2022-06-14 18:44:04
ያሰብነውን ለማሳካት ስንሻ ከማድረግ መታቀብ ያሉብን 4 ነገሮች
1. ሌሎችንና አካባቢን መውቀስ
በርግጥ ከኛ ቁጥጥር ውጭ ያሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ሆኖም ግን እኛ ልንቆጣጠራውቸው የምንችላቸው ነገሮችም እጅግ ብዙ ናቸው።
አዕምሯችን ችግር የማብሰልሰልም ሆነ የመፍታትም ችሎታ አለው። “ይህ ሁሉ ችግር እኔ ላይ የሆነው ለምንድን ነው?” ብሎ ከማማረር ይልቅ “አሁን በሕይወቴ ውስጥ ላሉ ችግሮች መፍትሄ እንዴት ማግኘት እችላለሁ? ብለን ራሳችንን መጠየቅ የተሻልን ያደርገናል.
2. ያለ ግብና ዕቅድ መኖር
ግብና ወደግባችን የሚያደርሰን ዕቅድ ከሌለን በደመ ነፍስ እየኖርን ነው ማለት ነው።እንደሰው አያሰብን እንጂ እንደ እንስሳ ዝቅ ብለን በደመነፍስ ብቻ መኖር የተፈቀደልን አይደለም።
ስለዚህ በ2014 ላሳካቸው የምፈልጋቸው ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው? እነዚህን ለማሳካት ምን ፕላን ልጠቀም? የሚሉትን ጥያቄዎች በመመለስ የተሻለ ትርጉም ያለው ሕይወት መፍጠር እንችላለን።
3. ለራሳችን የገባውነን ቃል መዘንጋት
ቃላችንን ሳንጠብቅ ስንቀር ሌሎች በኛ ላይ እምነት ያጣሉ። እኛም ለራችን የገባነውን ቃል መጠበቅ ሲያቅተን በራሳችን ላይ ያለን እምነት ይሸረሸራል። ይህን አደርጋለሁ፤ ይህን እሆናለሁ ካልን በኃላ ወደተግባር መግባት ካልቻልን ውስጣችን መጣረስ ተፈጥሮ ደስታችንንም ሊያሳጣን ይችላል። ስለዚህ በአዲሱ ዓመት ሌሎችን ለማስደሰት እንደምንተጋ ሁሉ ለራሳችንም የገባውነን ቃል መጠበቅ አንርሳ።
4. በየለቱ ወደግባችን የሚወስደንን ተግባር አለመከውን
ተግባር በአዕምሮ የተፀነሰውን ፍላጎት ወደገሃዱ አለም የምናመጣበት መንገድ ነው። ስለዚህ ግዜ የለኝም በማለት አሊያም እዚህ ግባ በማይባሉ ተግባራት ራሳችንን ከማዘናጋት ለመቆጠብ ለራሳችን ቃል መግባት ያስፈልጋል። ወደግባችን የሚወስዱንን ተግባራት ዕለታዊ የግዜ ሰሌዳችን ውስጥ በማስገባት በአዕምሯችን የፀነስውን ወልደን መሳም መብቃት እንችላለን።
ሰባተኛውን በአዲስ አበባ የምናካሂደውን የልባም ሕይወት ስልጠና በመሳተፍና ሃይለኛ በNLP የተቃኙ የስነልቡናና ራስን ማሳደግ መንገዶችን በመለማመድ ውጤትዎን ከፍ ያድርጉ። ስለዚህ በሃምሌ 11 የሚጀምረውን ስልጠና በአካል ለመሳተፍ በስልክ ወይም ቴሌግራም ቁጥር +251974046870 ይደውሉ ወይም ስምዎን ቴክስት ያድርጉ።
ቴሌግራም፡ https://t.me/libamhiwot
ዩቲዩብ፡
2.4K views15:44