
የስላሴ የፈረስ ባልደራስ ናቸው። በልባቸው የሚሳቡትን፣ በእግራቸው የሚሽከረከሩትን፣ በክንፋቸው የሚበሩትን የሚጠብቁ መላእክት ናቸው።

ሐ, በኤረር በ3ተኛው ከተማ አሥሩን ነገድ መላክት (1ጴጥ 3፥12) ብሎ ሰይሟቸዋል። አለቃቸውም አናንያ ይባላል።
አገልግሎታቸው እንደብረት የፀና የሳት ነጎድጓድን ወደ ምድር የሚወነጭፉ ፀሀይን፣ ጨረቃን፣ ክዋክብትን፣ አዝዕርትን፣ አትክልትን፣ እፅዋትን በላይ በሰማይ በታች በምድር የተፈጠሩትን ሁሉ የሚጠብቁ መላኢክት ናቸው።

እነዚህ መለእክት አርአያቸው/መጠናቸው የተለያየ ነው። ቁመታቸው አምድር እስከ ሰማይ የሚደርሱ መላእክት አሉ። መዝ 84፥3 ዘፍ 38...
በክንፋቸው አንድ ሀገርን የሚያለብሱ መላእክት አሉ። እራሳቸው ተራራ የሚያክል አሉ። መብረቅ ተጎናፅፈው/ለብሰው የሚኖሩ መላእክትም አሉ። በሀሩን ምንጩን በክንፋቸው የሚያቃጥሉ መላኢክት አሉ ማቴ 28፥3 ዮሐ 12፥7

#ብርሀን
እግዚአብሔር እሑድ ጧት ከቀኑ በመጀመሪያው ሰዓት ብርሀን ይሁን ብሎ ቢያዝ በምስራቅ በኩል ብርሀን ተፈጠረ ዘፍ 1፥3-14
ያንንም ብርሀን በምስራቅ በኩል መንገድ ሰራለት። ስሙንም መዕልት አለው። ማዕልትም ማለት ብርሐን ማለት ነው።

#ጨለማ
ከፍጥረት ሁሉ ጥቁር ጥቁሩን ወስዶ በርባኖስን ፈጠራት ይህች በርባኖስም እልፍ አእላፍ ፀሀይ ቢገባባት አትበራም አትታይም ጨለማም ከበርባኖስ ፈጥሮአል።

ስለምን ጨለማን ፈጠረ ቢሉ ጨለማ አይታይም አይዳሰስም እንዲሁም ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርየ መለኮቱ አይመረመርም፣ አይተረጎምም፣ አይዳበስም፣ አይጨበጥም (ዮሐ 1፥18 ፤ መዝ 17፥11-16
~~~~

ቀጣይ_ትምህርታችን
የሰኞ ሥነ-ፍጥረታት
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግልወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
❸❹
541 viewsKingston Ethiopia, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ