Get Mystery Box with random crypto!

ለሙስሊሟ እህቴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lemuslimuaehte — ለሙስሊሟ እህቴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ lemuslimuaehte — ለሙስሊሟ እህቴ
የሰርጥ አድራሻ: @lemuslimuaehte
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.56K
የሰርጥ መግለጫ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
بسم الله الرحمن الرحيم
በቻናላችን
ዲናዊ እውቀቶች
መሳጭ የሆኑ ታሪኮች
ስለ ትዳር ምክሮች

እናንተን ያዝናናል ያስተምራል የምንላቸው
በአላህ ፍቃድ ለናንተ እናደርሳለን።
ከናንተ ሚጠበቀው join ማረግ ነው።
@lemuslimuaehte
for any comment 👇
@fitayebot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 09:40:42 ኢማሙ ሻፍእይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

ሰዎችን ሁሉ ላስደስት ብትል በፍፁም አትችልም። ባይሆን ባንተና በአላህ መካከል ያለውን ግኑኝነት አስተካክል። ከዚያ በኋላ ሰዎች ምንም ቢሉህ ቦታ አትስጥ።
(توالي التأنيس ،صـ:168)
T.me/lemuslimuaehte
149 viewsSofi@, 06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:10:04 ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ። ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል 'እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው' ይለናል። ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን። ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።
196 viewsSofi@, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:23:41 ጁምዓ ቀን በርካታ ሰው ላይ የሚታይ ሱናን የተቃረነ
ተግባር!



①በኩጥባ ወቅት ወደ ኢማሙ
ዞሮ ኣለመቀመጥ
ታላቁ ሊቅ ሸይኽ አልባኒ ረሂመሁላህ እንዳሉት
(ኩጥባ ወደ ሚያደርገው ኢማም ፊትን ኣዙሮ መቀመጥ
ከተዘነጉ ሱናዎች አንዱ ነው) ብለዋልና
እንታረም !
ﺍﻟﺴﻠﺴﻠﺔ ﺍﻟﺼﺤﻴﺤﺔ )] 5/110 . ﻭﻗﺪ ﺫﻛﺮﺕ ﺃﺩﻟﺔ ﺫﻟﻚ ﻓﻲ ﺍﻷﺻﻞ .
②የጁምዓ ኩጥባ ላይ መዘናጋት
አንዳንዱ ሰው ቀድሞ መገኘት እየቻለ ኩጥባ እየተደረገ
ወደ መስጅድ ይመጣል። አንዳንዱ ደግሞ ጭራሽ
እየተሰገደ ይመጣል።
እባክዎን እንታረም !!
3 #ሳምንታዊ_በዓላችን_ለሆነውለ ማዓ እለት ለውበታችን - #ለፅዳታችን_ቦታ_ካለመስጠት)
ለአቅመ ኣደም ወይም ሀዋእ ለደረሰ ሰው የግድ ሆኖ
ሳለም
> ገላን ኣለመታጠብ
የነቢዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
ተወዳጅ ሱና ሆኖ ሳለ
> ሽቶ መቀባትን መዘንጋት
በተለይ ጁምዓ እለት ጥርስ መፋቅ የበለጠ አስፈላጊም
ሱናም ሆኖ ሳለ
> መፋቂያ ኣለመጠቀም
ጥሩና የተሻሉ መጋጌጫቻችንን ተጠቅመን ይበልጥ ወደ
መስጂድ ስንሄድ በተለይ ጁምዓ ቀን መዋብ እንዳለብን
ተጠቁመንም
> ቆንጆና ምርጥ ልብሳችንን ኣለመልበስ
ሁሉም አግባብ አይደለምና
እንታረም !!!
④ከአዛን_በኋላ_ንግድ_ኣቁሙ_እየተባልን
``> የጁምዓ ሰላት ከሁለተኛው አዛን በኋላ ግዢ ሆነ
ሽያጭን ኣለማቆም
« እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ለጁመረዓ ቀን ለስግደት
(ለሰላት) ጥሪ በተደረገ ግዜ ወደ አላህ ማውሳት ሂዱ።
መሸጥንም ተዉ። ይህ የምታውቁት ብትሆኑ ለእናንተመ
በጣም ተሻለ ነው። »
ሱረቱል ጁምዓ:9
ኢብኑ ዓባስ ረዲየላሁ አንሁማ እንዳሉት
" በዚህን ግዜ ሽያጭና ግዢ ሀራም ይሆናል " ብለዋልና
እንታረም !

⑤ ጁምዓ ከሌሎች ቀናት በበለጠ ወደ ጌታችን የምንቃረብበት፤ መልካም ስራዎችን የምናበዛበት፤
ኃጢኣቶችን የምንርቅበት፤ የሳምንቱን ወንጀሎቻችንን
የምናስፍቅበት ታላቅ እድል ሆኖልን ሳለ
> በጁምዓ ቀን በአንዳንድ ኃጢኣቶች ላይ መሳተፍ
ለምሳሌ:
• የሴቶች ሽቶ መቀባት፤
• ያልተሟላ ሒጃብ መልበስ
• ወንዶች ለውበት በሚል ፈሊጥ በዚህ እለት ፂም
መላጨት ፤
• ሱሪያቸውን ከቁልጭምጭሚት በታች ማራዘም …
ከሁሉም እንታቀብ እንታረም !
⑥ለወንድ_ልጅ_በላጩ_ከፊት_ያለው ሰፍ መሆኑ
እየተነገረን፤
ሌሎች በቀላሉ ወደ ፊት እንዳያልፉ መንገድ መዝጋት
አግባብ እንዳልሆነ እየተመከርን
> ከቸልተኝነት የተነሳ መስጅድ ሳይሞላ ደርሰንም ከፊት
ለፊት ቦታ እያለልን፤
~ ቀድሞ ያለው ሰፍ እንዳልተሟላ እያወቅን ከኋላ ሰፍ
ወይም ከመስጅድ ውጪ ከመቀመጥ
እንታረም !!
⑦ መስጂድ_ውስጥ በምንም መልኩ ምዕመናንን
መወስወስ የተከለከለ መሆኑን በመዘናጋት
> የሚሰግድን ሰው ወይም በድብቅ ድምፅ ቁርኣን
የሚቀራን ሰው በሚወሰውስ መልኩ ድምፅ ከፍ
በማድረግ ማውራት ወይም ቁርኣን ከመቅራትም
እንሳረም !!
⑧ የጁምዓ ቀን ዋናው መሰብሰቢያ የኹጥባውን
ምክርና መልዕክት መስማት፤ ሌሎችም እንዳይሰሙ
እንቅፋት ኣለመሆን ሆኖ ሳለ
> ኩጥባውን በጥሞና ካለመከታተል፤
~ ራስን በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ወይም ሃሳቦች
ከመወጠር
እንታረም !
⑨ከጁምዓ ሰላት በኋላ 4 ረከዓ ሱና መስገድ እየተቻለ፤
አዝካሮችን ማነብነብ ትልቅ አጅር እያለው፤ ሰለዋት
ማውረድንም ተዘናግቶ
> ሰላት እንዳበቃ የሚባሉ አዝካሮችን ትተው ብድግ
በማለት የሌሎች ሰጋጆችን ሰላት እያቋረጡ እየተጋፉ
እየተንጫጩ በሩን ማጣበብ፤
~ ሌሎች መቀመጥ የሚፈልጉትን ሳይፈልጉ እንዲነሱ
በነሱ ላይ ከመረማመድና ለመውጣት ከመንጋጋት
እንታረም !
~ ጭራሽ ከመስጂድ የተባረሩ ወይም የሚሸሹት ነገር
ያለ እስኪመስል ውጥረት ከመፍጠርም
እንታረም !!!
10) ኢስላም ለሁሉም አይነት የህይወት ዘርፍ ስርዓትና
ደንብ ኣኑሮልንና የአላህ ነቢይ
ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
መስጂድ ውስጥ በጁምዓ እለት ጉልበታችንን አቅፈን
ከመቀመጥ አግደውን ሳለ
> ኩጥባ ሲደረግ በሚከለከለው የአቀማመጥ ሁኔታ
መቀመጣችን የሱና ተቃራኒ በመሆኑ
እንታረም !
እሱም:
መቀመጫን መሬት ላይ አሳርፎ እግሮችን በሆድ ላይ
ለጥፎ አቅፎ ወይም በሆነ ጨርቅ አስሮ መቀመጥ ነውና
ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ እንታረም !
ጁምዓ ቀን ውድ ናት
ﻭﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗﺎﻝ : ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ
ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ :
‏( ﺧَﻴْﺮُ ﻳَﻮْﻡٍ ﻃَﻠَﻌَﺖْ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺍﻟﺸَّﻤْﺲُ ﻳَﻮْﻡُ ﺍﻟْﺠُﻤُﻌَﺔِ
، ﻓِﻴﻪِ ﺧُﻠِﻖَ ﺁﺩَﻡُ ، ﻭَﻓِﻴﻪِ ﺃُﺩْﺧِﻞَ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ، ﻭَﻓِﻴﻪِ
ﺃُﺧْﺮِﺝَ ﻣِﻨْﻬَﺎ ‏) .
ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ‏( 1410 ) .
አቡ ሁረይራህ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወሩን የአላህ
መልዕክተኛ
ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ኣሉ:
« ጁምዓ ፀሃይ ከወጣችባቸው እለታት ሁሉ በላጭ
የሆነች፤
ኣደም የተፈጠረበት፤ ጀነትም እንዲገባ የተደረገበት፤
ከጀነትም እንዲወጣ የተደረገበት እለት ናት ። »

@DinisNesiha
171 views. ...., 05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:11:24 ጨካኙ አባት

ሴት ልጁ እንዲህ ትላለች ....
" 6 አመታትን ያህል አባቴ ባልገባኝ ምክንያት ለትዳር ጥያቄ የሚያቀርቡልኝን ወንዶች ሁሉ እንቢ አለ ። በዚህም ጉዳይ ምንም አይነት ውይይት አይቀበልም ።
እኔን ፍለጋ በሩን የሚያንኳኩ ሰዎችን ሁሉ አባቴ በእንግዳ ማረፊያው ክፍል ለግማሽ ሰዓት አንዳንዴም ከዛ ያነሰ ያህል ያወራቸዋል ፣ ከዚያም የመጣው ወጣት በፍጥነት ይወጣል

እናቴ አባቴን ለመጠየቅ ቸኮለች" ምንድን ነው የሆነው "
እንዲህ ሲል መለሰላት፡- ጥሎሹን አልወደድኩትም የእሱ አቻ በቤታችን ውስጥ የለችም !

የመንፈስ ጭንቀት ወደ እኔ ዘልቆ መግባት ጀመረ ። አባቴ በኔ ድርሻ እና በኔ ደስታ መጋረጃ በመሆኑ በሱ መቆጣት ጀመርኩ። ራሴን እጠይቅ ነበር "እንዴት ሊሆን ይችላል? ለገንዘብ ብሎ ለአንዲት ሴት ልጁ የማይቻለውን ጥሎሽ ይመኛል !

አሁን ተዓምር ተፈጠረ ።
አባቴ ከአመልካቾች ከአንዱ ተስማማ ።
ባለቤቴ ስለከፈለልኝ ጥሎሽ አባቴ ሳይነግረኝ ትዳራችን ተፈፀመ...

የሚገርመው ነገር ባለቤቴ በአማካይ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያለ እንጂ ቀድመውት ከጠየቁት ሰዎች አንፃር ከብዙዎቹ ድሃ ነበር
እሱም ከአባቴ ጋ ስለተስማሙበት ጥሎሽ (መህር)አልነገረኝም

በትዳራችን አስር አመታት አለፉ ። ከባለቤቴ ምንም ክፉን ነገር አላየሁም። ያየሁት ርህራሄን, ደግነትን እና ስስትን ብቻ ነው

ዕድሜዬ እየጨመረ ቢሆንም በባለቤቴ እንክብካቤ ምክንያት ምንም የመከፋትም የመረበሽ ስሜት አይሰማኝም ነበር ።
አባቴ ጥሎን ወደማይቀረው ጉዞ እስኪሄድ ድረስ..

ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ባለቤቴ ወደኔ መጣ ወደ ደረቱ አቀፈኝና “ትንሿ አትዘኚ " አለኝ ።
" ትንሿ " በምትለው ቃል በጣም ተገረምኩ ።
በስስት አየኝና ... ‹‹አዎ ትንሼ ነሽ ።
.....
ለጋብቻ አንቺን ስጠይቅ አባትሽ ምን ማድረግ እንደምችል ጠየቀኝ። ትንሽ አሰብኩና ፡- አጎቴ ብዙ ምሰጠው የለኝም ። ግን ምዬ የምነግርህ ነገር ቢኖር አንተን በሞት ብታጣህ እንኳ የቲምነት እንዳይሰማት አደርጋለሁ። ልክ የአብራኬ ክፋይ እንደሆነች ሴት ልጅ እንከባከባታለሁ " አልኩት ።

አባትሽም ፈገግ አሉና ፡- "ሚስትህ ልጄ ናት"አሉኝ

@lemuslimuaehte
256 viewsSofi@, 08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:37:50 ሚስት እቤት ቁጭ ብላ ለባለቤቷ text አደረገች

"ከቢሮ ስትወጣ እግረመንገድህን ከጉሊት አትክልት ይዘህ መምጣትህን እንዳትረሳ፡ ሀዩ ሰላም እያለችህ ነው

ባል--"ሀዩ ደግሞ ማናት?"

ሚስት--"ዝም ብዬ ነው ባክህ ሚሴጁን ማየትህን ለማረጋገጥ ነው

ባል ተበሳጭቶ ትንሽ ካሰበ በኋላ text አደረገ፡

"ግን እኮ እኔ ከሀዩ ጋ ነው ያለሁት፡አንቺ ስለየትኛዋ ሀዩ ነው ያወራሽው?"

ሚስት--"የት ነው ያለሀው?"

ባል---"ጉሊቱ ጋ ነዋ"

ሚስት---"አሁኑኑ መጣሁ"

ከ10 ደቂቃ በኋላ፡

ሚስት---"የቱ ጋ ነህ ጉሊቱ ጋ ደርሻለሁ"

ባል--" ምን ጥሩ ነዉ ቢሮ ነኝ በቃ የፈለግሽውን አትክልት ገዝተሽ ቤት ሂጂ ማታ መጣለው"

@lemuslimuaehte
357 viewsSofi@, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:13:54 Attitude "አመለካከት"

ሰላም እንደት አደራችሁ ውድ የድርጅታችን ወኪሎቻችን በሙሉ!

ከአሁን በፊት ስለ አመለካከት ብዙ ጊዜ አውርተናል። ስንቶቻችን አሁን ላይ ያለን አመለካከታችን ለነገ ስኬታችንም ይሁን ውድቀታችን ትልቁን ሚና እንደሚጫወትልን ጠንቅቀን እናውቃለን

አመለካከት ቀላል የሚመስል ግን ልዩነት ፈጣሪ ነገር ነው፤ በዚህ አለም ታሪክ የገዘፈ ቦታና ስኬት ላይ የደረሱ ሰዎች ከኛ የተለየ ስጦታ አልተሰጣቸውም ግን ከኛ በተለየ መንገድ ችግሮችን እንደ ጥሩ እድል ይጠቀሙባቸዋል።

ከደሀ ቤተሰብ የተወለዱ ሁለት ሰዎች እንዲህ ሊያስቡ ይችላሉ። አንዱ "በቃ የሆነ ነገር በግሌ እንዳልሰራ ቤተሰቦቼ አቅም ስለሌላቸው ወይ ደግሞ ደህና ዘመድ ስለሌለኝ የትም አልደርስም።"
ሁለተኛው "ከድሀ መወለዴ ችግርን መቋቋም እንድችልና የትኛውንም ፈተና እንዳሸንፍ ጥንካሬ ሆኖኛል" ብሎ ለስኬቱ እንደመሰላል ይጠቀምታል።

አስቡት ሁለቱም የገጠማቸው ተመሳሳይ ችግር ቢሆንም የአመለካከት ልዩነት ግን አንዱን ከፍ አርጎ እላይ ይሰቅለዋል አንዱን ባለበት ያስቀረዋል።

ሰናይ የስራ እና የስኬት ቀን ተመኜሁላችሁ።
316 viewsSofi@, 06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 17:57:31 ➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ለሙተነቂቧ ኮኮብ አድርሱልኝ

ወላሂ ኒቃብ የለበሳቺሁ እህቶቼ ትለያላቺሁ ስላቺሁ በምክንያት ነው!!! እናንተ ከሌላው እጂግ በጣም ውድ ናቺሁ!! የኔ ጀግኖቺ ! ለአላህ ብላቺሁ የሰው ወሬ አውጥታችሁ ጥላቺሁ የአሏህን ትዕዛዝ ለመፈጸም ደፋ ቀና የምትሉ ጀግኖቼ አላህ ይጠብቃቺሁ!!! ጀነትም ደረጃቺሁ ከፍ ያለ እንደሆነ ጥርጥር የለውም ። አሏህ በዱንያ እንዲህ ያስከበራቺሁ የጀነት ደረጃቺሁ ምን ያምር እህቶቼ ? ወላሂ ለናንተ ያለኝ ውዴታና ክብር ትልቅ ነው! አሏህ በያላቺሁበት ይጠብቅልኝ ውዶቼ ! አሏህ በሁሉም ነገር ላይ ሶብሩን ይስጣቺሁ !!! መጨረሻቺሁንም አሏህ ያሳምርላቺሁ።

°• #የእውነት_እህቴ_ነሽ

#ሱኒዋ_እህቴ አንቺ ኒቃብ ለባሽ፡
ለፈጣሪሽ ትዕዛዝ እጅ እግር የሰጠሽ፡
በሰሜን በደቡብ በምስራቅም ያለሽ፡
መንደር ቢለያየን ቢርቅም ሀገርሽ፡
የሰለፍን መንገድ ተከታይ ከሆንሽ፡
ቢደአን ከጠላሽ ሱናን ከወደድሽ፡
ሽርክን ካወገዝሽ፡ተውሂድን ከያዝሽ፡
አብረን ባንውልም ባታቂኝ ባላቅሽ፡
ልባችን አንድ ነው የእውነት እህቴ ነሽ!!

ወንድማቺሁ ዐብዱል ከሪም

https://t.me/lemuslimuaehte
328 viewsSofi@, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 17:32:11
ይሄን ጥምጣም ከሀዲዎች ሲለብሱብን ስንት እንዳልተጣልንበት አሁን የኛዎቹ እህቶች ➧ጂልባብም ሂጃብም ካላደረግነው ሞተን እንገኛለን እያሉ ነው!!! የወንዶችን አልባሳት ➲የሚለብሱ ሴቶች ሁሉ በነብዩ صلى الله عليه وسلم አንደበት የተረገሙ ናቸው።
እህቶች እያስተዋል እንጂ
አሁን ላይ ረሱልን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እወዳለሁ ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ የሚለው ሰው እጅግ በጣም ብዙ ነው ።ኸረ ኡኽታ ከእናት አባትሽ በፊት አንቺ ራስሽ ሱናቸውን ተግባራዊ አድርጊ።


የውደታሽ መገለጫ በአፍሽ ብቻ ለምን ይሆናል እ ?

የእውነት ረሱልን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እወዳለሁ ምትይ ከሆነ እንድትሰሪው ያዘዙሽን በመስራት ቢዚ ሁኚ
የከለከሉትን ራቂ ይህ ነው ረሱልን መውደድ

ያዘዙሽ ኒቃብ እንድትለብሽ ነው

የከለከሉሽ ደግሞ ወንዶች የሚለብሱትን እንዳትለብሽ
ከካፊሮችም ጋር እንዳትመሳሰይ ነው

ውደታሽ የእውነት መሆኑ ሚታወቀው ያዘዙትን በመስራትሽ እና የከለከሉትን በመራቅሽ ነው ።

የእውነት ነው ምውዳቸው ካልሽ

የከለከሉሽን የወንዶች ልብስ መልበሱን አቁመሽ

ያዘዙሽን ኒቃብን ልበሺ በሱም ውስጥ ትክክለኛ ውበትን እና ደስታን ታገኛለሽ

ነፍሲ ወ ኡኽቲ

Z

t.me/lemuslimuaehte
746 viewsاِتقو الله حيث ما كنتم, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:50:21 አቤት ያ ገባውህለታ

አቤት የዛን ለታ የደስታዬ ብዛት
በነቢዩ ሱና ኒካ ያሰርኩ ዕለት

አለሜ ሲሞላ፡ ሀዘኔ ከኔ ሲሸሽ
ብቸኝነት ጠፍቶ ጭንቄ ሲል ገሸሽ

ሰለፊዩን ጀግና ለኔ ያረኩህ ለት
በአቂዳ በሱና ኒካ የመሰረትንለት

አለም ነው ውዴ የዛን ግዜ ደስታ
ታይዋለህ ሁሉን ያገባውህ ለታ ፡፡

T.me/HijabNewWebta
250 viewsخولة محمد, 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:47:28 የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።

የሱና ወንድማችን አብዱ ሰይድ ይባላል። በልጅነቱ በሆነ አጋጣሚ በተፈጠረ አደጋ አንድ አይኑን አጥቶ ሲኖር የነበረና በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን አግብቶ ሁለት ልጆችን ወልዷል።አላህ አግርቶሎት በቀረችው በአንድ አይኑ #ቁረአንም_ሀፍዟል እስካሁን በቆየበትም ጊዜ ለሱና ባለው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ከቤተሰቦቹ ተገሎና ርቆ ምንም እገዛ እንኳን የማያደርጉለትና ዘወር ብለው የማያዩት ሲሆን ስራም ትንሽም ቢሆን የቀን ስራ እየሰራ ቤተሰቦችን ያስተዳድር ነበር ። አሁን ግን መስጊድ ቁጭ ብሎ ቁረአን ሲቀራ ነው የሚውለው ።

ሆኖም አሁን ደግሞ የአሏህ ውሳኔ ሆነና በሚኖርበት ግቢ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ምክንያት እሳቱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የኤሌክትሪክ መብራት ይዞት ጭንቅላቱን ክፉኛ የተመታ ሲሆን ይህ አደጋም የቀረችው አንድኛው አይኑ ላይም ተፅእኖ በመፍጠሩ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥርበት ዶክተሮችም በፍጥነት አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ህክምና ካልወሰድክ የአይንህ ነርቭ በመነካቱ ሁለተኛውንም አይንህን ልታጣው ትችላለህ ብለውታል።

ስለዚህ ይህ የሱና ወንድማችን የቀረችውን አንድ አይኑን ለማትረፍ ህክምናውን ለመጀመር በትንሹ 70,000ሺ ብር( ሰባ ሺ ብር) እንደሚያስፈልገው በዶክተሮች ተነግሮታል ።ይሄንን ብር ደግሞ አይደለም በአንድ ጊዜ በአንድ አመትም ማገኘት ስለማይችል የኛ የወንድምና የእህቶቹ እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል

ያ አሏህ... ተመልኩቱ አንዷንም የተረፈችዋንም አይኑን ሊያጣት ነው ሲደመር ችግር ፣ ድህነት ፣ ልጆች ማሳደግ ፣ ስራ ማጣት ፣ ከቤተሰብ መገለል እያሰቃየው ነው።

እኛ ደግሞ ሁለቱም አይኖች አሉን። #አልሀምዱሊላህ ፣ አሏህም በቁረአኑ እንዲህ ብሎናል (أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ) "ለእርሱ(ለሰው ልጅ) ሁለት አይኖችን አላደረግንለትምን?"( ሱረቱል በለድ ፣ 8) ይላል። ታዲያ አሏህ እንዲህ አይነት ፀጋ ሲውልልን ምስጋናችን ከምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እንዲህ በአይናቸው የተፈተኑ ሰዎችን በማገዝና በመርዳት አሏህ የኛንም አይኖች እንዲጠብቅልን ዱዓ በማድረግ ነው።

ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣ ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን የአቅማቹህን እንድታበረክቱ ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች የእርዳታ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት።

ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ የባንክ አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ
#1000034096008
#የአካውንቱ ስም :- አብዱ ሰይድ መሀመድ

ለበለጠ መረጃ የወንድማችን ስልክ
ስልክ: #0914324157

"በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።

ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንዲታደርጉልን ።
423 views. ...., 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ