Get Mystery Box with random crypto!

lnspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ lnspire_ethiopia — lnspire Ethiopia L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lnspire_ethiopia — lnspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @lnspire_ethiopia
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.57K
የሰርጥ መግለጫ

Well come guies this channal is the most powerful idas to change your life to better way and injoy it
Certified Professional Life Coaches
✍✍ችግራችን የችግር መኖር አይደለም። ችግራችን ችግር በፍጹም መከሰት የለበትም ብለን አስበን ችግር መኖሩን እንደችግር መቁጠራችን ነው✍✍
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-21 09:00:19 ከጣልከው አይነሳም !

ወፍራምን ሰው ለመጣል ከባድ ነው ከበድ ያለ ትግል ይጠይቅ ይሆናል ነገር ግን ከወደቀ ፈፅሞ አይነሳም ፤ አንተም አንቺም ከባድ የሆነ ወቅት ላይ ትሆናላችው ችግሩን ለመጣል የማትችሉ ያህል ተሰምቷችው ይሆናል ነገር ግን ሙሉ አቅማችውን ተጠቅማችው ጣሉት ችግራችው ወፍራም መሆኑን ውደዱት ምክንያቱም አንዴ ከጣላችውት በኋላ ፈፅሞ ሊነሳ አይችልም! ቀላል የሆኑ ትግል የማይፈልጉ ነገሮች እኛንም አያጠነክሩንም ስለዚህ ደስ ይበልህ! ደግመህ የማትገባበት ልትጥለው የምትችለው ፈተና ነው እና የተሰጠህ!

የተባረከ ሰንበት ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
2.1K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:04:03 እመን!

"አንድ እምነት ያለው ሰው ፍላጎት ብቻ ካላቸው 99 ሰዎች እኩል አቅም አለው" ይለናል ጆን ስቱአርት ሚል። የእምነትን ፍሬ ሳትዘራኸው ማጨድ የለም፤ ምንም ነገር እንደማያቅትህ በሂደት ሁሉም ነገሮች እንደሚሳኩልህ ማመን አለብህ!

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.0K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:50:36 ውስጥህ ምን እያለህ ነው!

እኛ የሚሰማን ስሜት ሌሎች አይሰማቸውም ፣ ፈጣሪ በሁላችንም ልብ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብን አስቀምጦልናል ፤ አንዳንዴ ልባችን እያወቀ ውስጣችን ልክ እንዳልሆነ እየነገረን የምንሰራቸው ስራዎች ምንም ያህል ብንሄድባቸው ትክክል አይመጡም ከእኛ ጋር አይገጥሙልንም ፤ ምን አልባት እኛ ያመንበት ከሌሎች ጋር ላይጣጣም ይችላል ግን ደግሞ ይባስ የሚከብደው ከራሳችን ጋር ሳይጣጣም የምናደርገው ነገር ነው! ለመደነቅ ወይ ከሁሉም ሰው ድጋፍ ለማግኘት ከምትሰራው ይልቅ በልብህ በመደገፍ የምትሰራው ያዋጣሀል !

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
2.0K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 22:38:22 ትችላለህ!

ወዳጄ 'አልችልም' ካልክ ልክ ነህ አትችልም፤ 'እችላለሁ'ም ካልክ ልክ ነህ ትችላለህ! ሁሉም በመዳፍህ ነው! ውስጥህ ካመነበት የምትፈልገውን እንዳታገኝ የሚያስቆምህ ማነው?!

እንደምትችል ማንም እስኪነግርህ አጠብቅ! አንተ የምትችለውን ሁሉ ስታደርግ ፈጣሪ ደግሞ የማይቻል የሚመስለውን አድርጎ ያሳይሀል!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.0K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:41:30 ፈጣሪ መቼም አይተወንም!


ብዙ ሰዎች ቃል ሊገቡልን ይችላሉ ! አንተ ብቻ ተመረቅ እንጂ በበነጋታው ነው ስራ የማስገባህ ከሚለው አንስቶ እስከ ትልልቅ ነገሮች እኔ አደርግልሀለው፣ አሳካልሀለው፣ አስተካክልካለው እያሉ ብዙ ተስፋ ይሰጡሀል ከዚያ ግን በጣም በፈለግካቸውና ቃል የገቡልህ ሰዐት በደረሰ ግዜ ከጎንህ የሉም ያኔ ምን ይሰማሀል? አምነትህን ሙሉ ለሙሉ የጣልክባቸውን ሰዎች ምንም ሊያረጉልህ እንደማይችሉ ስታውቅ ተስፋ ትቆርጣለህ? ሁሉን ነገር ታቆማለህ? በፍፁም እንዳታደርገው ! የሰው ልጅ ትልቁ ተስፋ ፈጣሪው ብቻ ነው ስለዚህ ቃል የገቡልህ ያመንካቸው እነሱን ተንተርሰህ መንገድ የጀመርክባቸው ድንገት ቢሸሹህ የሚያስጨርስህ እና የሚያሳካልህ የሚያግዝህ ፈጣሪ እንዳለህ አስታውስ !


የተባረከ ሀሙስ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
800 views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:32:02 በፍቅር ማሸነፍ!

ሰዎችን ሁሉ አሳምናለው ካልክ ከድካም ውጪ ምንም አታተርፍም፤ ዝቅ ማለት ካለብህ ዝቅ ትላለህ፣ ያንን ጊዜ አጎንብሰህ ማለፍ ካለብህ አጎንብሰህ ታልፋለህ።

አንዳንዴ ታሪክ የምትሰራው በማሸነፍ ብቻ አይደለም፤ ለፍቅር ስትል ዋጋ በመክፈልና በመሸነፍም ነው። ይሄን የምታደርገው ለጊዜው ተሸንፈህ ለዘላለም ለማሸነፍ ነው!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
891 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:22:41 ሁሌም በመልካም መልስ!

አሸናፊ ሰው የሰዎችን ከባድ ስሜት መቆጣጠር የሚችል ነው ! ሰዎች በህይወት አጋጣሚ ብዙ ነገሮችን ሊያሳልፋ ይችላሉ ይከፋሉ፣ ይናደዳሉ፣ ይጨነቃሉ ከዛም በምንሰራበት ቦታ ወይ ደግሞ ያለንበት አካባቢ በዚያ ስሜት ውስጥ ሆነው ይገኙ እና የሚያስቀይም ንግግርን ሊናገሩን ይችላሉ ያኔ ታድያ እኛም ከእነርሱ በላይ የሚያስቀይም ንግግርን ከአንደበታችን ካወጣን ሊፈጠር የሚችለውን የማያልቅ ጭቅጭቅ እና አለመግባባት በዛ ላይ እርስ በራስ ከሚፈጠርብን ጥላቻ ባለፈ የዛን የተረበሸ ሰው ስሜት የባሰ መጉዳት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍልስ እናስበዋለን? ሁሌም ባለን እና በተቻለን አቅም ሁሉ ለሰዎች መልካም እንሁን ከልባችን እናግዛቸው ምንም አይነት ምላሽ ይስጡን ጥሩነታችንን እናጋራቸው ያኔ እነርሱ በነበራቸው መጥፎ ስሜት ያፍሩበታል መልካምነታችን ይጋባባቸዋል አሸነፍን ማለት ይሄ አይደለ!

ደስ የሚል ረቡዕ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.1K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:02:22 ደስተኛ መሆን አለብህ!

አንዳንዴ በጣም ከባድ ችግር የመሰለህ ነገር አስቂኝ ሆኖ ቁጭ ይላል፤ በዚህ ምድር ለመኖር የቀረህ 1 ሳምንት ብቻ ነው ቢባል የትኛው ሰው ነው የኑሮ ውድነት የሚያሳስበው? የትኛው ሰው ነው የፍቅረኛው ስልክ አለማንሳት የሚያበሳጨው? ያለህን አጭር ጊዜ እንዴት አጣጥመህ እንደምታልፈው ታስባለህ እንጂ በፍፁም አተክዝም።

አየህ ወዳጄ አሁንም የቀረህ እድሜ ስንት እንደሆነ አታውቀውም፤ ተኝተህ ማደርህን እንኳን እርግጠኛ አይደለህም! ስለዚህ ለማን ብለህ ነው የምታዝነው? በፈጣሪህ እመን ከዛ የምትችለውን ሞክር የቀረውን ለነገ ተወው!

ገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.2K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 08:25:56 ብቻህን ተደብቀህ አትታገል !

ምንም አይነት ስሜት ለይ ብትሆን ቢከፋህ ቢደብርህ ያለመቻል የመሸነፍ ስሜት ቢሰማህ በርህን ዘግተህ አትተኛ ፣ አትደበቅ ፣ ብቻህን ቁጭ ብለህ አትከፋ! ተነሳ ፣ ተታጠብ ፣ ልብስህን ቀይር ራስህን አስተካክል ከዛም ውጣ አካባቢህን በዙሪያህ ያሉትን ሁሉ ተመልከት እንቅስቃሴ አድርግ ሮጥ ሮጥ በል ከሠዎች ጋር ተወያይ ከዚያ ያ የነበረክ ስሜት ሁሉ ከላይህ ላይ እርግፍ ብሎ ሲለቅህ ታየዋለህ በአዲስ ሀሳብ በተሻለ ማንነት ትሞላለህ!

የተባረከ ቀን ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.2K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:51:00 የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል!

ታሪክ መስራት ከፈለክ አብዛኛው ሰው የማያደርገውን ማድረግ አለብህ፤ ሌላው ሲተኛ አንተ ትነሳለህ፣ ሌላው ጊዜውን በከንቱ ነገር ሲያጠፋ አንተ ራስህ ላይ እና ስራህ ላይ ታጠፋለህ፣ ሌላው ገንዘብ ሲያጠፋ አንተ ታስቀምጣለህ፣ ሌላው ወደ ፈጣሪው ለመቅረብና ፀሎት ለማድረስ ጊዜ ሲያጣ አንተ ይበልጥ በመንፈሳዊነትህ ትጠነክራለህ!

ወዳጄ የተለየ ነገር ከፈለክ የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል፤ ደስ የሚለው ምን ማድረግ እንዳለብህ አውቀህ መንገዱን ጀምረሀል፤ ማን እንደሆንክ ለራስህ ሳታሳየው ማቆም የለም!

አስደናቂ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.3K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ