Get Mystery Box with random crypto!

lnspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ lnspire_ethiopia — lnspire Ethiopia L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lnspire_ethiopia — lnspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @lnspire_ethiopia
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.57K
የሰርጥ መግለጫ

Well come guies this channal is the most powerful idas to change your life to better way and injoy it
Certified Professional Life Coaches
✍✍ችግራችን የችግር መኖር አይደለም። ችግራችን ችግር በፍጹም መከሰት የለበትም ብለን አስበን ችግር መኖሩን እንደችግር መቁጠራችን ነው✍✍
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-04 08:24:16 ከሁሉ ፍቅር ይቀድማል!

ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህ? ፍቅርን ፍጠር አካባቢህን በሙሉ በፍቅር ሙላው ለምታገኘው ሰው ሁሉ ሰላምን ስጥ ከልብህ መውደድን ተማር ! ከልብህ መስጠትን ጀምር ! ምንም ሳትጠብቅ ሁኔታዎችን ሳታይ ካንተ የሚጠበቀውን ብቻ ፈፅም ያኔ ህይወት መልካም ነገሯን በሙሉ ወደ አንተ ትገለብጣለች ደስታህ ወደር አይኖረውም ፤ ፍርሀት ጥርግ ብሎ ከውስጥህ ይጠፋል ፤ እመነኝ በፍቅር ከሆነ ሁሉን ነገር ታሸንፋለህ!

ደስ የሚል ሰኞ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.5K views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 08:17:12 ሰዎች እንዳያደክሙህ!

በጣም ጠንካራ እና ጎበዝ ስትሆን ሰዎች አስተያየት ያበዙብሀል እንደዚህ እኮ ብትጨምር ፣ ይሄንን እኮ ብታደርግበት ኖሮ እኮ በጣም ጥሩ ትሆን ነበር ግን አጠፋህ ይሉሀል የሰራሀቸውን ያደረግሀቸውን ትላልቅ ስራዎችህን ውርድ ያደርጉብሀል ግን የሚገርመው አንተ የለፋኸውን አንዲቷን ልፋት እንኳን አልለፉም ፣ ያደረግኸውን እንዲቷን ጥረት አልጣሩም ፣ በፍፁም ያንተን ድል አላገኙም ዝም ብለው ተቀምጠው ግን አንተን ይተቻሉ ያኔ አንተም ውስጥህ ይሸበራል አልችልም እንዴ ፣ ምንም ነገር አልሰራውም እንዴ ? ምንም አልችልም እንዴ ያስብሉሀል ያገኘኸውን ድል ፣ ያሸነፍከውን ሁሉ ያስረሱሀል ፤ ስለዚህ አስተውል በፍፁም ላትሰማቸው ለራስህ ቃል ግባ መጨመር ያለብህን ልትጨምር ስትነሳ በፍፁም ያለህን እንዳትረሳ ፤ ብዙ እኮ ለፍተህበታል ጀግና እኮ ነህ!

የተባረከ ሰንበት ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.5K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:57:56 መጠየቅ አትፍራ!

ህልመኛ መሆን አለብህ ያለበለዚያ ህልም ያለው አገልጋይ ነው የምትሆነው። ፈጣሪህ ውዱን ስጦታ በነፃ ሰጥቶሀል፤ ጤናህን ቤተሰቦችህን የምትወዳቸውን ሰዎች ሁሉ በነፃ ነው የሰጠህ፤ ሀብት ስኬት ደስታ ብትጠይቀው ለሱ ርካሽ ነው። ወዳጄ መጠየቅ መመኘት አትፍራ፤ ምንም የማይሳነው አምላክ ከጎንህ ነው!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.5K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 09:56:40 ለምንወደው ሁሉ!

አንድ ሰው "በጣም መብላት የምወዳት ብስኩት አለች ፤ እና ደግሞ ብዙ ግዜ አሳ ለማጥመድ መውጣት ያስደስተኛል ነገር ግን አሳ ለማጥመድ በምሄድበት ግዜ ለአሳዎቹ ይዤ የምሄደው እነሱ መመገብ የሚወዱትን ነው እንጂ እኔ የምወደውን ብስኩት አይደለም" ይላል ከአንድ ጋር ሰው የምንፈልገውን ጥሩ የፍቅር ግንኙነትም ሆነ ጥሩ ጓደኝነት ለማግኘት እኛ የምንወደውን ወይ ያስፈልገናል ብለን የምናስበውን ሳይሆን እነሱ የሚወዱትን እና የሚያስፈልጋቸውን ነው ልንሰጣቸው የሚገባው ፤ ያኔ የተሳካ ህይወት እንደምንመሰርት ምንም ጥርጥር የለውም !

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.6K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:26:12 ያንተ ጥንካሬ!

አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል፤ ሀሳብህ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ።

ጨለማው ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ አንተ ግን ለዛሬ ደርሰሀል፤ ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበውን ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነው!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.7K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:49:02 መጥፎ ልማዶቻችንን ትተን ለሰውነታችን ግዜ እንስጥ!

ሰውነታችን ከፈጣሪ የተሰጠን ውዱ ስጦታችን ነው ስለዚህ በደንብ ልናከብረው ፣ ልንንከባከበውና ልንጠብቀው ይገባናል ! በምን?

ስፖርት መስራት ለሰው ልጅ ሰውነት ማማር ብቻ ሳይሆን ጤናን በሚገባ ለመጠበቅና የአእምሮ ስራ ሂደትንም በጣም ከፍ ለማድረግ እጅግ ይረዳናል ወደ ውስጣችንም የምናስገባውን እያንዳንዱን ነገር የምንበላው ፣ የምናነበው ፣ የምናየውን ሁሉ በሚገባ ልንጠነቀቅለት ይገባል! ፈጣሪ አክብሮ በአምሳሉ ሰርቶናል ስለዚህ በየዕለት እንቅስቃሴያችን የምናደርጋቸውን አላስፈላጊ ነገሮች አስወግደን የሚጠቅመንን ተግባራት ለማከናወን ለራሳችን እድል እንስጠው ያኔ ሁሉ ነገራችን ሰላም እና መልካም ይሆናል!

መልካም ጁምአ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.7K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 15:10:14 አሸንፈሀል ማለት ነው!

የሞተን ውሻ ማንም አይደበድበውም! በህይወት እስካለን እና እስከሰራን ድረስ ሰዋች ሊወቅሱን ብዙ ትችቶችን ሊያደርሱብን እና በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ላይ አስተያየት ሊያበዙብን ይችላሉ ፤ ለምን? አነሱ አይሰሩማ ስለስራችን ዋጋ እና ክብደት አያውቁም ፣ እና ደግሞ በጣምም ተበልጠዋል ፤ ታድያ መሸነፋቸውን በፀጋ መቀበል ስለሚያቅታቸው ሌላውን በመተቸት የማሸነፍ ጥማቸውን ያረካሉ ስለዚህ
ሁሌም ቢሆን በስራችን ላይ ያለምክንያት የሚተች ከበዛብን በጣም ከፍ እያልን ነው ማለት ነዉ እና ደስ ይበለን !

የተባረከ ሀሙስ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.8K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:27:36 ድንቅ ነህ!

ምን ያህል ጀግና እና እድለኛ እንደሆንክ ማወቅ ከፈለክ እስከዛሬ ያለፍካቸውን የህይወት ፈተናዎች አስብ፤ አንተ ባትሆን ኖሮ እነዛን ከባድ ጊዜያት ማን ያልፍ ነበር?! ስለዚህ ድንቅ ነህ ወዳጄ! አንቺም እኮ የማይታሰበውን ነው ያለፍሺው ስለዚህ እህቴ አንቺም ልዩ ነሽ!


የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.9K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:54:51 የሚጠበቅብህን በሙሉ አድርግ !

እድሎች በየት በኩል ሊመጡ እንደሚችሉ አይታወቅም ፤ ዝም ብለህ አመስግነህ ማድረግ የሚገባህን ድብን አድርገህ ስራ ከዛ ታግሰህ ጠብቅ እመነኝ ካሰብካቸው በላይ የታሰበልህ ይበልጣል !

የተባረከ ቀን ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.9K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 09:37:22 ጥቂት ውሳኔ ብዙውን ለውጥ ያመጣል!

ህይወታችን ላይ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥረው ትልቁ ውሳኔ አይደለም! እያንዳንዷ በየደቂቃው የምንወስናትና የምናከናውናት ጥቃቅኗ ውሳኔያችንና ተግባራችን ነው እንጂ!

መልካም ቅዳሜ ተመኘን
@lnspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
2.8K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ