2022-06-29 09:55:35
*"የህይወት ስንቅ"*
አንድ ወጣት አንድን ታላቅ አባት ጥሩ
ሰው የሚባለው ምን የሚያደርግ ነው ብሎ ቢጠይቃቸው፤
:
*እኚህ ትልቅ አባትም መልሰው ይኸውልህ ልጄ አንተም ብትሆን ጥሩ ሰው ለመሆን ከፈለግክ ሊኖሩህ የሚገቡ ጉዳዮችን ላስቀምጥልህ ልብ ብለህ አድምጠኝ!!*
:
:::---::::---::::---::::---::::
1. "ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ጥሩ ሰው ማለት ፡-
:
~►ዘወትር ለኃጢአቱ የሚጨነቅና ይቅርታ የሚጠይቅ፤
፡
~►ዘወትር በሥራና በትጋት የተጠመደ፤
፡
~►ከመናገር ዝምታን ገንዘብ
የሚያደርግ፤
፡
~►የፈጣሪን ትእዛዛቱን የሚጠብቅና እራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው በማለት መለሱለት፡፡
:
ዓሣ ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከመንፈሳዊ ሕይወቱ ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡
፡
ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ
ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም በንስሐ ቶሎ ሲመለስ ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል፤
፡
ስለዚህ ንስሐን እንደ ቀላል ነገር አትቁጠረው፤
፡
2 ." መልካምነት ውደድ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ከተሰወረ ፍቅር የተገለጠ ዘለፋ፣ ከጠላት መልካም ሐሳብ የወዳጅ ክፉ ምክር፣ ከራቀ ወንድም የቀረበ ወዳጅ ሳይሻል እንደማይቀር አትዘንጋ፤
፡
መልካም ሞት የመልካም ኑሮ ውጤት ነው፤
፡
አንደበተ ትልቅ ውስጠ ቀላል እንዳትሆን ተጠንቀቅ
፡
3. "በፈጣሪ እንጂ በደጋፊዎች አትተማመን!"
:::---::::---::::---::::---::::
፡
በደጋፊዎች ከተማመንክ ከሰባራ ወንበር ላይ እንደተቀመጥክ ቁጠረው፤
፡
የሰይጣን ደህና ባይኖረውም፣ ብቻውን ካለ ሰይጣን ይልቅ በሰው ላይ ባደረ ሰይጣን ተጠንቀቅ፣ በሰው ላይ ያደረ ሰይጣን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስትለው ከሰውየው ጋር ተጣብቆ ያስቸግራልና፡፡
፡
4 ."ካለፈው ስህተትህ ተማርበት እንጂ አትማረርበት!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሰዎች በአንተ ላይ ምንም እንዳያወሩ ሥልጣን የለህምና፤ የሚሉህን እየሰማህ ስህተትህን አስተካክል፤
:
5 ."አስፍቶ መረዳትን አዳብር!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሌሎች እንዴት ማጥቃት እንዳለብህ
የሚነግርህን ሰው ሌላ ጊዜ እሱ ሲያጠቃህ እንዴት መካለከል እንዳለብህ እየነገረህ እንደሆነ ተረዳው።
:
ሌሎችን ቀርበህ እንዴት እንደምትወድ የሚነግርህን ሰው ግን ለፍቅር እድል ስጠው።
:
6 ." ለመታመን ማመን አለብህ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሰውን ማመን ቀብሮ ነው የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነው።
:
ለማመን ሰው መቅበር ካስፈለገ
የተቀበረን ለማመንም መቀበር ሊያስፈልግ ነው።
:
ሰውን የማምነው ቀብሬ ከሆነ ሌሎችም እኔን የሚያምኑኝ ቀብረውኝ ነው።
:
መኖር ግዴታ በሆነበት ህይወት ውስጥ ሞት መብት አይሆንም።
:
ማንኛውም ሰው ራሱን በህይወት ማቆየት እንጂ ለመሞት ራሱን መግደል አይችልም።
:
ነገር ግን ራስን ለመግደል ቀላል ዘዴ አለ። :
►መጀመሪያ ማሳብ ማቆም።
:
►ቀጥሎ ማሰብ ያቆምከውን አሳብ መኖር።
:
7. "ለማድረግ ተዘጋጅ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ለማድረግ ስታስብ እጥፍ አድርገህ አስብ!"
:
ያሰብከውን ስትተገብር በቁመትህ ልክ አድርግ።
:
ከፍ ባልክ ቁጥር ከፍታህ ቋሚ መድረሻህ አለመሆኑን እወቅ።
:
ወደ ላይ ከፍ ስትል ወደ ታች ተመልከት።
:
በከፍታህ ወቅት ወደታች መመልከትህ ስትወድቅ የምታርፍበትን ምቹ ቦታ እንድትለይ ያደርግሀል።
:
8. "ለችግር የተሸነፍክ አትሁን !"
:::---:::::---::::---::::---:::::
:
በህይወትህ ችግር ሲያጋጥምህ ችግሩን መለየት የመፍትሄ መጀመሪያ መሆኑን ተረዳ።
:
ችግሩን የመለየት መጀመሪያው ደግሞ አንተ ራስህ በራስህ ችግር አለመሆንህ ለይቶ ማረጋገጥ ነው።
:
ሳያልፍ የመጣ ክፉ ነገር የለምና እስኪያልፍ ታገሥ፤
፡
9 ."ትንሽ ለመስጠት አትፍራ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
የስጦታ ዋጋ በተቀባዩ ስሜት እንጂ በስጦታው ይዘት አይወሰንም።
:
ለሰጪው ትንሽ የሆነ ለተቀባዩ ትልቅ ዋጋ አለው።
:
10. "ክብርህን ከምግባርህ እንጂ ከሰው አትጠብቅ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
የምትቀበለው አንተ አስቀድመህ በሰጠኸው ልክ ነውና!
:
ለመከበር ፤ ለመወደድ ፤ ጥሩ ጓደኛ ለማግኘት አንተ አስቀድመህ ሌሎቹን አክብር ፤ ውደድ ፤ጥሩ ጓደኛም ሁንላቸው ምክንያቱም መልካምነት ለራስ ነውና!
:
በህይወታችን ለሰዎች ከክፋት የነጻ
በፍጹም ንጹሕ ልቦና መልካምና ቅን ሆነን እንኖር ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!
@kinexebebe
2.2K views06:55