ኢንተርቪው ሰዎች ስራ ሊቀጠሩ ኢንተርቪዉ ሲደረጉ አንድ የሚሳሳቱት ነገር አለ፡፡ እስኪ ይሄን ኢንተርቪዉ ተመልከቱ ጠያቂ፡ እሺ የመጨረሻ ጥያቄ ... ስለስራው ማወቅ እና መጠየቅ የምትፈልገዉ ነገር አለህ ? ስራ ፈላጊ፡ አይ ምንም የለኝም፡፡ ጠያቂ፡ መልካም! ዉጤቱን በስልክ እናሳዉቅሃን፡፡ ስራ ፈላጊዉ ምን የተሳሳተ ይመስላችኋል ? አዎ ስለስራዉ ሁኔታ ብዙ ጥያቄ መጠየቅ ነበረበት ፡፡ እሱ ግን ለስራው ምንም ፍላጎት እና ጉጉት እንደሌለዉ አሳይቷል ። ብዙ ጊዜ ቅጥር የሚፈፅመዉ ተቋም ወይም ሰዉ ኢንተርቪዉ ሲያደርጉ የስራ ፍላጎታችሁ ምን ያህል እንደሆነ በዚህ ቀልድ በሚመስል ግን ወሳኝ ጥያቄ ይመዝናሉ፡፡ ስለዚህ ቢያንስ የሆነ ነገር ጠይቁ እንጂ ዝም ብላችሁ አትዉጡ ! ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ @therapist_100 @therapist_group ሼር @love_therapist ሼር 2.2K views14:44