Get Mystery Box with random crypto!

ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahberetsion — ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahberetsion — ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን
የሰርጥ አድራሻ: @mahberetsion
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.85K
የሰርጥ መግለጫ

ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን:
✍የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ
✍ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መዝሙራት
✍ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች
✍ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ
✍ ወቅታዊ መረጃዎችና ሌሎችንም የሚያገኙበት ቻናል
➾ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Hailegebereal19አድርሱን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-26 20:27:28 ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።

#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።

#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።

#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል።

#ምልጃሽ #ኢትዮጵያን #ይታደግ። ለአለም ምህረት ይሁን ።
38 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:27:06 ድንግል ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ ስለዚህ ወደ ሰማይ ማረግዋ ክብሩ ለሰማዩ እንጂ ለእርስዋ አይደለም፡፡

እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ በእርግጥ አቀባበሉ እንዴት ይሆን? እኛ የሰው ልጆች እናታችንን ማክበርም መጦርም የምንችለው በምድር እስካለችና እኛም እስካለን ድረስ ነው፡፡ ‹እናትና አባትህን አክብር› ያለን ፈጣሪ ግን እናቱን ማክበር የሚችለው በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ነው፡፡ እናቱ ወደ እርሱ ስትመጣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንዴት ተቀብሏት ይሆን?
ንጉሥ ሰሎሞን እናቱ ቤርሳቤህ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመጣች ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ‹‹ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም ፤ በዙፋኑም ተቀመጠ ፤ ለእናቱም ወንበር አስመጣላት በቀኙም ተቀመጠች፡፡ እርስዋም ፡- አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች፡፡ ንጉሡም ፡- እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ለምኚ አላት›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (1ነገሥ. 2፡19-20) ከዳዊት ሆድ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ሰሎሞን ይልቅ በዳዊትን ዙፋን ለዘለዓለሙ ይነግሣል የተባለለት ክርስቶስ ይበልጣል፡፡ ስለ ክርስቶስ ‹‹ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማቴ. 12፡42) ክርስቶስ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከሆነ የክርስቶስ እናትም ከሰሎሞን እናት ትበልጣለች፡፡ ሰሎሞን ለእናቱ ከሠጣት ክብርም በላይ ክርስቶስ ለእናቱ የሚሠጣት ክብር ይበልጣል፡፡ የሰሎሞን ቤተ መንግሥት በምድር ነው ፤ የክርስቶስ ቤተ መንግሥት ግን በሰማይ ነው፡፡ መድኃኔ ዓለም ወደ ሰማያዊው መንግሥቱ እናቱን በጠራት ጊዜ እንደምን ተቀብሏት ይሆን? እንደ ሰሎሞን እናት ወንበር አስመጣላት እንዳንል በሰማይ መቆም መቀመጥ የለም፡፡ ነገር ግን ‹‹የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› ተብሎ ድንግሊቱ ስለተሠጣት ክብር ተጽፎአል፡፡ ወርቅ መልበስዋ አነሳት የሚል ካለ ደግሞ ‹‹አሕዛብን በብረት በር የሚገዛቸውን ወንድ ልጅ የወለደችው›› ድንግል ‹‹ፀሐይን ተጎናጽፋ ፤ ጨረቃም ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ፣ ዐሥራ ሁለትም ከዋክብት አክሊል የሆኑላት አንዲት ሴት ነበረች›› ተብሎ ተጽፎላታል፡፡ (መዝ. 44፡9 ፣ ራእ. 12፡1)

ለእኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር አቀባበል በሕሊናችን ከማሰብ በቀር ምን የሚያውከን ነገር የለም፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ድንግልን ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? እዚህ ‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ› ብሎ ሰላምታ ያቀረበላት ይህ መልአክ ጸጋን የተሞላችው ወደ እርሱ ስትመጣ ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? ቅድስት ኤልሳቤጥስ አሁንም ‹ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?› ብላት ይሆን? መጥምቁስ ዳግም በሰማይ በደስታ ዘልሎ ይሆን? ነቢያቱ ድንግልን እንዴት ተቀበሏት? ኢሳይያስ ‹ትፀንሳለች› ያላትን ድንግል ሲያያት ምን ይል ይሆን? ሕዝቅኤልስ ‹የተዘጋችዋ ደጅ› ወደ እርሱ ስትመጣ ምን አለ? ጌዴዎን ጸምሩን ፣ ኤልሳዕ ማሰሮውን ፣ አሮን በትሩን ፣ ኖኅ መርከቡን ባየ ጊዜ ምን ብሎ ይሆን? ሙሴስ ያልተቃጠለችው ዛፍ ወደ እርሱ ስትመጣ ዳግም እንደ ሲና ተራራው ጊዜ ጫማውን አውልቆ ይሆን? አዳም የልጅ ልጁን ሲያይ ሔዋንስ ዳግሚት ሔዋንን ስታይ ምን ብላ ይሆን? ሁሉንም በሰማይ ለመረዳት ያብቃን!
@ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

የእመቤታችን ትንሣኤ እንዲህ ሲገለጥ እንዴት ደስ ይላል በረከቷ በሁላችንም ላይ ይድረሰን አሜን!

ሼር በማድረግ ለሌላው ያዳርሱ ዘንድ በፍቅር እጠይቃለሁ
38 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:26:48 ++አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት++
❖ ❖ ❖ ❖

አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት
ብሎ ዳዊት ስለ ቤተ መቅደስ መሠራትና ታቦቱም ወደ ቤተ መቅደሱ ስለመግባቱ የዘመረው መዝሙር ፣ ልጁ ሰሎሞንም መቅደሱ ተሠርቶ ሲያልቅ ደግሞ የዘመረው ይህ መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? (2ዜና 6፡41) ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ከጥንት ጀምሮ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ጋር የሚጠቅሱት ዳዊት ስለ መቅደሱ መሠራትና ስለ ታቦቱ መግባት የተናገረ መሆኑ ጠፍቷቸው ነው? ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር አገናኝተን እንድናስብ ያነሣሣን ምንድር ነው? ወደሚለው እንምጣ፡፡

ዳዊት ስለ ታቦቱ የተናገረውን እኛ ስለ ድንግል ማርያም ሆኖ እንዲሰማን ያደረገው ራሱ ዳዊት ነው፡፡ ዳዊትን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እርሱ ስትመጣ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?›› ሲል አልሰማነውምን? (2ሳሙ. 6፡9) ይህን ንግግርስ ኤልሳቤጥ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› ብላ ለድንግል ማርያም አልደገመችውምን? (ሉቃ. 1፡43) ዳዊት የፈራው ታቦት ወደ እርሱ ሲቀርብ ከዙፋኑ ተነሥቶ በታቦቱ ፊት እየዘመረ ሚስቱ ሜልኮል እስክትንቀው አልዘለለምን? (2ሳሙ. 6፡16) በኤልሳቤጥ ማኅፀን የነበረው ዮሐንስስ የድንግልን ‹‹የሰላምታዋን ድምፅ በሰማ ጊዜ› እናቱ እስክታደንቀው ‹ፅንሱ በደስታ ዘለለ›› አልተባለምን? (ሉቃ. 1፡44) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የድንግል ማርያምና የልጅዋ ክብር ላልገባቸው ሰዎች ‹‹እንደ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ መዝለል ቢያቅታችሁ ምነው ነፍስ ካወቃችሁ በኋላ እንኳን ለእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ ዳዊት በምስጋና ብትዘሉ?›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ እኛ ምን እናድርግ የእግዚአብሔር ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች እንደተባለ ‹‹ማርያምም በዘካርያስ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች›› ተብሎ ተጽፎ አነበብን፡፡ (2ሳሙ. 6፡11 ፤ ሉቃ. 1፡56) ታዲያ የድንግል ማርያም ታሪክ ከእግዚአብሔር ማደሪያ ከታቦቱ ታሪክ ጋር አንድ ሆኖ ስናገኘው ዳዊት ስለ ታቦት የተናገረውን ስለ ድንግል ማርያም እንደምን አንጠቅስ? የነገረ ማርያምን ታሪክ እንጥቀስ ካልንማ ታቦቱ በወርቅ እንደተለበጠ በንጽሕና ያጌጠችውን ፣ ታቦቱ በመቅደስ እንደኖረ በመቅደስ ያደገችውን ፣ ታቦቱን በትሩ አብባ የተገኘች አሮን እንደ ጠበቃት በትሩ ያበበች ዮሴፍ የጠበቃትን፣ ታቦቱን የነካ ዖዛ እንደተቀሠፈ (2ሳሙ. 6፡7) የድንግልን ሥጋ ነክቶ የተቀሠፈውን ታውፋንያ ታሪክ እንጠቅስ ነበር፡፡

‹የመቅደስህ ታቦት› ማለት መቅደስ የተባለው የሰውነትህ ማደሪያ እናት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ሰውነቱን ‹ይህን መቅደስ አፍርሱት› አላለምን? ‹በጉ መቅደስዋ ነው› ተብሎ አልተጻፈምን? ስለዚህ ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ማለት ጳውሎስ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ እንዳለው ‹‹ጌታ ሆይ ‹ዕረፍትህ› ወደተባለ ወደ ሰማያት አንተ ብቻ ተነሥተህ አትቅር የመቅደስ ሰውነትህ ማደሪያ እናትህንም ይዘህ ተነሥ›› ማለት ነው፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤ ብዙዎችን ማከራከሩ እንዴት ያሳዝናል? ክርስቶስ ‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ› ብሏል፡፡ እውነት ትንሣኤን ለወለደች እናት መነሣትዋ ትልቅ ነገር ነው? የሕይወት እናት ሕያው ሆነች ቢባል ያስቆጣልን? ሞትን የሞተው በልጅዋ አይደለምን? የሕይወትን እናት ሞት ይዞ አስቀራት ማለት ደስታ የሚሠጠው ለሞት አበጋዞች ነው፡፡ ‹‹አምላክ ያደረባት የምትናገር ታቦት ፈርሳ ቀርታለች ማለት ፣ ታቦተ ጽዮን ድንግል በሞት ፍልስጤም ተማርካ ቀርታለች›› ማለት የሚያስደስተው በማኅፀንዋ ፍሬ የተፈረካከሰው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚደንቀን መሞትዋ እንጂ መነሣትዋ አይደለም፡፡

ቅዱስ ያሬድ ‹‹የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል›› እንዳለው ሕይወትን ያስገኘች ድንግል ፣ አምላክን የታቀፉ ክንዶች ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆኑ ጉልበቶች በሞት መሸነፋቸው ያስደንቀናል፡፡ መነሣትዋ ግን የምንጠብቀው ነው፡፡ አልዓዛርን ‹አልዓዛር አልዓዛር› ብሎ ያስነሣ ጌታ ፣ በዕለተ ዓርብ በሞቱ ብዙ ሙታንን ያስነሣ ጌታ እናቱን አስነሣ ሲባል የሚቆጡ እንዴት ያሉ ናቸው?

ሁለቱ ምስክሮች የተባሉ ሄኖክና ኤልያስ ወደ ምድር መጥተው አስተምረው ከተገደሉ ‹‹ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ… በሰማይም ፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ ወጡ›› ይላል፡፡ (ራእ. 11፡4-12) ሄኖክና ኤልያስን ከምጽአቱ በፊት ዳግም ላይሞቱ ከሞት አስነሥቷቸው በጠላቶቻቸው ፊት ወደ ሰማይ የሚያሳርጋቸው አምላክ እናቱን በወዳጆችዋ ፊት አስነሥቶ አሳርጓታል ሲባል በቁጣ መቃወም ምን ይባላል?

እንደልጅዋ በራስዋ ዐረገች (Ascension) በማለትና ልጅዋ ወደ ራሱ ነጥቆ ወሰዳት (Assumption) በማለት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከቻልን የእመቤታችን ማረግ ምኑ ያከራክራል? ዝናምን ከከለከለው ኤልያስ ንጹሑን ዝናም ያስገኘችው ድንግል አትበልጥምን ፣ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረገው ሄኖክስ ይልቅ ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው እመ አምላክ አትበልጥምን?

እኛ ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹‹በሞትዋ ምድር መራራ ኀዘን ስታዝን በሰማይ ደስታ ሆነ እንዳለ›› እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገርም ሆነ ፣ በልጅዋ ሥልጣን ተነሥታ ስታርግ በሰማይ የሚኖረውን ደስታ በእምነት እናስተውላለን፡፡ ያ ደሃ አልዓዛር እንኳን ሲሞት መላእክት ነፍሱን ወደ አብርሃም አጅበው ወስደውት ነበር ፣ ኤልያስም ሲያርግ መላእክት በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረሶች ነጥቀውት ነበር፡፡ የአምላክን እናት ዕርገት ስናስብ ከዚህ በላይ ዝማሬ ይታየናል ፤ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደጻፈው ቅዱስ ያሬድም ‹በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ› እንዳለው አባትዋ ዳዊት ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› እያለ እየዘመረ ወላዲተ አምላክ ወደዚያኛው ዓለም ተሸጋግራለች፡፡ ኤልያስ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ መጎናጸፊያውን ለበረከት እንዲሆነው ለደቀ መዝሙሩ ኤልሳዕ እንደሠጠው እመቤታችንም በልጅዋ ሥልጣን ወደ ሰማይ ስታርግ መግነዝዋን (መታጠቂያዋን) ለቶማስ በመሥጠትዋ ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት አሁንም ድረስ ተከፋፍለው በታላቅ ፍቅር በረከትዋን ይቀበሉበታል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ስለ እመቤታችን መነሣት ስናስብ የምንጠይቀው ‹ተነሣች ወይስ አልተነሣችም ፤ ወደ ሰማይ ዐረገች ወይንስ ዐላረገችም› ሳይሆን ‹በሰማይ የተደረገላት አቀባበል ምን ይመስል ይሆን?› ብለን ነው፡፡ ደሃው አልዓዛር በሞተ ጊዜ መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ከተባለ የአምላክን እናት ምን ያህል አጅበዋት ይሆን? ወደ ሰማይ ማረግ ለእርስዋ ቁምነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰማይን በእጆቹ የሚይዘውን አምላክ በእጆችዋ የያዘች ሁለተኛ ሰማይ ናት፡፡ እርስዋ ወደ ሰማይ በማረግዋም ዕድለኛዋ እርስዋ ሳትሆን ሰማዩ ነው፡፡ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ከእናትና ከዙፋን እናት ትበልጣለች፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አልወለደውም ፣ አላሳደገውም ፣ አላጠባውም
44 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:25:47 ††† እንኳን ለቅዱሳት አንስት ኄራኒ ሰማዕት: ንግሥተ ሳባ እና ንግሥት ዕሌኒ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅድስት ኄራኒ ሐዋርያዊት ሰማዕት †††

††† ይህቺ ቅድስት ወጣት መልክ ከደም ግባት: ምግባር ከሃይማኖት: ስም ከመልካምነት የተባበረላት ሰማዕት ናት:: #ኄራኒ ማለት "ሰላማዊት: የተወደደች" ማለት ነው:: አንድም በጥሬው "ሰላምና ፍቅር" ማለት ነው::

ቅድስት ኄራኒ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ እስያ የንጉሥ #ሉክያኖስ ልጅ ናት:: ከተወለደች ጀምሮ ስለ ክርስትና ሰምታ አታውቅም:: ምክንያቱም አባቷ ጣዖት አምላኪ ከመሆኑ ባለፈ ክርስቲያኖችን ይቀጣ ስለ ነበር ነው::

ልጁን ማንም እንዳያገኛት ሲል ንጉሡ ለቅድስት ኄራኒ ቤተ መንግስት ሠራላት:: ማንም እንዳይገባ በዙሪያው 12 አጥር አጠረበት:: ጣዖቶቹን እንድታጥን አገልጋዮችንም ሾመላት::

ምናልባት አጥር ሰውን ሊከለክለው ይችላል:: #እግዚአብሔር ግን እግዚአብሔር ነውና ምንም አይከለክለውም:: ጌታ ደግሞ ይህቺን ወጣት ለወንጌል አገልግሎት ይፈልጋታል:: አንድ ቀን አባቷ: ልጁ ምሑር እንድትሆንለት አለ የተባለ ሽማግሌ ፈላስፋ ቀጠረላት::

ጥበበ እግዚአብሔር ማለት ይሔ ነው:: አባቷ ይሕ ሽማግሌ ማንን እንደሚያመልክ አልተረዳም:: አረጋዊው እጅግ የተዋጣለት ክርስቲያን ነው:: ግን ማንም አያውቅበትም:: አረጋዊው ቅድስት ኄራኒን ዝም ብሎ ሊሰብካት አልወደደም::

መጀመሪያ በስነ ምግባር አነጻት:: ቀጥሎ ግን "ጌታ ሆይ! ጐዳናህን ምራት" እያለ ይጸልይላት ገባ:: ጌታችን ልመናውን ሰምቶታልና ቅድስቷ አንድ ቀን ግሩም ራዕይን አየች::

እርሷ ለማዕድ ተቀምጣ ሳለ: የምሥራቅና የምዕራብ መስኮቶቿም ተከፍተው ሳሉ: በምሥራቁ መስኮት ነጭ ርግብ በአፏ የወይራ ዝንጣፊ (ቆጽለ ዘይት) ይዛ ገባችና ማዕዷ ላይ አኑራው ሔደች:: እርሷን ተከትሎ ደግሞ ንስር በአፉ አክሊል ይዞ ገብቶ ማዕዷ ላይ ጥሎት ሔደ::

በ3ኛው ግን ቁራ: እባብ በአፉ ይዞ በምዕራቡ መስኮት ገብቶ ማዕዷ ላይ ጥሎት ወጣ:: ቅድስት ኄራኒ ያየችው ራዕይ ቢጨንቃት ሽማግሌ መምሕሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::

እርሱም "ልጄ ሆይ! ለዘመናት ስጠብቀው የነበረ ምኞቴን ነው ጌታ ያሳየሽ:: የሕልምሽ ትርጉም እንዲህ ነው:- ነጭ ርግብ የመንፈስ ቅዱስ (የሃይማኖት) ምሳሌ ናት:: የወይራ ዝንጣፊው ደግሞ #ማሕተመ_ጥምቀት( #ሜሮን) ነው:: ቁራ የክፉ ነገሥታት ምሳሌ ሲሆን እባብ የመከራ ምሳሌ ነው::

ንስር ድል የመንሳት ምልክት ሲሆን አክሊል ደግሞ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ነው:: ልጄ! ክርስቲያን ሆነሽ የሚደርስብሽን ሁሉ ጌታ አሳይቶሻል" ብሎ ተርጉሞላት ተሰናበታት::

እርሷም ወደ ምሥራቅ ዙራ ጸለየች:- "የማላውቅህ አምላክ ሆይ! ወደ እውነትህ ምራኝ" ስትል ለመነች:: በዚያች ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ አጽናናት:: የሚያጠምቃትም እንደሚልክላት ነገራት::

በዚያን ጊዜ አባቷ ገብቶ "ልጄ! ከመሣፍንቱ ላንዱ ልድርሽ ስለሆነ ምን ትያለሽ?" አላት:: "3 ቀን ስጠኝ" አለችውና ሰጣት:: ወደ ጣዖቶቹ ዕለቱኑ ወርዳ "ላግባ ወይስ ይቅርብኝ?" አለቻቸው:: ከቀድሞም በወርቅ የተለበጡ ድንጋዮች ናቸውና ዝም አሉ:: በሙሉ ቀጥቅጣ ሰባብራቸው ተመለሰች::

በዘመኑ #ቅዱሳን_ሐዋርያት(በተለይ እነ #ቅዱስ_ዻውሎስ) በሕይወተ ሥጋ ነበሩና ከቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ቤቷ እንደ ተዘጋ ገባ:: ክርስትናን ከጥንቱ እስከ ተፍጻሜቱ አስተምሮ አጠመቃት::

በ3ኛው ቀን አባቷ "ምን መከርሽ?" ቢላት "የእኔ ምክር #መርዓተ_ክርስቶስ(ሰማያዊ ሙሽራ) መሆን ነው" አለችው:: አባቷ ደነገጠ:: እጅግ ስለ ተናደደ ወደ አደባባይ አውጥቶ: አስሮ መሬት ላይ ጣላትና በመቶ የሚቆጠሩ ፈረሶች እንዲረግጧት አደረገ::

በወቅቱ ሰው የሚጠብቀው የአካሏን ቁርጥራጭ ነበር:: ነገር ግን ጌታ ከእርሷ ጋር ነበርና ልብሷ እንኩዋ ጭቃ አልነካም:: አባቷ ንጉሥ ሉክያኖስና ሠራዊቱ ያዩትን ማመን አልቻሉም:: ሁሉም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው "ከክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" አሉ:: ቅድስት ኄራኒ ምንም ሳትናገር ይህንን ሁሉ ሰው ማረከች::

ወዲያውም ንጉሡ መልእክተኛ ልኮ: የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙርን አስጠርቶ: ከነ ቤተሰቦቹ ተጠመቀ:: የዚህን ዓለም ክብር ንቆም ንግሥናውን ተወ:: የጸሎት ሰውም ሆነ:: የቅድስት ኄራኒ ተጋድሎ ግን ቀጠለ::

በአካባቢው የነበረ ንጉሥ መጥቶ የአባቷን መንግስት ቀማ:: እርሷንም እጅግ አሰቃያት:: እርሱ አልፎ አርማንዮስ የሚባል ንጉሥ እንዲሁ አሰቃያት:: እርሱም አለፈ:: ከእርሱ ቀጥሎ የመጣው ንጉሥ ብዙ መከራዎችን በእርሷ ላይ አደረሰ:: በጦርም ጐኗን ወግቶ ገደላት::

ከጥቂት ሰዓታት በሁዋላ ግን ልክ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ተነስታ ጠራችው:: በጣም ደንግጦ "አምላክሽ አምላኬ ነው" ሲል አመነ:: ከ30,000 በላይ ሠራዊቱን ይዞም ተጠመቀ::

ቅድስት ኄራኒ በቀረ ሕይወቷ በስብከተ ወንጌል እስያን አድርሳለች:: ጌታ አብርቶላት: እርሷም አብርታ: እልፍ ፍሬን አፍርታ: በዚህች ቀን ዐርፋለች:: የሐዋርያትንም: የሰማዕታትንም አክሊል ተቀዳጅታለች::

††† ንግሥተ ሳባ †††

††† ይሕቺ ኢትዮዽያዊት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት:: በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ #የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ #ኢየሩሳሌም ተጉዛለች::

ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች:: ድንግልናዋን ለታላቁ #ንጉሥ_ሰሎሞን ሰጥታ #ምኒልክን ወልዳለች:: ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች:: (ማቴ. 12:42) በስምም " #ሳባ: #አዜብና #ማክዳ ተብላ ትታወቃለች:: ዛሬ ዕለተ ልደቷ ነው::

††† ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት †††

††† ይሕቺ ቅድስት የቅዱስ #ቆስጠንጢኖስ እናቱ: የመስቀሉ ወዳጅ: የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ የሆነች ክብርት እናት ናት:: ይህቺም ቅድስት የተወለደቺው በዚሁ ዕለት ነው::

††† የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ እህት እናቶቻችንን ከክፋትም: ከጥፋትም: ይሠውርልን:: ለሃገርም: ለሃይማኖትም የሚጠቅሙ ሴቶችንም ጌታ አይንሳን:: በረከታቸውም ይደርብን::

††† ነሐሴ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (6ኛ ቀን)
2.ቅድስት ኄራኒ ሐዋርያዊት (ሰማዕት)
3.ቡርክት ንግሥተ ሳባ (ልደቷ)
4.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት (ልደቷ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

††† " #ንግሥተ_አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትፈርድበታለች:: የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና:: እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ::" †††
(ማቴ. 12:42)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
77 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:51:36 “በምድር ላይ የምንቆየው የዕድሜ ልክ ቆይታ በዘላለማዊው ሕይወት ካለው የዓይን ጥቅሻ አፍታ ጋር እንክዋን እኩል አይሆንም:: የዚህ ምድር ቆይታ እንግዲህ ለዚያኛው የሚያበቃን ነው" አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ



"እመቤቴ ሆይ በአንቺ ጸሎት በልጅሽ ቸርነት ከታመንሁ ሰማይ ወፍጮ ምድር መጅ ቢሆኑ ሁለቱም ሊያጠፉኝ ቢፈልጉ አንዳች ሊያደርጉኝ አይችሉም" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ



"ሰዎች የተራሮችን ከፍታ የባሕርን ሞገድ የወንዞችን ረዥም ፍሰት : ለማድነቅ ወደ ብዙ ሀገራት ይጉዋዛሉ : የከዋክብትን ውበትም ያደንቃሉ:: አንድን አስደናቂ ፍጥረት ግን ቸል ብለው ያልፉታል : ይህ ድንቅ ፍጥረት የሰው ልጅ ነው::" ቅዱስ አውግስጢኖስ



አንድን አባት ሰዎች መጡና "ዘወትር ጸሎት በማድረግህ በሕይወትህ ላይ የጨመረልህን ነገር ንገረን?" አሉት:: እርሱ ግን "ጸሎት በማድረጌ ከጨመርሁት ይልቅ የቀነስሁት ይበዛልና እርሱን ልንገራችሁ:: ጸሎት በማድረጌ ከሕይወቴ ውስጥ ጭንቀት ፍርሃት ተስፋ መቁረጥና ቁጡነትን ቀንሻለሁ አላቸው::



የትንሣኤ ሰሞን ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ ብሎ ሰላምታ መለዋወጥ በኦርቶዶክሱ ዓለም እጅግ የተለመደ ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ግን ይህንን ዓመታዊ ሰላምታ የዘወትር አድርጎ ወደ እርሱ የመጣን ሰው ሁሉ በፈገግታ"ክርስቶስ ተነሣ" ብሎ ያበሥር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 5 2011 ዓ ም
አዲስ አበባ
130 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:50:50 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ነሐሴ ፲፰ ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለሊቁ #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +"+ #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ_ሊቅ +"+ =>ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ (የተወለደባት) #ግብጽ ናት:: የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን በምግባሩ: በትምሕርቱ ለምዕመናን ጥቅም ሆኗቸዋል::…
131 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:50:31 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ነሐሴ ፲፰ ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለሊቁ #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ_ሊቅ +"+

=>ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ
(የተወለደባት) #ግብጽ ናት:: የተወለደው በ3ኛው መቶ
ክ/ዘመን ሲሆን በምግባሩ: በትምሕርቱ ለምዕመናን
ጥቅም ሆኗቸዋል:: ቅዱስ እለእስክንድሮስ ገና ልጅ ሳለ
ምሥጢረ ክርስትናን ይማር ዘንድ ወደ #ቅዱስ_ዼጥሮስ
#ተፍጻሜተ_ሰማዕት ሔዷል::

+ቅዱስ ዼጥሮስ የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክና ሊቅ ሲሆን
በታሪክ የዘመነ ሰማዕታት መጨረሻ ተብሎ ይታወቃል::
ከዚህ ሰማዕት ሥር የሚማሩ ብዙ አርድእት ቢኖሩም 3ቱ
ግን ተጠቃሽ ነበሩ::
1.ቅዱስ እለእስክንድሮስ (ደጉ)
2.አኪላስ (ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ)
3.አርዮስ (የቤተ ክርስቲያን ጠላት)

+ከእነዚህም አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ሲታትር
ነበር:: አኪላስ ደግሞ ሆዱ ዘመዱ: ስለ ምንም
የማይጨንቀው ሰው ነበር:: ቅዱስ እለእስክንድሮስ ግን
በጾምና በጸሎት እየተጋ መምሕሩን ቅዱስ ዼጥሮስን
ለመተካት (ለመምሰል) ይጥር ነበር::

+ወቅቱ ዘመነ ሰማዕታት እንደ መሆኑ ቅዱሱ ከመምሕሩ
ጋር ብዙ ነገሮችን አሳልፏል:: አርዮስ ክዶ: ቅዱስ
ዼጥሮስ ካወገዘው በሁዋላ እንደ ባልንጀራ ገስጾ
ሊመልሰውም ሞክሮ ነበር:: ነገር ግን የአርዮስን ክፋት
ከጌታ ዘንድ የተረዳው ቅዱስ ዼጥሮስ ደቀ መዝሙሩን
እለእስክንድሮስን ጠርቶ መከረው::

+"እኔ ከሞትኩ በሁዋላ አኪላስ ይተካል:: ከአርዮስ ጋር
ስለሚወዳጅ በ6 ወሩ ይቀሠፋል:: አንተ ግን ከአርዮስ
መርዝ ተጠበቅ" አለው:: ይህንን ካለው በሁዋላ
ወታደሮች የቅዱስ ዼጥሮስን አንገት ቆረጡ:: ይህ
የተደረገውም እ.ኤ.አ በ311 ዓ/ም ነው::

+ወዲያውም አኪላስ ተሾመ:: እንደ ተባለውም ከአርዮስ
ጋር ስለተወዳጀ በ6 ወሩ ተቀሰፈ:: በዚያው ዓመትም
ቅዱስ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ (ግብጽ) 19ኛ
ፓትርያርክ (ሊቀ ዻዻሳት) ሆኖ ተሾመ::

+ሊቁ ሲሾም መልካም አጋጣሚ የነበረው ያ የመከራ
ዘመን ማለፉ ሲሆን በጣም ከባዱ ግን የአርዮስ
ተከታዮች ከተገመተው በላይ መበብዛታቸው ነው::
ቅዱሱ ሊቅ በዽዽስና መንበሩ ለ17 ዓመታት ሲቆይ
ዕንቅልፍም ሆነ ዕረፍት አልነበረውም::

+በዚህ እየጾመ: እየጸለየ: ሥጋውን እየጐሰመ ለፈጣሪው
ይገዛል:: በዚያ ደግሞ ሕዝቡን ነጋ መሸ ሳይል
ያስተምራል:: ምዕመናንን ከአርዮስ የኑፋቄ መርዝ
ለመታደግ ባፍም: በመጣፍም (በደብዳቤ) አስተማረ::

+ብርሃን የሆነ ደቀ መዝሙሩ #ቅዱስ_አትናቴዎስ
እያገዘው: አርዮስን ከነአበጋዞቹ አሳፈሩት:: ለእያንዳንዷ
የኑፋቄ ጥያቄ ተገቢውን መንፈሳዊ ምላሽ ከመስጠቱ
ባለፈ አርዮስን ከአንዴም 2: 3ቴ በጉባኤ አውግዞታል::

+ነገሩ ግን በዚህ መቁዋጨት ባለመቻሉ ንጉሡ ቅዱስ
ቆስጠንጢኖስ ጉባኤ ኒቅያ እንዲደረግ አዋጅ ነገረ::
እ.ኤ.አ በ325 ዓ/ም (በእኛ በ318 ዓ/ም) ከመላው
ዓለም ለጉዳዩ 2,348 የሚያህሉ ሰዎች ተሰበሰቡ::
ከእነዚህ መካከል 318ቱ ሊቅነትን ከቅድስና የደረቡ: ስለ
ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ያሳለፉ ነበሩ::

+ይህንን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲመራ ደግሞ መንፈስ
ቅዱስ ቅዱስ እለአእስክንድሮስን መረጠ:: ሊቁም አበው
ቅዱሳንን አስተባብሮ በሺህ የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉትን
አርዮስን ተከራክሮ ረታው::

+በጉባኤው መጨረሻ አርዮስ "አልመለስም" በማለቱ
እርሱን አውግዘው: ጸሎተ ሃይማኖትን ሠርተው: 20
ቀኖናወችን አውጥተው: መጽሐፈ ቅዳሴ ደርሰው:
አሥራው መጻሕፍትን ወስነው: ቤተ ክርስቲያንን በዓለት
ላይ አጽንተው ተለያይተዋል::
የዚህ ሁሉ ፍሬ አበጋዙ ደግሞ ቅዱስ እለእስክንድሮስ
ነው::

+እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "#ወልድ_ዋሕድ:
#አምላክ: #ወልደ_አምላክ: #የባሕርይ_አምላክ"
መሆኑን መስክሮ ክብርን አግኝቷል:: የእምነታችንም
መሠረቱ ይሔው ነው:: ክርስቶስን "ፈጣሬ ሰማያት
ወምድር: የባሕርይ አምላክ: ዘዕሩይ ምስለ አብ
በመለኮቱ (ከአባቱ ጋር በመለኮቱ የሚተካከል)" ብለው
ካላመኑ እንኩዋን ድኅነት ክርስትናም አይኖርም::

+ከጉባኤ #ኒቅያ በሁዋላ ቅዱስ እለእስክንድሮስ
በመልካሙ ጐዳና ሲጋደል: ምዕመናንንም ሲያጸና ኑሯል::
ዘወትር ወንጌልን በፍቅር ያነብ ነበርና ሲጸልይ የብርሃን
ምሰሶ ይወርድለት ነበር::

+ስለ ውለታውም #ቤተ_ክርስቲያን በግብጽ ካበሩ 5ቱ
#ከዋክብት_ሊቃውንት እንደ አንዱ ታከብረዋለች:: ቅዱሱ
ሊቅ በ328 ዓ/ም (በእኛ በ320 ዓ/ም) በዚህች ቀን
ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::

=>ቸር አምላከ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን ከነጣቂ ተኩላ
ይጠብቅልን:: ከቅዱሱ ሊቅም በረከትን ይክፈለን::

=>ነሐሴ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (3ኛ ቀን)
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ዲያቆን
4.አባ ዘክርስቶስ ዘወሎ (ኢትዮዽያዊ ጻድቅ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)

=>+"+ . . . ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ
ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩአችሁ እጽፍላችሁ
ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: +"+ (ይሁዳ. 1:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
138 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 00:18:13 ††† እንኳን ለሰማዕታት ቅዱስ እንጣዎስ እና ቅዱስ ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ እንጣዎስ አሞራዊ †††

††† ይሕ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን የሚጠላ አስቸጋሪ አረማዊ ነበር:: ሃገሩ #ሶርያ( #ደማስቆ) ሲሆን ግብሩ ጣዖት ማምለክና መስረቅ ነበር:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይም ግፍን ፈጽሟል:: በሥጋዊ ጉልበቱ ኃይለኛ ስለ ነበር የተፈራ ነው::

ሁልጊዜ በጠዋት ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ይሔዳል:: የሚሔደው ግን ንዋያተ ቅድሳትን ለመዝረፍ: አንድም ካህናትን ለመደብደብ ነበር:: የሚገርመው ግን የወቅቱ ምዕመናንና ካህናት ይህን ሁሉ እያደረገባቸው አይጠሉትም:: ይልቁኑ ይጸልዩለት ነበር እንጂ:: ምክንያቱም ክርስትና ማለት ጠላትን መውደድ ነውና:: (ማቴ. 7)

የእግዚአብሔር ትዕግስትና የምዕመናን ጸሎት ተደምሮው አንድ ቀን ፍሬ አፈራ:: እንጣዎስ እንደ ለመደው ለክፉ ሥራ ወደ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ይሔዳል:: ከዚያም እንደ ደረሰ ወደ ውስጥ ገብቶ: የሚማታውን ተማቶ: የሚዘርፈውንም ዘርፎ: የተረፉትን ንዋያተ ቅድሳት በእሳት አቃጠላቸው::

#እግዚአብሔር ከዚህም በላይ ታጋሽ ነውና አላጠፋውም:: "ዘኢይፈቅድ ለኃጥእ ሞቶ" እንዲል የኃጢአተኛውን መመለስ እንጂ መሞቱን አይፈልግም:: ለዚያም ነው ዛሬ ይሔ ሁሉ ግፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተሠራ እግዚአብሔር እንደማያይ ዝም የሚለው:: ለሁሉም ቀን አለውና በፈረደ ቀን ግን በፊቱ የሚቆም አይኖርም::

እንጣዎስ ግን የሠራውን ሠርቶ እወጣለሁ ሲል አልተሳካለትም:: ከበሩ አካባቢ ሲደርስ: ከወደ ሰማይ አካባቢ ድምጽ ሰምቶ ቀና ሲል መላእክት እንደሱ ዓይነት ኃጢአተኞችን አሰልፈው በጦርና በቀስት ሲወጉአቸው ተመለከተ::

ድንገት ግን ከመላእክቱ አንዱ ዘወር ብሎ አንድ ቀስት ወደ እንጣዎስ ወረወረ (ተኮሰ):: ቀስቷ አካሉ ውስጥ ገብታለችና እንጣዎስ መሬት ላይ ወድቆ ለሞት ደረሰ:: ላበቱ በግንባሩ ላይ በጭንቅ እየፈሰሰ ጮኸ::

"ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ማረኝ? ራራልኝ? ይቅር በለኝ? በድፍረት ባለ ማወቅም በድየሃለሁ:: ይቅር በለኝና ላምልክህ: ስምህንም ልሸከም" ሲል በጭንቀት ውስጥ ሆኖ አሰምቶ ጸለየ:: በዚያ የነበሩ ምዕመናን ማን: በምን እንደ ወጋው ባያውቁም ባዩት ነገር ግን እጅግ ደስ አላቸው:: እነርሱም የፈለጉትና የጸለዩለት ነገር ይሔው ነበርና::

ወዲያው ግን እንጣዎስ ከሞት ጫፍ ተመልሶ ተነሳ:: መጀመሪያ በቦታው የነበሩ ካህናትና ምዕመናንን "ይቅር በሉኝ?" አለ:: ቀጥሎም ወደ ዻዻስ ዘንድ ሔዶ "አጥምቀኝ" ሲል ጠየቀ:: እርሱ በሚጠመቅበት ቀን ብዙ አሕዛብና ክርስቲያኖች ተሰብስበው ነበር::

እርሱ በከተማዋ ዝነኛ ነበር:: ሥርዓቱ ሁሉ ተደርሶ ቅዱሱ ወደ ውሃ ገንዳው ሲገባ ሁሉ እያዩ የብርሃን ምሰሶ ከሰማይ ወረደ:: ይህንን በገሃድ የተመለከቱ ከ10,000 በላይ አሕዛብ ወዲያውኑ በክርስቶስ አምነው አብረውት ተጠምቀዋል::

ቅዱስ እንጣዎስ ከዚህ በሁዋላ ምስጉን ክርስቲያን ሆነ:: ስለ ቀደመ ሕይወቱ ፈንታ ጾምን: ጸሎትን: ፍቅርን: ምጽዋትን ገንዘብ አደረገ:: ሕይወቱም ለብዙ ሰዎች መስታውት ሆነ:: #እመቤታችን ድንግል ማርያምንም ይወዳት ነበርና ወደ ቅዱሳን ማሕበር ( #ኢየሩሳሌም) ወስዳው በሥጋዊ አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይቻል ምሥጢርን ገልጣለታለች::

እነዚህን የቅድስና ጊዜያት በስኬት ያሳለፈው ቅዱስ እንጣዎስ መጨረሻው ሰማዕትነት ሆነ::
አረማውያን ወገኖቹና ቀድሞ የሚያውቁት ወደ ቀደመ ክፋትና ክህደት እንዲመለስ ጠየቁት:: "አይሆንም" አላቸው:: በአደባባይ ለፍርድ አቅርበው ደሙ እስኪፈስ ገረፉት::

ጥርሶቹን በሙሉ በድንጋይ አረገፏቸው:: ደሙና ጥርሶቹ መሬት ላይ ተዘሩ:: ነገር ግን ይሕ ስቃይ ቅዱሱን ከፍቅረ ክርስቶስ ሊለየው አልቻለም:: አሕዛብም ተስፋ ቆርጠው በዚህች ቀን ገድለውታል:: ቅዱስ እንጣዎስም ከሁዋለኛው ዘመን #ሰማዕታት እንደ አንዱ ተቆጥሯል::

††† ቅዱስ ያዕቆብ ግብጻዊ †††

††† ቅዱስ ያዕቆብ ተወልዶ ያደገው #መኑፍ (ግብጽ) ውስጥ ሲሆን ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ የተባረኩ ናቸውና እርሱ ሳይወለድ የነበሯቸውን 3 ሴቶች ልጆች "ተማሩ" ብለው ወደ ገዳም ቢያስገቧቸው በዚያው መንነው ቀሩባቸው::

በዚህ ሲያዝኑ #ቅዱስ_ያዕቆብ ተወልዶላቸዋል:: እነርሱም በቃለ እግዚአብሔርና በጥበብ አሳድገውታል:: ትንሽ ከፍ ሲል በአካባቢው ከነበረ አንድ ቅዱስ ሽማግሌ ጋር ተደብቀው ገድልን ይሠሩ ነበር:: ሁሌም መልካም ምግባራትን ከመፈጸም ባለፈ ሙሉውን ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ይጸልዩ ነበር::

ዘመነ ሰማዕታት በመጣ ጊዜም 2ቱ ተመካክረው ስመ ክርስቶስን በገሃድ ሰብከዋል:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱን ሽማግሌ ወዲያው ሲገድሉት ቅዱስ ያዕቆብን ግን ብዙ አሰቃይተውታል:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀብሏል::

††† አምላከ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ያሳትፈን::

††† ነሐሴ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል
2.ቅዱስ እንጣዎስ አሞራዊ (ሰማዕት)
3.ቅዱስ ያዕቆብ ግብጻዊ (ሰማዕት)
4.ቅዱስ አክራጥስ ሰማዕት
5.አባ እለእስክንድሮስ ዘቁስጥንጥንያ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

††† "ኃጢአተኞችን ሊያድን #ክርስቶስ_ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ::" †††
(1ጢሞ. 1:15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
126 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:37:17 +እመቤታችንንና ልጇን "አምጣ" ቢለው "አልናገርም"
አለው:: በዚህ ምክንያት አካሉን ከብዙ ቆራርጦ ገድሎታል::
በቤተ ክርስቲያን ታሪክም #ስለ_እመ_አምላክ_ፍቅር
የተሰዋ የመጀመሪያው ሰው ተብሎ ይታወቃል:: ጌታም
ስለ ሃይማኖቱ: ፍቅሩና ሰማዕትነቱ 3 አክሊላትን
ሰጥቶታል::=>አምላከ ቅዱሳን ከድንግል እመ ብርሃን ፍቅር:
ከጣዕሟ: ከረድኤቷ ያድለን:: የወዳጆቿን (ጊጋርና
ጊዮርጊስን) በረከትም ያብዛልን::

=>ነሐሴ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም (ፍልሠቷ:
ትንሳኤዋና ዕርገቷ)
2.ቅዱሳን ሐዋርያት
3.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ፍልሠቱ)
4.ቅዱስ ጊጋር ሶርያዊ (ሰማዕት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/
ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)

=>+"+ ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን::
እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን::
አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ::
አንተና #የመቅደስህ_ታቦት::
ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ::
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው::
ስለ ባሪያህ ስለ #ዳዊት . . ." (መዝ. 131:7)

=>+"+ ወዳጄ ሆይ! ተነሺ::
ውበቴ ሆይ! ነዪ::
በዓለት: በንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ!
ቃልሽ መልካም: ውበትሽም ያማረ ነውና:
መልክሽን አሳዪኝ::
ድምጽሽንም አሰሚኝ:: +"+ (መኃ. 2:13)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
161 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:36:54 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ነሐሴ ፲፮ ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለእመቤታችን
#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሳኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ # ዕርገተ_ድንግል_ማርያም +"+

=>ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም
የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል
እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ:
እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::

¤ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት
#እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

¤ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና
መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ
"እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500
ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ #ንጽሕት_ዘር
ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
¤ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና
ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን
ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም
መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ
እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::

+"+ የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ +"+

*ከአዳም በሴት
*ከያሬድ በሔኖክ
*ከኖኅ በሴም
*ከአብርሃም በይስሐቅ
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
*ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ
ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

¤ከሌዊ ደግሞ #በአሮን: #አልዓዛር: #ፊንሐስ:
#ቴክታና_በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

¤አባታችን #አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት
#ወላዲተ_አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት
ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ
#ኢያቄም_ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ::
(#ቅዱስ_ቴዎዶጦስ_ዘዕንቆራ)

¤ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ
#ቤተ_መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12
ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና
እያገለገለች: እርሷን ደግሞ #መላእክተ_ብርሃን
እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ
እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ
#አረጋዊ_ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

¤በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና
ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው::
ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር:
ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ::
(#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም #ለብሐዊ)

¤ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ:
እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14)
"#ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለ2
ዓመታት ቆዩ::

¤አርዌ ሔሮድስ "እገድላለሁ" ብሎ በተሳበት ወቅትም
ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም:
በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ
#ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር
ሲሆነው: ለርሷ ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር
ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

¤በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን
እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች::

እርሷ 45 ዓመት: ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን
ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3
ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም
እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

¤የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም
የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን
ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ
በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች::
ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

¤ከልጇ #ዕርገት በሁዋላ #በጽርሐ_ጽዮን ሐዋርያትን
ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮን
ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች::
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ:
ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና:
ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

¤ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን #መድኃኒታችን
አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን
ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም
በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት
ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ:
ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል::

¤ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም
እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው
ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

¤በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ
#ቅዱስ_ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ
እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር
አኑሯታል::

በዚያም #መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት
ቆይታለች::

¤#ቅዱስ_ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን
ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ
ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል
ማርያምን #ንጹሕ_ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም
#በጌሴማኒ ቀብረዋታል::

¤በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ #ትንሳኤ
ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ
#ቅዱስ_ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም
መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ
1 ቀን ሱባኤ ገቡ::

¤ለ2 ሳምንታት ቆይተው: በዚህች ቀንም ሁሉንም ወደ
ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ
የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ
ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን
ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ #ደብረ_ዘይት
ተመልሰዋል::

=>ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና #እመቤታችን:
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን:
ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::

+"+ # ቅዱስ_ጊጋር_ሶርያዊ +"+

=>ይሕ ቅዱስ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን የሶርያ
መስፍን የነበረ ሲሆን #ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ
ሰምቷል:: እመ ብርሃን ለስደት ስትወጣ በመጀመሪያ
የሔደችው ወደ #ሊባኖስ ተራሮች ነው::
#መስፍኑ_ጊጋር ነበርና እርሱም የአምላክ እናትነቷን
አምኖ አክብሮ አስተናግዷታል::

+ሔሮድስም ይሕንን ሲሰማ ጦር አስከትቶ ወደ ጊጋር
ሔደ:: መስፍኑ ጊጋር ሔሮድስን እንደማይችለው ሲረዳ
ድንግል ማርያምን ወደ #ግብጽ ሸሽጐ አሸሻት::
ሔሮድስንም ፊት ለፊት ተገናኘው:: ከአቅሙ በላይ
ስለነበረም በወታደሮች ተማርኮ ወደ ሔሮድስ ቀረበ::
120 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ