Get Mystery Box with random crypto!

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

የቴሌግራም ቻናል አርማ love_therapist — 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀
የቴሌግራም ቻናል አርማ love_therapist — 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀
የሰርጥ አድራሻ: @love_therapist
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.29K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ
✅ ጤና
✅ ስነ ልቦና
✅ ቤተሰብ
✅ ጓደኝነት
✅ የፍቅርና ወሲብ ጉዳዮች ላይ እንመካከራለን ።
የግለሰብ ችግር የማህበረሰብ ችግር ነው
የግለሰብ ጥያቄ የማህበረሰብ ጥያቄ ነው
ስለዚህ ጥያቄዎን ይዘው ይምጡና ለብዙሀን መልስ እና ማስተማሪያ ይሁኑ
ለማንኛውም ጥያቄ @therapist_100

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-11 16:46:34 አታምባርቅ

አንድ ጊዜ አባት ከቢሮ ድክም ብሎት ቤት ሲገባ ልጁ ሁለት ፖም ይዞ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ አባት ፈገግ አለና ልጁን አንዱን ፖም እንዲሰጠዉ ጠየቀዉ፡፡ ይህን የሰማዉ ልጅ ሁለቱንም ፖሞች አንድ አንዴ ገመጥ ገመጥ አደረጋቸዉ፡፡

በዚህ ጊዜ አባት ተቆጣ... “አንተ ሆዳም! እንደዚህ ይደረጋል! አንዱ አይበቃህምና ነዉ ሁለቱንም ለመብላት የምትጣደፈዉ...!” እያለ የንዴት መትረየሱን አርከፈከፈዉ፡፡

ልጅ አዝኖ እንዲህ አለ “አባዬ እኔኮ ሁለቱንም የገመጥኩት ከሁለቱ የትኛዉ በጣም እንደሚጣፍጥ ለማወቅ ነዉ ...ይሄ በጣም ይጣፍጣል...ስለዚህ እንካ ላንተ! እኔ የቀረዉን ልብላ' ብሎት ለአባቱ የሚጣፍጠዉን ፖም ሰጠዉ፡፡ አባት እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም፡፡

አንዳንዴ ነገሮች ምንም ሳይገቡን መጮህ፣ መናደድና መቆጣት እንፈልጋለን፡፡ አንድን ነገር ዉጤቱን ገምተን ከምንጀምር ቀረብ ብለን ከመሰረቱ ብንረዳ የበለጠ መልካም ነዉ፡፡

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
828 views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 11:16:01 ፈራጁ

አንድ በከባድ ወንጀል ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት የቀረበ ወንጀለኛ በጣም ጎበዝ ጠበቃ ነበረውና ተከራክሮለት ከቅጣት አዳነው ከእስርም ተፈቶ ኑሮውን ቀጠለ ፡፡

ከአመታት በኋላ ይኸው ልማደኛ ወንጀለኛ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ ያን ጊዜ ጠበቃው ሆኖ ተከራክሮ ነፃ ያወጣውን ሰው ግን አሁን ላይ ሊያድነው አልቻለም ምክንያቱም የዛኔው ጠበቃ አሁን ላይ ዳኛ ሆኗልና እናም በወንጀሉ ልክ ፈርዶ ቅጣቱን ሰጥቶታል ፡፡

ፈጣሪም በምድር ሳለን ምንም ያህል ብንበድል ብናጠፋ ጠበቃችን ሆኖ ከችግር ከመከራ ከአደጋ ከፈተና ይጠብቀናል ነገር ግን ጊዜያችን ደርሶ ወደማይቀረው ስንሄድ ግን ዳኛ ሁኖ ይጠብቀናል ፡፡

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
1.5K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 11:10:09 እድሜ

አንዲት በእድሜ የገፉ አሮጊት ሴት ወደ ባንክ ሄደው ከረጅም ወረፋ በኋላ ለሰራተኛው "10 ብር ማውጣት እፈልጋለሁ " ይሉታል ።

ሰራተኛውም ተናዶ “ከ100 ብር በታች ለሚወጣ ገንዘብ ኤቲኤም ይጠቀሙ ይላቸዋል ።

አሮጊቷ ሴት ለምን ብላ ጠየቀች ሰራተኛውም የባንኩ ህግ ነው ፣ እባክዎ ከኋላ ብዙ ደንበኞች ስላሉ ውጡ ብሎ ተቆጣ ።

አሮጊቷ ሴት ለሰከንዶች ያህል ዝም አሉ እና "እባክህ ያለኝን ገንዘብ በሙሉ አውጥተህ ስጠኝ " አሉት ።

ሰራተኛውም ሂሳባቸውን ሲያይ ደነገጠ እናም በአክብሮት "3,000,000,000 ብር በሂሳብዎት ውስጥ አለሽ ነገር ግን ባንኩ በአሁኑ ጊዜ በካሽ ያን ያህል ገንዘብ የለውም ። ቀጠሮ ይዘው ነገ መመለስ ይችላሉ " አላቸው ።

ሴትየዋም እና ምን ያህል ነው አሁን ማውጣት ምችለው ብለው ጠየቁ ።

ሰራተኛውም 300,000 ብር ማውጣት ይችላሉ አላቸው ።

"እሺ አሁን ይሰጠኝ " አሉት ። ሰራተኛውም በትህትና 300,000 ቆጥሮ በትህትና ሰጣቸው ።

ሴትየዋም ቦርሳቸውን ከፍተው 10 ቀንሰው ከተቱና ሌላው 299,990 ብር መልሼ ማስገባት እፈልጋለሁ አሉ ።

ለዕድሜ ባለፀጎች ትሁት እና ተባባሪ እንሁን ፣ የብዙ ዓመታት ልምድ አላቸው ።

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
1.4K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:55:25 ዝምታ

በህብረተሰዉ ዉስጥ ዋጋ የማይሰጠዉ ባህሪ ወይም ችሎታ ‘ዝምታ’ ይባላል፡፡

ሰዎች ሁሉ ሲያወሩ ነገሩን በዝምታ ስታልፍ

ሰዎች ሁሉ 'ኸረ ባክህ አዉራ?!' ብለዉ ሲለማመጡህ ዝም ስትል

ከራስህ ጋር የማይገናኝ የባጥ የቆጥ ወሬ ሰዎች ሲያወሩ ዝም ስትል

የራስህል የግል አስተያየት ለራስህ ስታቆየዉ

ስታወራ ድምፅህ ሰዎችን የሚረብሽ አይነት ቃና እያወጣ መሆኑን ስትረዳ

ሰዎች የሚሰሟቸዉን እንጂ የሚመልሱላቸዉን አድማጭ እንደማይፈልጉ ስትረዳ

ነገሮችን በጥሞና መከታተል እንጂ ሰዉ 'ትንፋሽ ወደ ዉስጥ በሳበ ቁጥር' ሺህ ቃላት ማዉጣት ድካም እንደሆነ ሲገባህ ዝም ጭጭ ትላለህ ።

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
1.8K views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 00:01:42 ቀናቶች
2.2K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 17:04:46 ባለህ ተደሰት

የሆነ እድሜ ስንደርስ ‘እርፍ እንላለን’ የሚል የተሳሳተ ሃሳብ ብዙዎቻችን ልብ ዉስጥ አለ ፡፡

ለምሳሌ “ልክ ሚስት አግብቼ እንትን መስሪያ ቤት ስገባ እርፍ እላለሁ፣ እንዲህ ሳደርግ እርፍ እላለሁ፡ ጭንቀቴ ይጠፋል ወዘተ...” እንላለን፡፡

አንድ ቀላል እዉነት አለ...በየትኛዉም እድሜ ላይ ብንሆን ሁሉን ነገር ማቅለል አይደለም ማሰብ እራሱ ይከብደናል፡፡

‘ይሄ ከተከናወነልኝ ደስተኛ እሆናለሁ’ ብለን መስፈርት ከሰጠን ደስተኛ የመሆን እድላችን ከጊዜ ወደጊዜ እየጠበበ ይሄዳል! ዛሬን፡ አሁን፡ እቺን ሰአት ባለን ነገር ደስታ እንፍጠርበት፡፡

ነገ እቅዶቻችን ሁሉ ቢሳኩ እንኳን ልክ ለመደሰት እቅድ ስንነድፍ ሌላ ሃሳብ፣ ሌላ ማነቆ፣ ሌላ ችግር እንፈጥራለን፡፡

ስለዚህ ዛሬን በጭንቀት ከመኖር የምንችለዉን በማድረግ፣ ከአቅማችን በላይ የሆነዉን ደግሞ ይለፍ ብለን በማሳለፍ ለራሳችን ዋጋ መስጠት!

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.5K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 16:37:32
ነፍስ ይማር

አርቲስት ዳዊት ነጋ በህይወት ሳለ " ካሌብ ሾው ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቃለመጠይቅ በሰጠበት ወቅት ለወጣቶች ያስተላለፈው መልዕክት ፦

" ... ስኬት አጠገብህ ነው ያለው። በጣም ሩቅ መስሎ የሚታያችሁ ፣ በጣም ጨለማ መስሎ የሚታያችሁ ነገር ከናተ ጋር ነው ያለው።

ለምንም ነገር መሸነፍ የለብህም። ማንም ሰው የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል በእኔ መማር አለበት።

እኔ ትልቅ ነገር ሰርቼ ሳይሆን በአቅሜ የምችለውን ነገር እየሰራው ነው፤ ቢያንስ ትላንት የምተኛበት ቤት አልነበረኝም፤ ለረጅም ጊዜ የእራት መብያ እንኳን አልነበረኝም እንደኔ ያጣ ኢትዮጵያዊም ያለ አይመስለኝም።

ተስፋ አልቆርጥም። አንድ ጊዜ ሰው ሆናለሁ ብዬ አልሸነፍም ነበር። የ200 ብር የቤት ኪራይ መክፈል ሲያቅትህ አስበው ...

ወጣቱ በእኔ እንዲማር እፈልጋለሁ። የሚፈልገውን ስራ ዶክተር ፣ መሃንዲስ ሊሆን ይችላል የፈለገውን አይነት ሞያ ያለው ሰው እኔ ሰርቼ እቀየራለሁ ብሎ እራሱን ማሳመን አለበት ፤ ከዛ ለራሴ ሆኜ ለሀገሬ ፣ ለህዝቤ ሆናለሁ ብሎ ማሰብ አለበት ፤ ተስፋ ካልቆረጠ ማንም ሰው ምንም ማደረግ ይችላል። "

@tikvahethiopia

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.2K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 12:59:43 ችግርህን ፃፍ

“በህይወቴ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ” ብለህ ካሰብክ አንድ ነገር ልንገርህ...

ማድረግ የማትፈልጋቸዉን ነገሮች ፃፋቸዉ፡፡ “ይህን አልፈልግም” ብለህ በግልፅ ወረቀት ላይ ፃፋቸዉ፡፡

ቀላል የሳይኮሎጂ ምክር ሊመስል ይችላል ግን በጥናት እንደተረጋገጠዉ 90 % የሚሆነዉን ችግርህን እንድታቃልል ይረዳሃል...

ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር አያዉቁም ነገር ግን የማይፈልጉትን በደንብ ያዉቃሉ፡፡ ስለዚህ የማትፈልገዉን ከፃፍከዉ ወደመፍትሄዉ ለመግባትና እንዴት መሄድ እንዳለብህ ለመወሰን ይቀልሃል!

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.0K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 17:44:03 ኢንተርቪው

ሰዎች ስራ ሊቀጠሩ ኢንተርቪዉ ሲደረጉ አንድ የሚሳሳቱት ነገር አለ፡፡

እስኪ ይሄን ኢንተርቪዉ ተመልከቱ

ጠያቂ፡ እሺ የመጨረሻ ጥያቄ ... ስለስራው ማወቅ እና መጠየቅ የምትፈልገዉ ነገር አለህ ?

ስራ ፈላጊ፡ አይ ምንም የለኝም፡፡

ጠያቂ፡ መልካም! ዉጤቱን በስልክ እናሳዉቅሃን፡፡

ስራ ፈላጊዉ ምን የተሳሳተ ይመስላችኋል ?

አዎ ስለስራዉ ሁኔታ ብዙ ጥያቄ መጠየቅ ነበረበት ፡፡ እሱ ግን ለስራው ምንም ፍላጎት እና ጉጉት እንደሌለዉ አሳይቷል ።

ብዙ ጊዜ ቅጥር የሚፈፅመዉ ተቋም ወይም ሰዉ ኢንተርቪዉ ሲያደርጉ የስራ ፍላጎታችሁ ምን ያህል እንደሆነ በዚህ ቀልድ በሚመስል ግን ወሳኝ ጥያቄ ይመዝናሉ፡፡

ስለዚህ ቢያንስ የሆነ ነገር ጠይቁ እንጂ ዝም ብላችሁ አትዉጡ !

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.2K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:46:30 ቀንህ ነው

አንድ ጊዜ የሞት መልአክ ወደ አንድ ሰው ጋር ይመጣና ❝ ዛሬ ያንተ ተራ ነው ልወስድህ መጥቻለሁ❞ ይለዋል ።

ሰውዬውም ተደናግጦ
❝ ግን እኮ አልተዘጋጀሁም ❞ ብሎ ይመልስለታል።

የሞት መልአከከም ❝ እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም የተሰጠኝ የስም ዝርዝሩ ላይ ያለው የመጀመሪያ ስም ያንተ ነው ተራህ ደርሷል ❞ ይለዋል ።

ሰውዬውም ተስፍ በመቁረጥ ❝ እሺ በቃ ትንሽ አረፍ በል የሚበላ ነገር ላምጣልክ እኔም ቤተሰቦቼን እና ጕደኞቼን ልሰናበት ከዛ ይዘከኝ ትሄዳለክ❞ ይለዋል ።

መልእኩም በሰውዬው ሀሳብ ተሰማምቶ ቁጭ አለ። ሰውዬው አንድ ሀሳብ መጣለት ፣ ምግቡ ውስጥ የእንቅልፍ መድሀኒት ጨምሮ ለመልዓኩ ሰጠው ።

መልእክተኛው ምግቡን በልቶ ከጨረሰ በኃላ ወዲያው ቅልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው ።

ሰውዬው በፍጥነት የያዘውን ስም ዝርዝር አንስቶ የራሱን ስም ከመጀመሪያው አጥፍቶ መጨረሻ ላይ አደረገው ።

መልአኩም ከእንቅልፉ ሲነቃ ሰውየውን ላደረገለት መስተንግዶ ከልቡ አመስግኖ እንዲህ አለው ❝ በል እንግዲህ ወዳጄ ስላደረክልኝ እንክብካቤ ሁሉ በጣም አመስግናለው በጥሩ ሁኔታ ሰላስተናገድከኝ ለዛሬ ከመጨረሻው እጀምራለው ❞ ።

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር

ማንም ሰው ከቀኑ አያልፍም!!
2.3K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ