Get Mystery Box with random crypto!

lnspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ lnspire_ethiopia — lnspire Ethiopia L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lnspire_ethiopia — lnspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @lnspire_ethiopia
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.57K
የሰርጥ መግለጫ

Well come guies this channal is the most powerful idas to change your life to better way and injoy it
Certified Professional Life Coaches
✍✍ችግራችን የችግር መኖር አይደለም። ችግራችን ችግር በፍጹም መከሰት የለበትም ብለን አስበን ችግር መኖሩን እንደችግር መቁጠራችን ነው✍✍
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 10:40:24 መጀመሪያ እኛን እንይ !

አብዛኛውን ግዜ ላሳኩ ሰዎች አስተያየት መስጠት ይቀናናል ፣ እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ እንደዚያ ቢፈጥሩ እኮ የተሻለ ያገኙ ነበር የተሻለ ይሆንላቸው ነበር ፣ እንደዚህም ቢጨምሩበት እንላለን እነሱ ያንን ነገር ሲያሳኩ እኮ ብዙ ነገሮችን ሞክረው አይተው ተረድተው ነው! ምን አልባት ግን እኛ እነሱ የደረሱበት ሩቧን እንኳን አልሞከርናትም አንዳንዴ አስተያየት ለመስጠት የምናባክነውን ግዜ ከነሱ ለመማር ብንጠቀመው ከእኛም አልፈን ለብዙዎች እንተርፋለን!

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.5K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:04:22 ያንተ ተስፋ ማነው?!

እንደ አንተ ጭንቀትና ሀሳብ ቢሆን ዛሬን ማየት የማይታሰብ ነበር፤ ያንን ጊዜ ማለፍ ቅዠት ነበር፤ ግን አለፍከው፤ ያልገመትከው ሁሉ ሆነ አንተ ተስፋ ቆርጠህ ስትጨርስ ፈጣሪ ጀመረ። ያንተ ተስፋ የዚህ አለም ተለዋዋጭ ነገር አይደለም! ያንተ ተስፋ የማይለወጠው፣ በዘመናት የማያረጀውና የማያልፈው ፈጣሪህ ነው!

አስደሳች ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.5K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:32:33 ስኬት እና ደስታ በእጃችን ነው!

ስኬታማ እና ደስተኛ ሰዎች ፍቅር የተሞሉ ናቸው ፤ ሁሌም ቢሆን ከመስጠት አይቆጠቡም ከማድረግ ወደኋላ አይሉም ለመጣው ሰው ሁሉ ሰላም ፍቅር መረጋጋትን ይሰጣሉ ሁሉም ሰው እነሱ ባሉበት መገኘትን ይወዳል ፤ ስለዚህ ስኬትን እና ደስታህን እሩቅ አትፈልገው ከውስጥህ ፍጠረው ከልብህ ሁን ከልብህ ውደድ ከልብህ ስጥ ያኔ ከልብህ ትደሰታለህ!

ደስ የሚል ጁምዓ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.6K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:29:36 ስኬት የኪራይ ቤት ነው!

ስኬት ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል ልናገኘው ለምንፈልገው ነገር ሁሌም ልንተጋለት በየቀኑ ሊሰጠው የሚገባውን ነገር ልንሰጠው ይገባናል ! አንዴ አሳክቻለው ብለን ቆመን የምናየው ነገር አይደለም ዛሬም ነገም ከነገ ወድያው ከስር ከስሩ እየኮተኮትን ልናሳድገው ይገባናል ካለበዚያ ግን የቤቱን ኪራይ እንዳልከፈለ ሰው ዋጋ ባለመክፈላችን እንባረራለን!

የስኬት ጊዜ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.7K views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:48:10 በፈጣሪህ እመን...ከዛ በራስህ እመን!

"ማየት ማመን ነው" ሲባል እንሰማለን ግን አንድ ነገር ካየኸውማ ማረጋገጥ ነው የሚባለው። ማመን ያለብህ ገና ያላየኸውን ነው፤ ገና እጅህ ውስጥ እንዲገባ የምትፈልገውን ደስታ፣ ሀብትና መንፈሳዊ እርካታ ገና ከመሳካቱ በፊት እንደሚሳካ እርገጠኛ መሆን ነው ማመን ማለት።

እልም ባለ ጨለማ ውስጥ ብርሀን የሚያይ ሰው ከምንም ነገር ይወጣል፤ ወዳጄ እምነት እንዳለው ሰው ሀያል የለም፤ አስፈሪ የሚመስሉ ሁኔታዎችና ነገሮች ሁሉ በእምነትህ ፊት ቁጫጭ ናቸው!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.7K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:09:49 "አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም !"

ስላላወቅኩ ነው አልሰማውም ነበር ብለን ከፍርድ መዳን አንችልም በላይኛውም በዚህኛውም ምድር ጥፋት ሁልግዜም ጥፋት ነው ! በህይወትም ባለማወቅ ፣ ባለመረዳት ብዙ ነገሮችን አጥተናል ከዚህ በኋላ ግን እስቲ ይብቃን መንገዳችን የተበላሸ ሲመስለን ኑሮ ሲቆረቁረን እስቲ ራሳችንን እንፈትሸው ልክ ያልሆነውን ነገር ተምረን እንለውጠው ለማወቅ አንተኛ!

የተባረከ ቀን ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.8K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:56:50 እችላለሁ በል!

ለትልቅ አላማ ነው ወደዚህ ምድር የመጣኸው ግን የምትፈልገውን ሁሉ ማሳካት እንደማትችል እያመንክ ስለሆነ ከአብዛኛው ሰው ጋር ለመመሳሰል እየጣርክ ነው። እንደ ንስር ከፍ ብለህ መብረር እየቻልክ ለምን እንደ ዶሮ መሬት ትጭራለህ?

ትልቅ ነገር የምታሳካው መጀመሪያ በነፃነት ትልቅ ማሰብ ከቻልክ ነው፤ አየህ መጀመሪያ ሀሳብ ትዘራለህ ከዛ ወደ ተግባር ትገባለህ። ወዳጄ አልችልም የሚለውን ትብታብ በጥሰህ የፈለከውን ሁሉ ለማሳካት ፈጣሪ እንደፈቀደልህ ራስህን አሳምነው! አሁን ለራስህ እችላለሁ ከማለት ጀምር!

የሚገርም ምሸት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.8K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:56:00 "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!"

አንዳንዴ የሆነ ቦታ ላይ የምንፈልገው ነገር ይኖራል ከእርሱ ውጪ ምንም ነገር የሌለ ይመስለናል ፤ አልተሳካም ማለት በቃ አለቀልን መንገድ ላይ መቅረታችን ነው ፣ የእኛ ነገር አበቃ ተበላሸ ይመስለናል ግን ደግሞ ከአጠገቡ ሌላ ትልቅ እድል ትልቅ ህይወት ተቀምጦ ይጠብቀናል የፈጣሪ አላማ እኮ ሁሌም ለእኛ የሚበጀውን መስጠት ነው እንጂ ፈፅሞ ሊጥለን አይፈቅድም የአንዱን በር ሲዘጋብን ሌላውን ወለል አድርጎ እየከፈተው ነው ስለዚህ አትቁም ዞር ዞር ብለህ ተመልከት ይሄ ተዘጋ እንግድያው ያ ተከፍቷል በል መቼም አትቁም!

የስኬት ቀን ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.9K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:19:30 ለውጥ ህመም አለው!
1.9K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:33:46 ተማመን ጥያቄህ ይመለሳል!

"ፈጣሪ ለጥያቄዎችህ ሁሉ ፈጣን ምላሽ ሲሰጥህ እምነትን እያስተማረህ ነው ፤ ትንሽ ከዘገየ ትዕግስትን እያስተማረህ ነው ፤ በጣም ከዘገየ ግን ከጠየቅኸው የተሻለ እጥፍ እያዘጋጀልህ ነው!" ስለዚህ ጥያቄህን ለፈጣሪ ብቻ ስጥ ከዛ ግን መመለሱ እንደማይቀር እመን መንገዱ ይለያይ እንጂ ሁሉም ጥያቄ ይመለሳል!

የበረከት ሰኞ ይሁንላችው
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.9K views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ