Get Mystery Box with random crypto!

ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahberetsion — ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahberetsion — ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን
የሰርጥ አድራሻ: @mahberetsion
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.85K
የሰርጥ መግለጫ

ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን:
✍የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ
✍ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መዝሙራት
✍ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች
✍ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ
✍ ወቅታዊ መረጃዎችና ሌሎችንም የሚያገኙበት ቻናል
➾ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Hailegebereal19አድርሱን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-22 07:36:34 ✞✞✞ እንኳን ለንጹሐት እናቶቻችን ቅድስት እንባ መሪና እና ቅድስት ክርስጢና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞

✞✞✞ ቅድስት እንባ መሪና ✞✞✞

✞✞✞ ቤተ ክርስቲያን "እንቁዎቼ" ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ቅድስት እንባ መሪና ናት:: ጣዕመ ዜናዋ: ሙሉ ሕይወቷ: አስገራሚም: አስተማሪም ነው:: ቅድስቷ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ናት:: ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸውም ደግና ቅን ነበሩ::

ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ "መሪና" ነው:: ምክንያቱም "እንባ መሪና" የወንድ ስም ነውና:: ነገር ግን በወንድ ስም የተጠራችበት የራሱ ታሪክ አለውና እርሱን እንመለከታለን::

ቅድስት መሪና ገና ልጅ ሳለች እናቷ ማርያም ሞተችባት:: ደግ አባት አንድ ልጁን በሥጋዊም: በመንፈሳዊም ሳያጐድልባት አሳደጋት:: ዕድሜዋ አሥራ አምስት ዓመት በሆነ ጊዜ ወደ ፊቱ አቅርቦ "ልጄ! እኔ ወደ ገዳም ስለምሔድ አንቺን መልካም ባል ላጋባሽ::" አላት::

ቅድስት መሪናም "ነፍሰ ዚአከ ታድኅን: ነፍሰ ዚአየኑ ታጠፍእ - የአንተን ነፍስ አድነህ እንዴት የእኔን ትተዋታለህ? እኔም እመንናለሁ::" አለችው:: አባቷ የተናገረችው ከልቧ እንደሆነ ሲያውቅ "ልጄ! ገዳም ሁሉ በአካባቢው የወንድ ብቻ ነውና ስሚኝ::" አላት::

እርሷ ግን "አባቴ! ግዴለህም: ስሜን እንደ ወንድ ቀይረህ: አለባበሴንም ለውጥ::" አለችው:: (እንደ ወንድ ለበሰች ማለት ግን እንደ ዘመኑ ዓይነት እንዳይመስላችሁ አደራ!)

ከዚያ አባትና ልጅ ሃብት ንብረታቸውን ሸጠው ለነዳያን አካፈሉ:: በፍጹም ልባቸውም መነኑ:: በደረሱበት ገዳም ቅድስት መሪና በወንድ ስም "እንባ መሪና" በሚል ገባች:: ቀጣዩ ሥራዋ እንደ ወንዶች እኩል መስገድ: መጾምና መጸለይ ነበር::

ይህችን ቅድስት ልናደንቃት ግድ ይለናል:: ማንም በእርሷ አይፈተንም:: አያውቋትምና:: እርሷ ግን ወጣት ሆና: አንድም ሴት በሌለበት ገዳም ጸንቶ መቆየት በራሱ ልዩ ነው:: መልአካዊ ኃይልንም ይጠይቃል::

ተጋድሎዋ በጣም ስለ በዛ ወንድሞች መነኮሳት ይደነቁባት ነበር:: ጺም ስለሌላትና ድምጿ ቀጭን ስለሆነ አልተጠራጠሩም:: ምክንያቱም ጃንደረባ ናት ብለው አስበዋልና:: ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን አባቷ ታሞ ከማረፉ በፊት አበ ምኔቱን ጠርቶ "ወደ ከተማ ልጄን እንዳትልክብኝ: አደራ!" ብሎት ነበር::

ያም ሆኖ አንዳንድ መነኮሳት ቅሬታ በማንሳታቸው ወደ ከተማ ተላከች:: ችግሩ ለተልእኮ ባደሩበት ቤት አንድ ጐረምሳ ገብቶ የአሳዳሪውን ልጅ ከክብር አሳንሷት ሔደ:: ሲወጣም "ድንግልናሽን ያጠፋ ማን ነው? ካሉሽ ያ ወጣት መነኩሴ አባ እንባ መሪና ነው በይ::" አላት::

ከሦስት ወራት በኋላ የዚያች ዘማ ሴት ጽንስ በታወቀ ጊዜ ለአባቷ "አባ እንባ መሪና እንዲህ አደረገኝ::" አለችው::

አባት መጥቶ እየጮኸ መነኮሳትን ተሳደበ:: አበ ምኔቱ ግራ ተጋብቶ ቢጠይቀው "የአንተ ደቀ መዝሙር እንባ መሪና ልጄን ከክብር አሳነሳት::" አለው:: አበ ምኔቱ እውነት መስሎታልና ቅድስቲቱን ጠርቶ ቁጣና እርግማንን አወረደባት:: በዚያች ሰዓት ተንበርክካ አንድ ነገር ወሰነች::

"ሴት ነኝ" ብሎ መናገሩስ ቀላል ነው:: ግን ደግ ናትና የእነዛን አመጸኛ ሰዎች ኃጢአት ልትሸከም ወሰነች:: ቀና ብላ "ማሩኝ ወጣትነት ቢያስተኝ ነው?" አለቻቸው:: ተቆጥተው ዕለቱን እየገፉ ከገዳም አስወጧት:: ከባድ ቀኖናም ጫኑባት:: ከስድስት ወራት በኋላም የእርሷ ልጅ ነው የተባለ ሕፃን አምጥተው ሰጧት::

ይህኛው ግን ከባድ ፈተና ሆነባት:: እንዳታጠባው አካሏ በገድል ደርቁአል:: በዚያ ላይ ድንግል የሆነች ሴት ወተት የላትም:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: የበጋውን ሐሩር: የክረምቱን ቁር ራሷ ታግሣ ለሕፃኑ ከእረኞች ወተት እየለመነች: እየመገበች ሦስት ዓመታት አለፉ::

በዚህ ጊዜ ወደ ገዳሙ ከከባድ ቀኖና ጋር ተመለሰች:: ሕፃኑን ስታሳድግ: ለገዳሙ ስትላላክ: ምግብ ስታዘጋጅ: ውኃ ስትቀዳ: የእያንዳንዱን ቤት ስታጸዳ ሰላሳ ሰባት ዓመታት አለፉ:: ሕፃኑም አድጐ ደግ መናኝ ወጣው:: (የቅድስቷ እጆች ያሳደጉት የታደለ ነው::)

በመጨረሻ ቅድስት መሪና (እንባ መሪና) ታማ ዐረፈች:: እንገንዛለን ብለው ቢቀርቡ ሴት ናት:: እጅግ ደንግጠው አበ ምኔቱን ጠሩት:: በዙሪያዋ ከበው እንባቸውን አፈሰሱ:: ጸጸት እንደ እሳት በላቻቸው:: ሥጋዋን በክብር ገንዘው: በአጐበር ጋርደው: በራሳቸው ተሸክመው ምሕላ ገቡ::

ሙሉውን ቀን "ስለ ቅድስት መሪና ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን?" ሲሉ ዋሉ:: ድንገት ግን ከተባረከ ሥጋዋ "ይቅር ይበለን::" የሚል ድምጽን ሰምተው ደስ ብሏቸው ቀበሯት:: እነዚያ ዝሙተኞችም ከእርሷ ይቅርታን እስካገኙበት ቀን አብደው ኑረዋል::

✞✞✞ ቅድስት ክርስጢና (ክርስቲና) ሰማዕት ✞✞✞

✞✞✞ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን የተነሳችው ሰማዕቷ ቅድስት ክርስጢና ከዋና ሰማዕታት አንዷ ስትሆን በዓለማቀፍ ደረጃም ተወዳጅ ናት:: ከመነሻው የሃገረ ገዢ ልጅ ብትሆንም ቤተሰቦቿ ጣዖት አምላኪዎች ነበሩ:: አጥር አጥረው: በር ዘግተው: ከማንም ጋር ሳትገናኝ: ጣዖት እንድታጥን አደረጓት::

ወጣት በሆነች ጊዜ ግን ጣዖቱን ተመለከተችው: መረመረችው:: አምላክ እንዳልሆነም ተረዳች:: ወደ ምሥራቅ ዙራ "እውነተኛው አምላክ ራስህን ግለጽልኝ?" ስትል ጸለየች::
መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ክርስትናን በልቡናዋ አሳደረባት:: ቅዱስ መልአክም መጥቶ ሰማያዊ ሕብስትን መገባት::

ፈጥና ተነስታ አብርሃማዊት ቅድስት ጣዖታቱን ሰባበረች:: በዚህ አባቷ ተቆጥቶ (ርባኖስ ይባል) በዛንጅር (ሥጋን የሚልጥ: የሚቆርጥ ጀራፍ ነው::) አስገረፋት:: ንጽሕት ናትና ከአካሏ ደም ሳይሆን ጣፋጭ ማር ፈሰሰ::

በድጋሚ በእሳት ቢያቃጥላትም አልነካትም:: ድንገት ግን አባቷ ርባኖስ ተቀሰፈ:: ሌላ ንጉሥ መጥቶ በእሳትም: በስለትም አሰቃያት:: እሱንም መልዐክ ቀሠፈው:: ሦስተኛው ንጉሥ ግን ብዙ አሰቃይቶ: ጡቶቿንና ምላሷን አስቆረጣት:: በመጨረሻውም በዚህች ቀን ለእፉኝት (እባብ) አስነድፎ ገድሏታል::

✞✞✞ የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ ለእነርሱ የሰጣቸውን ጽናት አይንሳን:: ከበረከታቸውም አብዝቶና አትረፍርፎ ያድለን::

✞✞✞ ነሐሴ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት እንባ መሪና ገዳማዊት
2.ቅድስት ክርስጢና ሰማዕት
3.ቅዱስ ለውረንዮስ ሰማዕት
4.ሰላሳ ሺ ሰማዕታት (የቅድስት ክርስቲና ማኅበር)
5.አበው ቅዱሳን ሐዋርያት (ወላዲተ አምላክን ለመገነዝ በዚህ ዕለት ተሠብስበዋል::)

✞✞✞ ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)

✞✞✞ "ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ::" ✞✞✞
(፩ጴጥ. ፫፥፫)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
57 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:36:16 ✞✞✞ እንኳን ለጌታችን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞

✞✞✞ ቅዱስ ዕፀ መስቀል ✞✞✞

✞✞✞ የዕፀዋት ሁሉ ንጉሣቸው የሚሆን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ለእኛም ኃይላችን: ቤዛችን: መዳኛችን: የድል ምልክታችን ነው:: መስቀል በደመ ክርስቶስ ተቀድሷልና አንክሮ: ስግደት ክብርና ምስጋና በጸጋ ይገባዋል::

ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ ላለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: ከእነዚህ መካከልም አንዱን በዚህ ዕለት እናዘክራለን::
ታሪኩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በ400 ዓ/ም አካባቢ በግብፅ አባ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ሳለ: ቅዱስ ቄርሎስም በሊቀ ዲቁና ሲያገለግል ሳለ በእስክንድርያ ከተማ ሁለት ደሃ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የቀን ሠራተኞች በመሆናቸው ከዕለት ምግብ አይተርፋቸውም ነበር::

ከሁለቱ አንዱ ፍጹም አማኝ ሲሆን ሌላኛው ግን ተጠራጣሪ ነበር:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- በከተማዋ ብዙ ሃብታም አይሁድ ነበሩና እነሱን እየተመለከተ ነው:: ለእርሱ ክርስትና ማለት ገንዘብ መስሎታልና ዘወትር "ለምን ክርስቶስን እያመለክን ድሃ እንሆናለን?" እያለ ያማርር ነበር::

"ያዛቆነ ሰይጣን . . . " እንደሚባለው አንድ ቀን ባልጀራውን "ለምን ክርስቶስን አንክደውም? (ሎቱ ስብሐት!) እርሱን ከማምለክ የተረፈን ድህነት ብቻ ነው" አለው:: ባልንጀራው ሊመክረው ሞከረ:: "እግዚአብሔር አምላከ-ነዳያን ነው:: ቅዱሳን ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታትም በሥጋዊ ሃብት ነዳያን ነበሩ::" ብሎ ቢለውም ሰይጣን ሠልጥኖበታልና አልሰማውም::

ያ ስሑት ደሃ ወዲያው ወጥቶ ወደ ማኅበረ አይሁድ ሔደ:: እነርሱ በቁጥር ብዙ ሁነው በአንድነት ይኖሩ ነበር:: "ሥራ ቅጠሩኝ" አላቸው:: "በእምነት አትመስለንምና አይሆንም" አሉት:: ያን ጊዜ ለአለቃቸው (ፈለስኪኖስ) "አንተ ሥራ ቅጠረኝ እንጂ እኔ ክርስቶስን እክዳለሁ::" (ሎቱ ስብሐት!) አለው::

ወዲያው የከተማው ሕዝብ ተጠርቶ: በጉባኤ መካከል ሊያስክዱት ተዘጋጁ:: በፍጥነትም መስቀል: ጦር: ሐሞት አዘጋጁ:: ሥዕለ ስቅለቱንም አመጡ:: ያን ደሃ ከሃዲም "በል-ክርስቶስ ሆይ! ካድኩህ ብለህ ምራቅህን ትፋበት: ሐሞቱን አፍስበት: በጦርም ውጋው::" (ሎቱ ስብሐት!) አሉት::

ያ ልቡ የደነቆረ መስቀለ ክርስቶስ ላይ ተፋ:: ሐሞትም አፈሰሰበት:: በመጨረሻ በጦር ሲወጋው ግን ድንቅ ተአምር ተገለጠ:: በጦር ከተወጋው ከመስቀሉ ጐን ብዙ ደም ፈሰሰ:: ለረዥም ሰዓትም አላቋረጠም:: በዚህች ሰዓት በአካባቢው የነበሩ ሁሉም አይሁድ በግንባራቸው ተደፍተው ለክርስቶስና ቅዱስ መስቀሉ ሰገዱ::

ሁሉም በአንድነት "ክርስቶስ የአብርሃም አምላክ ነው:: መድኃኒትም ነው::" ሲሉ እየጮሁ ተናገሩ:: ባለማወቅ ስላደረጉት እነርሱ ምሕረትን ሲያገኙ ያ አዕምሮ የጐደለውን ደሃ ግን ዘወር ብለው ሲያዩት ወደ ድንጋይነት ተቀይሮ ነበር:: ነፍሱንም: ሥጋውንም በፈቃዱ አጠፋ::

የአይሁድ አለቃም ዓይነ ሥውር ዘመድ ነበረውና ወዲያው አምጥቶ ከደሙ ቢቀባው ዐይኑ በራ:: ታላቅ ደስታም በዚያ ሥፍራ ተደረገ:: ነገሩን የሰሙት ቅዱሳን ቴዎፍሎስ እና ቄርሎስ ሲመጡ ደሙ ከመፍሰስ አላቆመም ነበር::

በተአምሩ ደስ ተሰኝተው: ከደመ ክርስቶስ ለበረከት ተቀቡ:: የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ከነአፈሩ አንስተው: መስቀሉን በትከሻ ተሸክመው: በፍፁም እልልታና ዝማሬ ወስደው በቤተ መቅደስ አኑረውታል:: የከተማዋ ሁሉም አይሁድም በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል::

✞✞✞ ቅዱሳን ስምዖንና ዮሐንስ ✞✞✞

✞✞✞ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ አስደናቂ ታሪክ ካላቸው ጻድቃን እነዚህ ሁለቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ::
እርሱስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅዱሳኑ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ተወልደው ያደጉ ክርስቲያኖች ናቸው::

ዘመዳሞች ከመሆናቸው ባሻገር አብረው ስላደጉ እጅጉን ይፋቀሩ ነበር:: የዋሃንም ነበሩ:: ወጣት በሆኑ ጊዜ ትልቁ ዮሐንስ ሚስት አገባ:: ታዲያ አንድ ቀን ከጌታችን መቃብር ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ ገዳመ ዮርዳኖስ አካባቢ ደረሱ:: እርስ በእርሳቸውም "ይህ ገዳምኮ የመላእክት ማደሪያ ነው::" ተባባሉ::

በዚያውም መንነው ለመቅረት አሰቡ:: ፈረስና ንብረታቸውን ለዘመዶቻቸው ልከው ጸሎት አደረሱ:: ፈቃደ እግዚአብሔርን ሊረዱም ዕጣ ተጣጣሉ:: ዕጣውም "ወደ ገዳም ሒዱ" የሚል ስለሆነ ተቃቅፈው ደስ አላቸው::

ወደ ገዳሙ ሲደርሱም አበ ምኔቱ አባ ኒቅዮስ ፈጣሪ አዞት የገዳሙን በር ከፍቶ ጠበቃቸው:: ተቀብሎ ሲያስገባቸውም አንድ ደግ መነኮስ ሲያልፍ: ቆቡ ቦግ ቦግ እያለ እንደ ፋና ሲያበራ እና መላእክት ከበውት አዩ:: ወዲያውም አበ ምኔቱን "እባክህ አመንኩሰን" አሉት::

እርሱም የአምላክ ፈቃድ ነውና በማግስቱ አመነኮሳቸው:: ፍቅረ ክርስቶስ ገዝቷቸዋልና በጥቂት ዓመታት ተጋድሎ ከብቃት (ከጸጋ) ደረሱ:: ሁለቱም ቆመው በፍቅር ሲጸልዩ የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ይወርድ ነበር:: አካላቸውም በሌሊት ያበራ ነበር::

እንዲህ ባለ ቅድስና ለዓመታት ቆይተው ከገዳሙ ወደ ጽኑ በርሃ ሊሔዱ ስለ ፈለጉ የገዳሙ በር በራሱ ተከፈተ:: አበ ምኔቱ አባ ኒቆን (ኒቅዮስ) እያነባ በጸሎት ሸኛቸው:: በበርሃም በጠባቡ መንገድ: በቅድስና ተጠምደው ለሃያ ዘጠኝ ዓመታት ተጋደሉ:: በዚህ ሰዓት ግን ሁለቱን የሚለያይ ምክንያት ተፈጠረ::

እግዚአብሔር ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ እንዲገባ: ቅዱስ ዮሐንስ ግን በዚያው እንዲቆይ አዘዘ:: ሁለቱ ለረዥም ሰዓት ተቃቅፈው ተላቅሰው ተለያዩ:: ከሃምሳ ዓመታት በላይ ተለያይተው አያውቁም ነበርና::

ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ ሲገባ ክብሩን ይደብቅ ዘንድ እንደ እብድ ሆነ:: በዚህ ምክንያትም የወቅቱ ከተሜዎች ይንቁት: በጥፊም ይመቱት ነበር:: (እባካችሁ ብዙ በየመንገዱ የወደቁ አባቶች አሉና እንጠንቀቅ!) ቅዱሱ ግን ስለ እነርሱ ይጸልይ ነበር::

በከተማዋ የነበሩ እብዶችን ሁሉንም በተአምራት ፈወሳቸው:: አንድ ቀን ግን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ደብድበውት ደከመ:: የእግዚእብሔር መልአክ ወርዶ "ና ልውሰድህ" ብሎ ዮሐንስን ከበርሃ: ስምዖንን ከከተማ በዚህች ቀን ወሰዳቸው:: እነሆ ብርሃናቸው ዛሬም ድረስ ለሚያምንበት ሁሉ ያበራል::

✞✞✞ ቅዱስ ባስሊቆስ ሰማዕት ✞✞✞

✞✞✞ በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ከነበሩ ስመ ጥር ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ባስሊቆስ ነው:: ብዙ ጊዜ "ኃያሉ ሰማዕት" በመባልም ይጠራል:: ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በመከራ በቆየባቸው ዘመናት ሁሉ ከማመስገን በቀር ምግብ አይቀምስም ነበር::

"ለምን አትበላም?" ሲሉት "እኔ የአምላኬ ስሙና ፍቅሩ አጥግቦኛል::" ይላቸውም ነበር:: አሥረው በግድ ለጣዖት ሊያሰግዱት ወደ ቤተ ጣዖት ቢያስገቡት በጸሎቱ እሳት ከሰማይ ወርዳ አማልክቶቻቸውን በልታለች:: ተበሳጭተው ለቀናት የደረቀ ባላ ላይ አንጠልጥለው ቢገርፉት ደሙ ፈሰሰ::

የታሠረባት ደረቅ እንጨት ግን ለምልማ: አብባ: አፍርታ በርካቶች ተደንቀዋል:: ከበረከቱም ተሳትፈዋል:: ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ባስሊቆስ በዚህች ቀን ተከልሎ ጌታችንና መላእክቱ ወርደው ሲያሳርጉት ብዙ ሰው አይቶ አምኗል::
44 viewsⓋⓐⓣⓛⓚⓐⓝⓐ, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ