Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ወቅታዊ ዜና ትላንት ሰው በተባለች አካባቢ፣በተካሄደው ጦርነት የብዙ ሰው ሂ | መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ

መንፈሳዊ ወቅታዊ ዜና


ትላንት ሰው በተባለች አካባቢ፣በተካሄደው ጦርነት የብዙ ሰው ሂዎት ማለፍ እና ንብረት መውደሙን ተነገረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ትላንት ሰው በተባለች አካባቢ፣ በተካሄደው ጦርነት የብዙ ሰው ሂወት ማለፍ እና ብዙ ንብረቶች ወድመዋል።
ጦርነቱም የተካሄደው፣ ነፍስ እና ስጋ በተባሉት ቡድኖች መሃል ነበረ።
ይሁን እንጂ የእነዚ ሁለቱ ቡድኖች፣ ጦርነት መጋጠም መንስኤው ፣ ልደት እና ሞት በተባሉት ወንዞች መሃል ይምትገኘው፣ ስሟም ሰው ተብላ የምትጠራ ተራራ ላይ ፤ በኔ ጎዛት ስር ትሁን በማለት ፣ሁለቱም ቡድኖች ጦርነት መግጠማቸውን ኑሮ ተናገረች።

ሆኖም ትላንት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከተኩል(2፡30) ላይ የሁለቱም ቡድኖች፤ ጦር መሪዎች ከነ ጦራቸው ወደ ጦር ሜዳ ወረዱ።
ብዙም ሳይቆዩ ጦርነት ተጀመረ፣ጦርነቱም እየተፋፋመ ስሄድ የሁለቱም ጦር አዛዦች ጦርን መምራት ጀመሩ።

ነፍስ የተሰኘው ቡድን ብዙ የጦር አዛዦች አላት፥ከእነዚ መሃል ዋኖቹም፦ጄነራል ፆም,ጄነራል ፀሎት,ጄነራል ስግደት,ኮማንደር መፅዋዕት እና ሺ አለቃ ፅናት ናቸው።
ይሁን እንጂ የስጋ ቡድንም ብዙ ወታደር እና የጦር አዛዦች አሉዋቸው እነሱም፦ጄነራል ልብላው,ጄነራል ትዕቢት,ጄነራል ተንኮል ,ኮረነኤል ቅናት እና ሌሎችም አሉዋቸው ።

ይሁን እንጂ አራት ሰዓት ከተኩል ላይ፣ ከረፋዱ ከልደት ወንዝ ተነስተው ሲዋጉ ሰው ተራራ መሃል ላይ ደረሱ።

ጦርነቱ በጣም እየተፋፋመ ስሄድ፣በሁለቱም ቡድን መሃል ከባድ መሳሪያ ስለ ነበረ፦የሚሳኤል መወንጨፍ የፈንጅ ፍንዳታ በመሬቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረስ ተችሏል ።
በተለይ ከነፍስ ቡድኖች መሃል ፣ በጄኔራል ፆም እና ስግደት የሚመሩ ጦርች አቅም ያላቸው ነበሩ።
ይሁን እንጂ በጦርነት መሃል ፣ የስጋ ቡድን መሬቱ ላይ ትልቅ ጉዳት ስለፈጠረ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ።

ሁሉም ጦርነቱን ትተው ግርግ ጀመሩ፣ብዙም ሳይቆዩ ለነፍስ ቡድኖች መላከ፦ ብርሃን የተሰኝ አየር ተላከ ፣ነፍስ የተሰኝ ቡድንም ጦርነቱን ትቶ፣በግርግሩ መሃል ከተጣሉበት ተራራ ተነስቶ፣ ሞት ወንዝን ተሻግሮ ጠፋ።

ቢሆንም ግን የስጋ ቡድን፣ ከነጦራቸው ሰው በተባለች ተራራ ውስጥ ሰምጠው ቀሩ።
ይቺ ሰው የተባለች ተራራ፣ ከሰው ወታጀሮች ጋር ሰምጣ ለዘላለም አበረው ቀሩ።
ስብሃት ለእግዚአብሔር
@kinexebebe