2023-03-02 10:47:07
አንድ ኮርስ ከፈላ እጫራለሁ
አንድ ተማሪ F ክልል ውስጥ ገባ ማለት ለኮርሱ የሚመጥን ምንም ዓይነት or sufficient እውቀት አልሸመተምና ኮርሱን እንደገና መማር ይኖርበታል ማለት ነው ። ኮርሱን ደግሞ መማር የሚችለው በቀጣይ ዓመት ከሚማሩ ታናሾቹ ይሆናል or ደግሞ F ያመጣው ኮርስ ምንም የሚዘጋበት ነገር (pre-request) ከሌለ till graduation ድረስ በፈለገው ጊዜ መማር ይችላል።
የፈላው ኮርስ Major course ከሆነ ሊያስጭር አልያም አንድ ሴሚስተር ሊያስጨምር የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል።
Cases of F
ብዙ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል እኔ ግን እየቸከሉ ፍፁም ባላሰቡት መልኩ ኮርሱ ተበላሽቶ ስለሚያስድነግጣቸው ተማሪዎች ብቻ ትንሽ ልበል ምናልባት ፍሬሾችንና ሌላውንም ነባር ተማሪ ሊጠቅም ስለሚችል
በመጀመሪያ ትምህርታችን ላይ ትኩረት እስካደረግን ድረስ F ምናምን ብዙም አያስጨንቀንም ሆኖም ግን አንዳንዴ ያልጠበቅነው ነገር ሊገጥመን ይችል ይሆናል።
አንድ ሁለት ነጥቦችን ብቻ ልጥቀስላቹህ
የአጠናን ዘዴ
ከElementary ጀምሮ በየጊዜው የተለያዩ ተማሪዎች ላይ ያየሁት ችግር ነው፤ ማንም ከሚያነበው በላይ እያነበቡ ውጤታቸው ግን ከሰው በታች የሚሆንባቸው ተማሪዎች እንደኔ እምነት የአነባበብ stylachew ጤነኛ አይደለም ብዬ አስባለሁ።
ሲመስለኝ ጭንቅላታቸው ጋር ትልቅ ፀብ ውስጥ ተዘፍቀዋል ፤ የማናችንም አእምሮ መጨናነቅ አይሻም እነሱ ደግሞ ከልክ በላይ በማንበብ mindachewn ብዙ busy and stack እንዲያደርግ ፈርደውበታል ።
ለማንኛውም እንደዚ አይነት problem ያለባቹህ ተማሪዎች አነባበባችሁን reform አርጉ ፤
ባያሳምናችሁም አንድ አባባል ልንገራችሁ
*በገለጠ ሳይሆን በተገለጠለት ነው* ይል ነበር ma friend
የመምህራን እንዝላልነት
አንዳንድ የግቢ መምህራን ስለ ተማሪው ምንም ግድ ስለሌላቸው ፈተናውን በሚያርሙበት ጊዜ ወይም ከእርማት በኋላ ግሬድ ሲሰሩ ስለሚሳሳቱ (በቸልተኝነት) በስህተታቸው ምክንያት F ሊፈላ ይችላል so ፈተናችሁን በወቅቱ ማየትና ከተቻለም ፎቶ ማንሳት ይኖርባቹሃል
ፈልገውም ይሁን ሳይፈልጉ ማስኮረጅ
ፈተና በምትፈተኑበት ጊዜ አንዳንድ ተማሪዎች በሚሰሩት ስህተት ምክንያት ከተፈረመባቹህ ፤ በተለይ የውጭ መምህራን ከፈተኗቹህ ለመፈረም ስለሚፈጥኑና እነሱን ለመማፀን የሚሆን እንግሊዝኛም ስለማይኖራቹህ መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል ፤ ፈተናው final exam ከሆነ ምንም ምህረት የሌለው F grade ይደረጋል so take care .
መቼም ስለ F አንስቼ ቀጣዩን ጉዳይ አለማንሳት አይቻልምና አንድ ኮርስ ክፍል በኋላ ምን እንደሚገጥማችሁም መናገር ያስፈልጋል
ግቢ ውስጥ ማንኛውም ኮርስ በየትኛውም ምክንያት ከፈላ ADD and DROP በሚባለው ሲይስተም መፋታት ይቻላል እንጂ ብዙም የሚያሳስብ ችግር አይደለም ብዙ ጊዜ አንደኛ አመት ተማሪዎች ላይ ድንጋጤ ሊፈጥር ስለሚችልና በህይወታቸውም ላይ አስፈላጊ ውሳኔ እንዲወስኑ ሊያነሳሳቸው ስለሚችል ነባር ተማሪዎች ስለዚህ ጉዳይ ቀላልነት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ብትሞክሩ መልካም ነው
ADD and DROP ምን ማለት ነው
ADD and DROP ማለት አንድ ተማሪ F ከፈላበት ወይም ያላጠናቅቀው ኮርስ ሲኖር የሚፈጠር የግቢ ትምሮ process ነው።
DROP ማለት F በማምጣታችን ምክንያት ቀጣይነት ያለውን ኮርስ ወይም የፈላው ኮርስ እንዳንማር የሚዘጋብንን የትምህርት አይነት መጣል(drop) ማድረግ ማለት ነው
ADD ማለት ደግሞ በጣልነው ኮርስ ምትክ ሌላ ተመጣጣኝ credit hour ያለው ኮርስ መውሰድ ማለት ነው
Add የምናደርጋቸውን ኮርሶች የምንማረው ከኛ በላይ ወይም ከኛ በታች ከሚገኙ ተማሪዎች (batch ) ነው።
የማወራው ነገር ለፍሬሽ ተማሪዎች ላይገባቹህ ይችላል፡ ካልገባቹህ የግድ ሁሉም ነገር አሁን ይግባኝ አይባልምና ቀስ በቀስ በጊዜ ሂደት ትደርሱበታላቹህ
እኔ ግን ከ F, ከADD and ከDROP እንዲሰውራቹህ እመኝላቹሃለው ሆኖም ግን ባላሰባችሁት አጋጣሚ ይህን ኮርስ ቢፈላ ብዙም እንዳትረበሹ እጫራለሁ ብላችሁም አታስቡ ሌሎች ኮርሶች ላይ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ሞክሩ
በተለይ አንድ ሴምስተርና ከዛ በላይ ተምራቹህ ግቢ የምትቀይሩ ተማሪዎች add and drop በማድረግ የግቢ ህይወታቹህ አስቀያሚ ሊሆን ስለሚችል ግቢ ለመቀየር ከማሰባቹህ በፊት ስለ ምትቀይሩት ግቢ ሙሉ መረጃ መሰብሰብ ይጠበቅባቹሃል ።
የ amharictutorialclass ቤተሰቦች ስለ F አያሳስባቹህ ኖርማል ስለሆነ አታካብዱት
ማሳሰቢያ
በዚህ ሴሚስተር F ግሬድ የመጣባቹህ ኮርስ ካለ የትምህርት መስክ ምርጫ ከመምረጣቹህ በፊት የምትፈልጉት የትምህርት መስክ ከፈላው ኮርስ ጋር ያለውን ግንኙነት በደንብ አጣርታቹህ ምረጡ
ለምሳሌ Mathematics Ir General Physics F grade ያለው ተማሪ ምህንድስና ለመቀላቀል ከማሰቡ በፊት ቢያንስ በትንሹ ለሁለት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ በ ADD and DROP ዛግ እንደሚል አምኖ መቀበል ግድ ይለዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ እንደየግቢዎቻቹህ የተማሪ ፍላጎት ADD and DROP ማድረጉን ፈልጋቹህ እንኳን የትምህርት መስኩን ብትቀላቀሉ ብዙ ተማሪዎች ማለትም የትምህርት መስኩ ሜጀር ኮርስ ያልተበላሸባቸው ተማሪዎች የመረጡት ፊልድ ከሆነ ላይደርሳቹህ ስለሚችል አደራችሁን በመረጃ ላይ የተደገፈ ምርጫ ለመምረጥ ምክር
ከምህንድስና በተጨማሪም ሌሎች የትምህርት መስኮችን መቀላቀል የምትፈልጉ ተማሪዎች ምናልባት በዚህ ሴሚስተር የተበላሸ ኮርስ ካለባቹህ ከነባር ተማሪዎች ጋር መረጃ ብትለዋወጡ ጥሩ ነው
F ግሬድ አለባቹህ ማለት ወይም ADD and DROP አደረጋቹህ ማለት አንድ ሴሚስተር ወይም ከዚያ በላይ ትጫራላቹህ ማለት አይደለም አልያም ሴሚስተር ትጨምራላቹህ ማለት አይደለም ምክንያቱም በዚህ ሴሚስተር ሜጀር የሚባል ኮርስ ባለመኖሩ ይሁን እንጂ የምትገቡበት የትምህርት መስክ ለቀጣይ ሴሚስተሮች ተጽዕኖ ይኖረዋል ተፅዕኖውም ከላይ የተነጋገርነው ነው።
Physical fitness F ከመጣ ያስጭራል ወይም አንድ ኮርስ ከፈላ ያስጭራል ምናምን ስለሚባሉት የህፃናት ወሬ ጆሮ ሳትሰጡ ስለቀጣይ ኮርሶች በማሰብ ጠንከር ለማለት ሞክሩ
ATC
━━━━━━━━━━━━━━━━━
••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @keleme_2013
@keleme_2013
5.5K views07:47