Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ kinexebebe — መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ kinexebebe — መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @kinexebebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.36K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡
ግጥሞች
መነባነቦች
ከዚያም ከዚህ
እናስተዋውቃችሁ
፡ ጭውውት
ድራማ.... ወዘተ
ለሀሳብ @ty1921 ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-07 08:21:11 ፨ፆም፨

ከሥጋ ፍቃድ መለየት ነው። ኢሳ 58:3


ሥጋን እያደከሙ ነፍስን ለማጠንከር እግዚአብሔርን መለመን ነው።
መዝ108:24


ለሰው ልጆች የተሰጠ የመጀመሪያው ትዕዛዝ ነው።
ዘፍ3:3

ከጸሎት ጋር ከሆነ የጦር ዕቃ ነው። ማቴ17:21

የእንባ መፍለቂያ ምንጭ ናት።
ማር ይስሐቅ

አርምሞን የምታስተምር ናት።
ማር ይስሐቅ

የንጽሕና መገለጫ ናት።
ማር ይስሐቅ
እንኳን ለፆመ ፍልሰታ ቅበላ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!!!
በዕለተ እሁድ ፆመ ፍልሰታ ይጀመራል።
የበርከት ፆም ያድርግልን
@kinexebebe
2.3K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 13:43:40 ✞#ኧረ_አልሆንልኝም_አለ✞

/ድንቅ የንስሐ መነባንብ/

ኧር አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኃጢአት ሸፈተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

ኧር አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ስወጣ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት መድረክ ስወጣ፤
ልብሰ ተክህኖ ለብሼ ንፍቅ ገባሬ ሰናይ ስሆን፤
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ፤
አካሌ እዚህ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ፤
ነፍሴን በኃጢአት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ።

ኧር አንድ በይኝ እመብርሃን ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ጸሎት ጨርሼ፤
ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ስጋ ገቢያ ተመልሼ፤
በኃጢአት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ ስረግጥ እውላለሁ፤
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን እሸጣለሁ።
እዚህ መልአክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ፤
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ኃጢአት በጽድቄ ተተክቶ፤

በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ ሸር ስሸርብ፤
ስዋሽ ስቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ፤
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስገባ፤
ሰዓሊለነ ቅድስት ስል ያለ ንስሐ እንባ፤
የመውደቂያዬ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወሰን ዳርቻ የለውም፤
እዝነ ህሊናዬ ለዓለም እንጂ ለጽድቅ ቦታ የለውም፤

መሃረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ፤
ኃጢአት በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ፤
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ።
ስለእኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ፤
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም ተቃጥዬ።

ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን?

ዓይኔን ወደ ፀፍፀፈ ሰማይ ወደ ሥላሴ መንበር፤
አንስቼ ማየት አቃተኝ ማረኝ ብዬ ለመናገር።
ለሰው ጻድቅ መስዬ የኃጢአት ጎተራ ሆኛለሁ፤
እንዴት አባቴ ቀና ብዬ መንበረ ጸባኦትን አያለሁ።
እባክሽን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
እንደቃና ዘገሊላ ባዶ ማድጋዬን ሙዪልኝ።
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤል ጋር አስታርቂኝ፤
ለተጠማ ውሻ እንዳዘንሽ ለመጻተኛው እዘኚልኝ።

አንቺ የትሁታን ትሁት ርህሪይተ ልብ እናቴ፤
ከልጅሽ ከኢየሱስ አማልጂኝ እዘኚ ለእኔም እመቤቴ።
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ፤
በላኤሰብዕ በእፍኝ ውሃ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ።

አንቺ መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው፤
በመወሰን የማይወሰን እሳተ መለኮትን የቻልሽው።
አንቺ ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው፤
ዛሬም ለእኔም ተስፋ ሁኚኝ ለነፍሴ ስለነፍሴ ተዋሺው።

እንጂ እኔማ አልቻልኩም የልቤ ንጽህና ጠፍቷል፤
ለጸሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፡፡
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

የልቤን መወላወል የነፍሴን ድካም አበርቺ፤
በአማላጅነትሽ ስር ነኝ እና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ።
ለሰው ዓይን ባይገለጥም ሰውሬ የሰራሁት ኃጢአት፤
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ሕይወት፤
ይኸው የምናገረው አይሰምር የወረወረኩት አይመታም፤
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም፤
ዕውቀት ምርምር አይዘልቀኝም ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር፤
ዝርው ሆኖብኝ ቀርቶ የነፍስ የስጋዬ ምስጢር።

ይኸው የማወራው ለሰው አይጥም ፍቅር ከእኔ ቤት ርቋል፤
መቆም መቀመጤ አያምርም ሰው በስራዬ ይማረራል፤

የኃጢአት ምንዳዬ ይኸው የኃጢአት ደሞዜ ይኸው ስቃዬ ውስጤን በልቶታል፤
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል።

እና አዛኝቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ፤
ከሰው የሸሸግኩት ኃጢአት ጨርሶ በልቶ ሳይውጠኝ።
የበላኤሰብዕ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ፤
አንቺ ሕይወቴን ዳብሺው ነፍሴ ዕረፍት እንድታገኝ።

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@kinexebebe
2.4K viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 09:31:31 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
መንፈሳዊ ሥነጽሑፍ

ርዕስ፦ደብረታቦር

ከደብሮች ሁሉ ልቀሽ
እውነትን ብርሃን አጥልቀሽ
ተንቀሽ የነበርሽ ተራራ
አንቺ የሚስጥር ስፍራ
የመለኮት ብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጢር
ልቆ ያታየብሽ መንበር
ደብረ ታቦር !!!
ከአድማሳት ከፍ ከፍ ብሎ
ያስምሽ ተረፈ ውሎ
የተዘከረው በአለሙ
ምን ይሆን ወርቅ ስሙ?
ምን አገኘሽ የኔ ታቦር
እንዲያ ተከፍሎ የብርሃንሽ በር
የክብሩ ግርማ የዋጠሽ
እኮ ማነው የረገጠሽ
ጌታሽ ነው አሉ ስሰማ
ከተራራሽ አናት ማማ
የብረሃን ጉንጉን ሻማ
የጎነፀፈሽ በግርማ
ደብረ ታቦር

ከተራሮች አንቺን መርጦ
ከነ አባቱ ተገልጦ
ደጅሽን ሳይንቅ ማክበሩ
እንዴት እንዴት ይሆን ሚስጥሩ?
ይሄንንም አውቆ ዳዊት
ተናግርዋል አሉ በትንቢት
ታቦር ወአርማንኤም በሚል ቅኔ
በስሙ ተደሰቱ የኔ
እያለ ዘመረ በክብር
የዛችን ተራራ ሚስጢር
ያልብ አምላክ ዳዊት
የተናገረው ትንቢት
ለካ ይሄ ኖርዋል ግብ
ደጅሽ በብርሃን ማበቡ
ብሉ በዚያች የብረሃን እልፍኝ
የዘላለም ደስታ ልናገኝ
አስቦ በቅፅጰት እውነቱ
ገርሞትም አይደለ ከስተቱ
የብረሃን ፀዳል ድምቀቱ
እኮ እንደምን አይገርመው
ሙሴ እና ኤለያስ ቆመው
ክብሩን ሲያውጁ እያዩ
ማነዉ የሙሴን አምላክ ሙሴ ባዩ
ሲል ሙሴ ባህር ከፋዩ
የኤልያስንስ ክብር ጌታ
አውርደውት ከሰው ተርታ
ኤለያስ ባዮቹ እነማን ናቸው
ሲል ኤለያስ ገርሙዋቸው
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጢር
የተገለጠብሽ መንበር

ደብረ ታቦር

ይሄን ሲያዩ ሃዋርያቱ
በድንጋጤ ሲመቱ
ደግሞ ወርዶ አባቱ
ልጄን ስሙት በማለቱ
በፍረሃት ማእበል ሲንገላቱ
ይሄን ሁሉ ሚስጥር በመታየቱ
በአንቺ አይደለ ታቦር
መገለጡ የሦስትነት ሚስጥር
ጥንትስ ታሪክሽ ተዘክሮ
መቼ ያልቃል ተነግሮ
እንዲያ ድንቅ
እንበል እንጂ ድንቅ!ድንቅ!
የብረሃንሽ ሰንደቅ

ከአድማሳት ልቆ ሲደምቅ
ክብር እንበልሽ ክብር!ክብር!
አንቺ እውነተኛ የሚስጥር በር
የሥሉስ ቅዱስ ነገር
የተገለጠብሽ መንደር

ደብረ ታቦር

ታቦር አንቺ ታድለሻል
የማይቻለውን ችለሻል
ለመሆኑ እንዴት ቻልሺው ታቦር!
ያን እውነተኛ ፍቅር

ከመንበሩ የተሳበ ንጉስ
ከብረሃን ሰረገላው ሲፈስ
መሰረትሽ ሳይናጋ
ባለበት ቆሞ የረጋ
ምን ይሆን ሚስጥሩ የፅናትሽ
በፊቱ ቆመሽ መታየትሽ??
ልብሱ ነጭ ሆኖ በረድ
አብም ከሰማይ ሲወርድ(ድምጽ ስልክ)
ዙርያው በክብር ደመና
ተመልቶ በብርሃን ፋና
ሙሴ ከመቃብር ተጠርቶ
ኤለያስ ከቤሄረ ሄያዋን መጥቶ
በእየሩሳሌም ስለ ሚሆነው
ሲወያዩ ላስተዋለው
ምን ይመስል ይሆን ገፁ
የብርሃን መለኮት መገለፁ
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጢር
ልቆ ይታየብሽ መንደር

ደብረ ታቦር

ደግሞ የሃዋርያቱ
የእነዚያ የሦስቱ
ጴጥሮስ ያዕቆብ ዮሃንስ
በድንጋጤ ፈረስ
ሲጋልቡ ርደው
እንደ ቄጤማ ወርደው
ከስሩ የተነጠፈው
ምን ይሆን ምክኒያቱ?
ጴጥሮስ ተሸብሮ
ናላው በድንጋጤ ዞሮ
ለእያንዳንዳቹ በጋር
ሦስት ዳሶችን እንስራ
ያበራሽ ይበራ ስሙ ይግነን
ዛሬም ለእኛ በርሃኑ ይሁን
ገኖ የገነነ በፍቃዱ
በሪ ይሁንልን ሠንገዱ
ክብሩን ከፍ ከፍ ወደ ላይ
ከሰማይ ሰማያት በላይ
እንዲሁም በምድር በቀላይ
የ!!አምላካችን አዱናይ
ክብርሽ ዛሬም ነገም ይነገር
መሆንሽ እውነተኛ የብረሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጥር
የተገለጠብሽ መንበር
ደብረ ታቦር
@kinexebebe
2.3K viewsedited  06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 09:59:29 #ዛሬም_አልተውከኝም!!!


ትናንትናን ረስቼ፣
ውለታህን ማሰብ ትቼ፣
በጉልበቷ ተረትቼ፣
በዓለም ስኖር ተስፋ አጥቼ...
ስደክም ስለፋ ስወድቅ ስነሳ፣
የህይወቴን ችግር ለራሴ ሳወሳ፣
መፍትሔ ላመጣ እኔ ለኔ አቅጄ፤
ስኬትን ፍለጋ ላይ ታች ወርጄ፤
.
.
.
በማይጠቅም
ነገር ስባክን ከርሜ፤
ከሚገባኝ በላይ
ለራሴ ደክሜ፤
በጥበብ ልሻገር
ከድልድዩ ቆሜ፤
ማለፍ ተስኖኝ
ሲሰባበር ቅስሜ፤
በመጨነቅ ብዛት
ሲነጠቅ ሰላሜ....
.
.
.
ዳግመኛ ልማጸን
ከቤትህ ስመጣ፤
ናልኝ ልጄ አልከኝ
በፍቅር ያለ ቁጣ።

ፍቅርህ በድርጊቴ
አልቀነሰብኝም፤
ከቤቴ ግባ እንጂ
ውጣ አላልከኝም፤
ትናንት ከኔ ጋር ነህ
ዛሬም አልተውከኝም፤
ጊዜ ማይገድብህ
ፍቅር ነህ ዘላለም፤
መድኃኔዓለም መድኃኔዓለም
መድኃኔዓለም......
ቸርነት ምህረትህ
ከቶ አይገደብም።
@kinexebebe
2.8K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 09:46:10 መፅሐፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔርን በዘፈን አመስግኑ ሲል ምን ለማለት ነው?

ሀ) ዘፈን ለምን ተከለከለ?
በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስትምህሮ መሠረት ዘፈን መስማት፣ መዝፈንም ሆነ በዘፈኑ መጨፈር የተከለከለ ነው። ይህም የሆነው በሚከተሉት ምክነያቶች ነው። ዘፈን የአጋንንት ሥራ ነው። የአጋንንት ግብራቸው ዘፈን መዝፈን ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዘፈን በግልፅ አነጋገር እንዲህ ይላል "በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ" በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል (ኢሳ.13:2)። አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን መረዳት አለብን። ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል:- "እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር። አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር" (1ኛ.መቃ.36:27-28)። በዚህ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለው አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጐራ መሰለፋቸው ነው። ታላቁ የቤተክርስትያናችን የሥረዓት መፅሐፍ "ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ" ሥራን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል:- "ስለ ተግባረ ዕድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ሕግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሠሩ ይገባል። ... እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጫወታ፣ በእግር እንደ ማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር ነው።" (ፍት.ነገ.መን.አን. 23:820)። ይህ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደ ሥራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል።

ዘፋኝነት "የሥጋ ሥራ" በመሆኑ ኃጢአት ነው። የሚዘፍን የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም። (ገላ.5:21):: "በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።" ተብሏልና (ገላ.5:16)። ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል። ሐዋርያት በዲድስቅልያ "ኢትኩኑ ዘፈንያነ" ~ "ዘፋኞች አትሁኑ" ብለዋል። (ዲድስ.አንቀጽ 7) ቅዱስ ጳውሎስ "በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ:: በዘፈንና በስካር አይሁን" ብሏል። (ሮሜ.13:13)። ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ "በስካርና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።" ይለናል (1ኛ.ጴጥ.4:3)። መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ "ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል።" ይለናል (መጽ.ሐዊ አን. 50)። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ "ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችሗለሁ" በማለት ይማጸናል። (ተግ.ዘዮሐ.አፈ.28)። ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ጸንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን። (መጽ.ሐዊ.አን. 12)::

ሁላችሁ ወዳጆቼ የእኛ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችንን በከንቱ ዘፈን ዳንኪራ እና ጭፈራ አናርክሰው። እግዚአብሔር በባህርይው ንፁህ ይወዳልና ሰውነታችንን አንፅተን እንደተዘጋጀን የእርሱ ማደሪያ እና መቀደሻ እንድንሆን ፈቃዱ ይሁንልን።

ለ) መጽሐፍ ለምን በዘፈን አመስግኑ ይላል?
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስትምህሮ መሠረት ዘፈን መስማት፣ መዝፈንም ሆነ በዘፈኑ መጨፈር የተከለከለ ነው። ይህም የሆነው ሐዋርያት እና ሊቃውንት እንዳስተማሩን በእግዚአብሔር የተወገዘ ስለሆነ ነው። በቤተክርስትያናችን ዘፈን የማይፈቀድባቸውን ምክንያቶች መጽሐፍ "በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።" (1ኛ ጴጥ 4፤3) ይለናል። እንዲሁም ዘፈን የሥጋ ሥራና የዝሙት ማቀንቀኛ ስለሆነ ነው።( ማቴ14፤ 4 ገላ 5 ፣19 )።

ጥቂቶች ታዲያ የፅሁፉን መሰረታዊ ሀሳብ በጥልቀት ባለመረዳት እና ከመፅሐፍ ቅዱስ ላይም አገናዝበው ባለማስተዋል ተወዛግበውበታል። በተለይ በመፅሐፍ ቅዱስ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ "እግዚአብሔርን በዘፈን አመስግኑ" የሚል ስለተፃፈ አሁን በየምሽት መዝናኛዎች (Night clubs) የምንሰማውን ዘፈን መልካም እንደሆነ በማሰብ በሌላም በኩል መፅሐፍ ቅዱስ ዘፈንን እንደሚደግፍ አድርገው ማስረጃ ሳይቀር እየጠቀሱ ሲከራከሩ እንሰማንለን።


በመፅሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔርን በዘፈን አመስግኑ" ለምን ተባለ? መዝሙር እና ዘፈን የሚሉት ቃላት በመፅሐፍ ቅዱሳችን በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ። ይሄውም ሁለቱም ቃላት "ኅለየ~ሃሌ ሃሌ" ከሚለው የግእዝ ግስ ትርጓሜ የወጡ ሰለሆነ ነው። የቤተክርስትያናችን የቀድሞ ሊቃውንት "ኅለየ" የሚለውን በአንድ በኩል "ዘመረ ፤ አመሰገነ" ብለው ሲተረጉሙት በሌላም በኩል "ዘፈነ" ይላል ብለው ያስተምራሉ። በተጨማሪም ሁለቱም ዜማ ያላቸው በመሆኑ ሊመሳሰሉ ይችላል። ከላይ እንደነገርኳችሁ ዘፈን እና መዝሙር የሚሉት በመጽሐፋችን ተለዋዋጭነት ስላላቸው በተለያዩ ቦታዎች ላይ በዘፈን አመስግኑ ተብሏል። ሁለቱ ቃላት የትርጉም ተወራራሽነት እንዳላቸው ምሳሌ እንስጣችሁ። "ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት" (መዝ 149:3)። በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ላይ ያሉት ሁለቱ ዓረፍተ ነገሮች መልእክት በተመሳሳይ እግዚአብሔር የሚቀበለውን ስለማድረግ ነው። "በዘፈን" የተባለው ሥጋን ስለሚያስደስተው ሳይሆን በረከት ስለሚገኝበት መዝሙር መሆኑን ልናውቅ ይገባናል። "ይዝፈኑለት" እና "ይዘምሩለት" የሚሉት ቃላት የትርጉም ተወራራሽነት ባይኖራቸው ኖሮ በዚህ አግባብ መፅሀፍ ቅዱስን የሚጋጭ ነው ባልን ነበር። ከላይ "ስሙን በዘፈን ያመስግኑ" ብሎ ያስቀመጠው አሁን እኛ በሥጋና ደም በምናውቀው ወደ ስካር እና ዝሙት ስለሚስበው "አስረሽ ምችው" ሳይሆን እግዚአብሔር የሚቀበለው እና በረከት የሚገኝበት መንፈሳዊ መዝሙር ነው። "የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በገባ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች። ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘፍን ተመልክታ በልብዋ ናቀችው። እግዚአብሔርም ሜልኮልን እስክትወልድ ልጅ አልሰጣትም (መ.ሳ.ቀ 6:16-23)። በዚህም የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ዘፈን የተባለው እግዚአብሔር የሚቀበለው እና የሚመለክበት ባይሆን ኖሮ ዳዊትን በዘፈኑ ያቃለለችው ሜልኮል ልጅ እንዳትወልድ ባልሆነች ነበር። የቤተክርስትያን አባቶቻችን ይሄንን ትክክል ያልሆነ ትርጓሜ በመረዳት በ2ሺህ ዓ.ም በብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርክነት ዘመን ከግሪኩ፣ ዕብራዊው፤ ግእዙ እና ከሰባው ሊቃናት መፅሐፍት በማመሳከር በታተመው መፅሐፍ ቅዱሳችን ተስተካክሎ ይገኛል። በመዝ 149: 3 እና በሌላም ክፍል ላይ "በዘፈን" የሚለውን " በሽብሸባ" ተብሎ ተስተካክሏል።

ይቆየን።

@kinexebebe
2.6K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 09:34:14 ++ ሥነጽሑፍ - የንስሐ መነባንብ !

(ርዕስ - ተንስዑ ለጸሎት )

ያኔ... ከቅዳሴዉ ሥፍራ ከጸሎቱ ቦታ
ሠዎች ነጭ ለብሰዉ ሲቆሙ በተርታ ቄሱም ተንስዑ ሲል ልቤ ሲያመነታ
ተስዐለነ ለማለት አፌም አይፈታ።

ያኔ... ቃጭሉ ሲቃጨል ዜማዉ ሲንቆረቆር
ደዉሉ ሲደወል ጌታን ለማመስገን ሁሉም ሲወዳደር
ካህኑም ሲቀድስ ተንስዑ ሲል ገና
ተሰጥኦ ይመልሳል ተስዐለነ ይላል ህዝቡ በየተራ
ከአርያም መንደር ከቅዱሱ ሥፍራ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ከመላእክት ጋር
እጣኑ ሲያርግ ዉዳሴዉ ሲሰማ
የኔ ልብ እዚያዉ ነዉ ከመላእክቱ ጋር አልሄደም ራማ ።

ያኔ... ሁሉም በየተራ አክሊሉን ሲቀዳጅ
ጸሎቱ ሲሰማ ከእግዜር ከአምላኩ ደጅ እመቤቴ ማርያም ጸሎቱን ስትሰማዉ ፊቱ እንደ ፀሀይ ሲያበራ ለሚያየዉ መልአክ ይመስላል እዚያ ሚያስቀድሰዉ
ጌታንዉን ለማምለክ ከሚንበረከከዉ
ከጽርሀ አርያም ልቡ ከደረሰዉ
ከዚያ ሁሉ ቅዱስ መስቀሉን በመሳል ልቡ ከሚያለቅሰዉ
እኔም ከዚያ አለዉ ከቶ ባለማፈር በመሀል ቆምያለዉ
በልቤ ሳልሰግድ በእግሬ እወድቃለሁ የእጣኑን ሽታ በዉስጤ ሳይሰርግ እንዲሁ ምገዋለሁ ።

ዛሬ... ከቅዳሴዉ ሥፍራ ከጸሎቱ ቦታ
መሔድ የለም አሉ ሁሌ ጠዋት ማታ የለም የካህን ድምፅ የሚስረቀረቀዉ ተንስዑ ለማለት አልቆመም ከቦታው
ህዝቡም የለም ከቶ ተስዓለነ አይል አይንበረከክም እንደድሮ መቶ
ቁርባን አይቀበል ቃጭልም አይሰማ
የለም የእጣን ጢሱ የለም ጎንበስ ቀና
መሐረነ ናፍቋል ቅዱስ ቅዱስ ማለት ከመላእክት ጋራ ።

ዛሬ ግን የኔ ልብ በጸጸት ይደማል የካህኑን ተንስዑ ሁሌም ይናፍቃል
ምንም ድምፅ ሳይሰማ ተስዓለነ ማለት በጣም ይዳዳዋል
የእጣን ጢሱን ሽታ በልቡ ይምጋል
ያኔ ባለመስማት ያጠፋዉን ጊዜ በብርቱ ይረግማል ።

ተንስዑ ሚለዉን ቃል ደጋግሞ ይሰማል
የካህናቱን ሥርዓት በልቡ ይስለዋል
አሁንም ደጋግሞ በጸጸት ይደማል
ብቻ ይምጣ ይላል ደግሞ የዚያን ጊዜ
አንዴ ብቻ አይደለም ተስዓለነ እላለሁ እልፍ አእላፍ ጊዜ
አምላኬ እባክህ አምጣዉ ያንን ጊዜ
ካህኑም ደግሞ ይበል ደግሞ ደጋግሞ ይበል ተንስዑ ለጸሎት ተንስዑ ለቅዳሴ።

ተንስዑ ለጸሎት !
@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe
2.0K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 21:00:59 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ርዕስ፦ቅዱስ ገብርኤል

የሰለስቱ ደቂቅ መጠሪያ ስማቸው
ሳትመራመረው በእውነት ልጆች ናቸው
በእሳት ሲጫወቱ ከገብርኤል ጋራ
ንጉሡ ተደንቆ ለአራተኛው ፈራ
የሰለስቱ ደቂቅ ቁመት በማነሱ
ከፍ ከፍ ብለው እላይ እንዲደርሱ
ተቀጣጠሉ ሲል አዘዘ ንጉሡ
የሰለስቱ ደቂቅ ፀባይ መጠንከሩ
ወደ ፍቅር ጌታ ሄዱ በረሩ
እንደ ንጉሡ ፍርድ እንዳነጋገሩ
የጠብ ሰው ነውና ተጠብሰው በቀሩ
ናቡከደነጾር እዩት ሐሳቡን
ከምስል ቢጣሉ በዚያ ቀውጢ ቀን
የሠለሰስቱ ደቂቅ ገላጋይ ሊሆን
ይልቅ የእርሱ አሽከሮች መልካም ገላጋይ
መላ ቢስ ነው ለካ ፍጹም ወላዋይ
ከላይ ወረደ እንጂ መና ከሰማይ
ናቡከደነጾር በቁጣ ተናዶ
በሰለስቱ ደቂቅ በመሳሳት ፈርዶ


ገብርኤል ነህና ታዳጊ ለሁሉ
እስከ ሰራዊትህ ላትነጣጠሉ
ከጧት እስከ ማታ ለአምላክህ ባለሟል
እናት ኢትዮጲያን ቅዱስ ገብርኤል
እንደባቢሎን ተአምረኛ ገድል
ከአለማውያን እሳት የጦር ነበልባል
ጠላቷን አጥፋላት በበትረ መስቀል
ሲድራቅን ሚሳቅን አብድናጎን ሶስቱን
ቅድስት እየሉጣን ቂርቆስን ሁለቱን
እንደታደግሀቸው አጥፍተህ እሳቱን
ኢትዮጲያን ታደጋት አደራ
ካሰከረው ከጠላት ወረራ
ቀልድ አይወድም ሲባል ቅዱስ ገብርኤል
በዘካርያስ ላይ አፍ ይዟል በቃል
ድንግል ሀርና ወርቅ ፈትላለች በአዋጅ
ለወልድ ሙሉ ልብስ ሆኖ ሊዘጋጅ
መንፈስ ቅዱስ ነበር ድርናማግ አዋሀጅ
ገብርኤልን ልኮ አብስር አለው እንጅ
@kinexebebe
2.9K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 11:10:45 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
መዝሙር እንዴት ማግኘት እችላለው ብለው ተጨንቀዋል።
#እንግዲያውስ
#ሊቀ_መዝሙራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ
#ሊቀ_መዝሙራን_ይልማ_ኃይሉ
#ዘማሪ_አርቲስት_ይገረም_ደጀኔ
#ዘማሪ_ገ/ዮሐንስን_ገ/ፃዲቅ
#ቀሲስ_ምንዴዬ_ብርሀኑ
#ቀሲስ_እንግዳወርቅ_በቀለ
#ዘማሪ_ዲን_አቤል_መክብብ
#ዘማሪ_ዲን_ሮቤል_ማቲያስ
#ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን
#ዘማሪት_አቦነሽ_አድነው
#ዘማሪት_ዶር_ሔለን_ተስፋዬ
እና የሌሎችንም ዘማሪዎች መዝሙሮች ማግኘት ይፈልጋሉ
እንግዲያው ከታች ካሉት ውስጥ መርጠው ይጫኑ
3.2K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 11:08:45 መንፈሳዊ ወቅታዊ ዜና


ትላንት ሰው በተባለች አካባቢ፣በተካሄደው ጦርነት የብዙ ሰው ሂዎት ማለፍ እና ንብረት መውደሙን ተነገረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ትላንት ሰው በተባለች አካባቢ፣ በተካሄደው ጦርነት የብዙ ሰው ሂወት ማለፍ እና ብዙ ንብረቶች ወድመዋል።
ጦርነቱም የተካሄደው፣ ነፍስ እና ስጋ በተባሉት ቡድኖች መሃል ነበረ።
ይሁን እንጂ የእነዚ ሁለቱ ቡድኖች፣ ጦርነት መጋጠም መንስኤው ፣ ልደት እና ሞት በተባሉት ወንዞች መሃል ይምትገኘው፣ ስሟም ሰው ተብላ የምትጠራ ተራራ ላይ ፤ በኔ ጎዛት ስር ትሁን በማለት ፣ሁለቱም ቡድኖች ጦርነት መግጠማቸውን ኑሮ ተናገረች።

ሆኖም ትላንት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከተኩል(2፡30) ላይ የሁለቱም ቡድኖች፤ ጦር መሪዎች ከነ ጦራቸው ወደ ጦር ሜዳ ወረዱ።
ብዙም ሳይቆዩ ጦርነት ተጀመረ፣ጦርነቱም እየተፋፋመ ስሄድ የሁለቱም ጦር አዛዦች ጦርን መምራት ጀመሩ።

ነፍስ የተሰኘው ቡድን ብዙ የጦር አዛዦች አላት፥ከእነዚ መሃል ዋኖቹም፦ጄነራል ፆም,ጄነራል ፀሎት,ጄነራል ስግደት,ኮማንደር መፅዋዕት እና ሺ አለቃ ፅናት ናቸው።
ይሁን እንጂ የስጋ ቡድንም ብዙ ወታደር እና የጦር አዛዦች አሉዋቸው እነሱም፦ጄነራል ልብላው,ጄነራል ትዕቢት,ጄነራል ተንኮል ,ኮረነኤል ቅናት እና ሌሎችም አሉዋቸው ።

ይሁን እንጂ አራት ሰዓት ከተኩል ላይ፣ ከረፋዱ ከልደት ወንዝ ተነስተው ሲዋጉ ሰው ተራራ መሃል ላይ ደረሱ።

ጦርነቱ በጣም እየተፋፋመ ስሄድ፣በሁለቱም ቡድን መሃል ከባድ መሳሪያ ስለ ነበረ፦የሚሳኤል መወንጨፍ የፈንጅ ፍንዳታ በመሬቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረስ ተችሏል ።
በተለይ ከነፍስ ቡድኖች መሃል ፣ በጄኔራል ፆም እና ስግደት የሚመሩ ጦርች አቅም ያላቸው ነበሩ።
ይሁን እንጂ በጦርነት መሃል ፣ የስጋ ቡድን መሬቱ ላይ ትልቅ ጉዳት ስለፈጠረ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ።

ሁሉም ጦርነቱን ትተው ግርግ ጀመሩ፣ብዙም ሳይቆዩ ለነፍስ ቡድኖች መላከ፦ ብርሃን የተሰኝ አየር ተላከ ፣ነፍስ የተሰኝ ቡድንም ጦርነቱን ትቶ፣በግርግሩ መሃል ከተጣሉበት ተራራ ተነስቶ፣ ሞት ወንዝን ተሻግሮ ጠፋ።

ቢሆንም ግን የስጋ ቡድን፣ ከነጦራቸው ሰው በተባለች ተራራ ውስጥ ሰምጠው ቀሩ።
ይቺ ሰው የተባለች ተራራ፣ ከሰው ወታጀሮች ጋር ሰምጣ ለዘላለም አበረው ቀሩ።
ስብሃት ለእግዚአብሔር
@kinexebebe
2.6K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:54:51 ለሐምሌ ሥላሴ ያዘጋጀሁት ግጥማዊ ተዉኔት ነው፡፡ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የኪነጥበብ አገልጋዮች ካላችሁ እስኪ ተመልከቱ፡፡
3.2K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ