2022-06-17 09:06:30
++ ሥነጽሑፍ - ግጥም !
( ርዕስ - ምን አሉ ? )
ምን ነበር ያሉት አበው ሲናገሩ
የታሪክ አደራ የቅርሳቸው ክብሩ
ለምን ነበር ይጨነቁ የነበሩ
ስለምን ነበር ያስቡ የነበሩ
ስጋቸውን ለማስደሰት
ያመረና የጣመ ለመብላት
በእስፕሪንግ አልጋ ላይ ለመተኛት
ቢሮ ተቀምጦ ዳቦ ለመብላት
ባለስልጣን ሆነው ለመታየት
ስለምን ነበር ሲያስቡ የነበሩት
ስለምን ነበር ሲናገሩ የነበሩት
ምን ተብሎ ተጽፎ ስለ እነርሡ ክብር
ምን ተብሎ ታወሰ የእነርሡ ዝክር
ብርሀናው ይውጣ ይነገር ሥራቸው
ዳግም ይነገር ይታይ ውጤታቸው
ብርሀናው ከወጣ ከተፈለገ ሥራቸው
አስታዋሽ ካገኛ ከታየ ሥራቸው
እንዲህ ነበር አበው የታሪክ ገድላቸው
ገና ጉዞውን ሲጀምር የክርስትናውን
ከሰባት ወንድሞች ጋር በአበው የተሾመው
ያ ታለቅ አባት የወንጌል አርበኛው
በአንድ ስብከት 12ሺህ ያተመቀው
ምን አለ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሲወግሩት
ስጋውን ቆራርጠው ደሙን ሲያፈሱት
እንደ ስንዴ ክምር ድንገይ ሲጭኑበት
ስለምን ተናገረ ምና ብሎ መሰከረ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍስን ተቀበል
ጌታ ሆይ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው
ያ አረጋዊ ታላቅ አባት
ጌታን የሚወደው ከሁሉ በፊት
ሲናገር ቀደም ቀደም ብሎ የሚመሠክረው
ከጌታ ስብከት ለአፍታ ያልተለየው
አንተ ከምትሞት እኔ ልሙት ያለው
የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ አደራ የተሰጠው
በጎቹን እንዲያሰማራ ቃል የገባው
ለመሆኑ ምን አለ ጴጥሮስ ያ ታላቁ አባት
ጌታ ሆይ ወዴት ትሄዳለህ ደግመኛ
በሮም አደባበባይ ልሰቀል ሲለው
ጌታ ሆይ አንተ ከምትሰቀል እኔ እሰቀላለሁ
ስለመንግስተ ሠማያት ሲከራከሩ ሀዋሪያት
ጌታችን በምሳሌ የነበረው አቅርቦት
ያ ታናሽ ብላቴና ያልተለየው ከዮሐንስ
የሠማውን ለማስተላለፍ የተሯሯጠው በእግር በፈረስ
ምን አለ አግናጢዎስ ለባሴ እግዚአብሔር ምጥው ለአንበሳ
በትርኢት ቀርቦ በሮም አደባባይ ሲሰዋ
ዛሬ ተረኛ ነኝ በአምላክ እንደንጹህ መገበሪያ ስንዴ ልቀርብ ይገባኛል አለ
በ451 በጉባኤ ኬልቄዶን
እንዲቀበል ተገደደ ሁለት ባህሪይን
በበክርሊያና መለቂያ በሀይል የታዘዘው
ወልድ ዋህድ አንድ ባህርይ ብሎ የመሰከረው
የበርክሊያንና የመርቂልያን ዱላ የጠገበው
በግዞት የተሰደደው
ጥርሱ በግፍ የወለቀው
ፅህሙ በግፍ የተነጨው
ምን አለ ዲዮስቆሮስ ያ ታላቅ ባለሙያ
ምን ብሎ መሰከረ ስለምንስ ተናገረ
ጥርሱንና ጽህሙን በመሀረብ አስሮ ክርስቲያኖች
ይህ የሀይማኖት ፍሬ ነው በርቱ አይዟችሁ
ምን አለች ያቺ ታላቅ እናት
በስጋ ስትኖር ዓለምን የናቀች
ምን ያደርግልኛል ብላ በልጅነቷ የመነነች
የሰውን ልጅ ከአምላክ ለማስታረቅ የበቃች
ደግሞም ሰይጣንን ለማስታረቅ የለመነች
የዓለምን አምልኮት ታግላ ያሸነፈች
ለስጋዋ ሳይሆን ለነፍሷ የቆመች
ለብልጭልጭና ለጌጥ እጇን ያልሰጠች
በአጓጉል ፋሽን ያልተንበረከከች
በስጋዊ ምኞት በሀይሏ የገደለች
ለመሆኑ ምን አለች ክርስቶስ ሰምራ
ዘብሄረ ቡልጋ የኢትዮጲያ የቅርስ አደራ
ሳጥናኤል ሆይ ሳጥናኤል ሆይ ና ውጣ
ከአምላክህ ጋር ላስታርቅህ ማነው
በክብር ስሜ የጠራኝ ብሎ ሲናገር ሚካኤል ደርሶ በሰይፍ መታው
ይህ ነበረ የአበው ገድላቸው
የቅድስና ስራ የክብር ጌጣቸው
ይሄን ነበር ያሉት አበው በቃላቸው
ለትውልድ እንዲተላለፍ የፃፉት በደማቸው
ስጋቸውን ቆርሰው አጥንታቸውን የሰበሰቡት
ህይወታቸውን ለክርስቶስ እንደስንዴ መገበሪያ የሰጡት
ኸረ ዛሬስ ምን አለን እኛ
የአበው ልጆች የተቀበልን አደራ
በእነርሱ እግር ለመተካት የጀመርን ስራ
ምን ነበር ስራችን ጌጥ ክብራችን
ስለምን ነበር ሀሳብ ጭንቀታችን
የእኛ ጭንቀትማ እንደው ከተነሳ
ስጋን ለማስደሰት የምናየው አበሳ
ድንቅና ውብ አድርጎ በፈጠረው አካላችን
ይበልጥ ለማሳመር ስናደርግ አዲስ ፋሽን
ግድግዳ ይመስል ቀለም ስንቀባው
የጠቆረውን ለማቅላት ብራውን እያልን ስንከልሰው
በዓለም ፋሽን ይበልጥ ስናጌጠው
እንደልኳንዳ ቤት ስጋ በመቶ ሻማ ስናሳየው
ይሄ ነው ጭንቀታችን ሀሳብ ክብራችን
ለመሆኑ ምን አላችሁ መናፍቅ ቤታችሁ ሲገባ
ወንጌል ተሰበኩ ብሎ ሊላችሁ አላስወጣ አላስገባ
ምን ብላችሁ መለሳችሁ ስለምንስ አወራችሁ
ጀርመናዊ በንዴ ወንጌልን ለመስበክ ሲመጣ
ከተማራችሁት ውጭ አዲስ ቃል ሲያመጣ
ምን ብላችሁ መለሳችሁት ይህን መናፍቅ
ዘመቻ ተብሎ በአንድ ቃል ሲታወጅባችሁ
መዳን አለባችሁ ተብሎ ሲሰብክላችሁ
ቃሉን አልሰማችሁም ስሙ ስትባሉ
ለመሆኑ ምን አላችሁ
ከአበው አባቶች የተቀበልነውን አደራ
እንድንወጣ አምላክ ይሁን ከእኛ ጋራ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን !
@kinexebebe
2.0K views06:06