Get Mystery Box with random crypto!

✞ገድለ ቅዱሳን✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የሰርጥ አድራሻ: @kegdlat
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.13K
የሰርጥ መግለጫ

✝✞ከኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የተገኙ የየዕለቱ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድል ይነገርበታል✝

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-15 06:59:35
141 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 06:59:16 ስንክሳር ዘወርሃ መጋቢት ስድስት(፮)
https://t.me/SinkisarZekidusan2
144 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 06:58:47 1.ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ተአማኒ (ዘቆረንቶስ)
2.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሰማዕት (አማሌቃውያን የገደሉት)
3.አባ ዘሩፋኤል ጻድቅ
4.አባ እንጦንስ ገዳማዊ
5.አባ አርከሌድስ ገዳማዊ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ . . . ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
130 views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 06:58:46 Daniel:
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
††† እንኳን ለቅዱስ ቴዎዶስዮስ ተአማኒ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቴዎዶስዮስ †††

††† በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል:: ከእነዚህ አንዱ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደሆነ በትውፊት ይታመናል:: የጉባዔውስ ነገር እንደምን ነበር ቢሉ:-
የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)

2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)

3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)

4.ቅዱስ ቴዎዶስዮስ (በምድረ ቆረንቶስ መከራን የተቀበለ)

5.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)

6.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)

7.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕፃንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)

8.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)

9.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ: ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)

10.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከሁለቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውንት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በአራቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት::
በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል:: ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

ቅዱስ ቴዎዶስዮስ የቆረንቶስ ጳጳስ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን አሳልፎ ከሰማዕታት ተቆጥሯል:: ነገር ግን አልተሰየፈም ነበርና እስከ ጉባኤ ኒቅያ ቆይቶ የጉባኤው ተሳታፊ ሆነ::

ከጉባኤው በኋላ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ወደ ሃገሩ ቆረንቶስ ተመልሶ : ሕዝቡን ሲመክር ቆይቶ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን::

††† መጋቢት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
129 views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 06:43:32 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ ማክሰኞ መልካም ቀን።
+++
1.1K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 06:42:53
1.1K views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 06:42:16 ገድለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዘወርሃ መጋቢት
https://t.me/SinkisarZekidusan2
1.0K views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 06:41:45 † † እንኳን ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † †

† † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †

† † አቡነ ገብረ ሕይወት † †

† † ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::

የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል?
*እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል?
*ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ:-
*እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና ነውና)::
*ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና)::
*ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት::
*ሃገራችንን አስምረው: አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል::

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም : ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል::

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቅር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ::
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ::
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ::
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ::
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::

††† የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው::

††† ቸር አምላክ ከጻድቁ ዋጋና በረከት ይክፈለን::

††† መጋቢት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ (አባ ገብረ ሕይወት)
2.ቅዱስ አባ ሰረባሞን (በምድረ ግብፅ ምንኩስናን ካስፋፉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ)
3.አባ ግርማኖስ ጻድቅ (ሶርያዊ)
4.ቅድስት አውዶክስያ ሰማዕት (ከከፋ የኃጢአት ሕይወት ተመልሳ ለቅድስና የበቃች እናት)
5.ቅዱሳን ስምዖንና ሚስቱ አቅሌስያ (የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወላጆች)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
4.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

††† "ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" †††
(ማቴ. 10:41)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
964 views03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 05:27:55 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ ሰኞ መልካም ቀን።
+++
726 views02:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 05:27:10
724 views02:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ