Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላማዊ እውነታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamictrueth — ኢስላማዊ እውነታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamictrueth — ኢስላማዊ እውነታ
የሰርጥ አድራሻ: @islamictrueth
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.31K
የሰርጥ መግለጫ

ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-09-10 18:12:48 አስካሪ መጠጥ የጠጣ...

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
https://t.me/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
1.0K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 10:39:58
1.1K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:03:31 "...وَمِنْكُمْ مَنْ يُتَوَفَّى وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَى أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنْ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْئًا..." سورة الحج 5
"…ከናንተም የሚሞት ሰው አለ፤ ከናንተም ከዕውቀት ቡኋላ፣ ምንንም እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ…" (ሱረቱል ሐጅ 5)፡፡

4/ እሱ አስተማሪ እንጂ ተማሪ አለመሆኑ፡- ጌታ አላህ በራሱ የተብቃቃ የዕውቀት ሁሉ ምንጭና አስተማሪ ነው እንጂ ከፍጡራኑ የሚማር ዕውቀትን የሚቀስም ጌታ አይደለም፡፡ እኛ ግን በራሳችን ያልተብቃቃን አስተማሪ የሚያስተምረን መሪ የሚያስፈልገን ተመሪዎች እንጂ ዐዋቂዎች አይደለንም፡-

" الرَّحْمَنُ * عَلَّمَ الْقُرْآنَ * خَلَقَ الْإِنْسَانَ * عَلَّمَهُ الْبَيَانَ " سورة الرحمن 3-1
"አል-ረሕማን፤ ቁርአንን አስተማረ። ሰውን ፈጠረ። መናገርን አስተማረው።" (ሱረቱ-ራሕማን 1-3)፡፡

"...وَأَنْزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُنْ تَعْلَمُ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا " سورة النساء 113
"…አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፤ የማታውቀዉንም ሁሉ አስተማረህ። የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 113)፡፡

" قُلْ أَتُعَلِّمُونَ اللَّهَ بِدِينِكُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ " سورة الحجرات 16
"አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ ሲኾን አላህን በሃይማኖታችሁ ታስታውቁታላችሁን? በላቸው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።" (ሱረቱል ሑጁራት 16)፡፡

" وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُوحِي إِلَيْهِمْ فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِنْ كُنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ " سورة النحل 43
"ከአንተም በፊት ወደነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤ የማታውቁም ብትሆኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ።" (ሱረቱ-ነሕል 43)፡፡

በአላህ ፍቃድ ክፍል 2 ይቀጥላል

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
https://t.me/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
1.4K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:03:31 ከዘማናዊ ጥንቁልና እንጠንቀቅ!

ክፍል አንድ

በፊት በፊት እገሌ ሼህ የሩቅ አዋቂ ነው እየተባላ በየጉራንጉሩ ሰዎች ይጎርፋሉ፤ አሁን ላይም ባይቀርም። በአሁን ሰአት ግን ዘምኖ በቴክሎጂ ብቅ ብለዋል።

ይህንን አሳሳቢና ወሳኝ መልእክት በትኩረት ያንብቡ!

ቴክሎጂ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጉዳትም አለው። ስለ ጥቅሙ ተጠቃሚዎቹ ስለሚያውቁት በሱ ቢዚ አናደርጋቹም። ነገር ግን ከጉዳቶቹ መሀል ግን የተወሰኑትን እናሳውቃቹሀለን። መቼ እንደምትሞት የሚናገሩ፣ በዚህ እድሜ ላይ ምን እንድምትመስል የሚናገሩና መሰል ከአላህ በስተቀር የማይታወቅን ነገር እናውቃለን የሚሉ ቴክኖዎሎጂዎች ብቅ ብለዋል። ይህ ተግባር በኢስላም ምንም ጥርጥር የሌለው ወንጀል ነው። ምክንያቱም ደግሞ በተለያዩ የቅዱስ ቁርአን አንቀፅ ላይ የሩቅን አዋቂ እራሱ ብቻ እንደሆነ ይናገራል። ለዚህም መረጃ በውዱ ኡስታዛችን አቡ ሀይደር የተፃፈውን ድንቅ ፁሁፍ በሁለት ክፍል አድርገን እናስነብባቹሀለን። በትእግስት ሙሉ ፁሁፉን ያንብቡ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን። ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡

ከፈጣሪ አምላካችን አላህ መለኮታዊ ባሕሪያት መካከል አንዱ ‹‹ሁሉን ዐዋቂነት›› ነው፡፡ ከጌታ አላህ ስሞች አንዱ ‹‹አል-ዐሊም›› የሚለው ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ ትርጉሙም፡- ሁሉን ዐዋቂ ማለት ነው፡፡ አላህ ከዚህ በፊት የተፈጸመና የሆነን ነገር፣ አሁን እየተፈጸመና እየሆነ ያለን ነገር፣ ገና ያልተፈጸመና ወደፊት ሊመጣ ያለን ነገር ሁሉ ያውቃል፡፡ ያም ብቻ አይደለም፡፡ የማይሆን ነገር ራሱ የመሆን ዕድል ቢሰጠው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ለዕውቀቱ ምንም ገደብ የለውም፡፡ ጌታ አላህ ከርሱ የሚሸሸግና የሚሰወር አንዳችም አይነት እንቅስቃሴ ስለሌለ "አል-ዐሊም" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በደረቶቻችን ውስጥ በልብ ያሰብነውን በአንደበታችን የምንገልጸውንና በስራ የምንተገብረውን ገና ከመከሰቱ በፊት ቀድሞ ስለሚያውቀው "አል-ዐሊም" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በዕውቀቱ ፍጡራንን በመላ ያካበበ በመሆኑ "አል-ዐሊም" ይባላል፡፡

ሰዎች በዚህ ምድር ላይ በተሰጣቸው ዕውቀት "ዐሊም" ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ (ሱረቱ ዩሱፍ 55.68፣ ፋጢር 28) ፡፡

ነገር ግን የጌታችን አላህ ዕውቀት ፈጽሞ ከፍጡራኑ ጋር እንደማይገናኝ ለመረዳት የተወሰኑ ነጥቦችን እንመልከት፡-

1/ ያልተገደበ መሆኑ፡- አምላካችን አላህ ዕውቀቱ ያልተገደበ፣ በጊዜና በቦታ ያልተወሰነ ሁሉንም ያካተተ ያለፈውንና የአሁኑን እንዲሁም መጪውን ነገር ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን፤ ፍጡራን ግን ዕውቀታቸው ውስን በጊዜና በቦታ የተገደበ እየሆነ ካለው ነገር አጠገባቸው ያለውን እንጂ የራቀውን የማያውቁ፣ መጪውን ነገር ፈጽሞ ሊያውቁ የማይችሉ ናቸው፡-

"...يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ..." سورة البقرة 255
"…(ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)…" (ሱረቱል በቀራህ 255)፡፡

" اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا " سورة الطلاق 12
"አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፤ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፤ አላህ በነገር ሁሉ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)።" (ሱረቱ-ጦላቅ 12)፡፡

" وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُمْ مِنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا " سورة الإسراء 85
"ከሩሕም ይጠይቁሃል፤ ሩሕ ከጌታዬ ነገር (በዕውቀቱ የተለየበት) ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።" (ሱረቱል ኢስራእ 85)፡፡

2/ መሐይምነት ያልቀደመው መሆኑ፡- አምላካችን አላህ በባሕሪው ጥንትም ዘላለምም ዐዋቂ ጌታ ነው፡፡ ለህልውናው ጅማሬ እንደሌለው እንዲሁ ለዕውቀቱም መነሻ የለውም፡፡ የሱ ዐዋቂነት ካለማወቅ ቡኋላ የመጣ ሳይሆን ከራሱ ባሕሪይ ጋር አብሮት የነበረ ነው፡፡ የፍጡራን ዕውቀት ግን መነሻቸው ጅህልና ነው፡፡ ማንኛውንም ነገር የምናውቀውና የምንረዳው ካለማወቅ በኋላ ነው፡፡ ዐዋቂ ሆኖ የሚፈጠር የለም፡-

" وَاللَّهُ أَخْرَجَكُمْ مِنْ بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ " سورة النحل 78
"አላህም ከናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፤ ታመስግኑም ዘንድ ለናንተ መስሚያን፣ ማያዎችንም፣ ልቦችንም አደረገላችሁ።" (ሱረቱ-ነሕል 78)፡፡

" الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ * عَلَّمَ الْإِنْسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ " سورة العلق 5-4
"ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን።" (ሱረቱል ዐለቅ 4-5)፡፡

3/ የማይቀያየር መሆኑ፡- ጌታ አላህ ዕውቀቱ ሁሉን ያካበበና መነሻም የሌለው ነው ብለናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ የማይቀያየር ነው እንላለን፡፡ ማለትም፡- መርሳትና መዘንጋት፣ የዕውቀት መጨመርና መቀነስ የመሳሰሉት የመለዋወጥ ባሕሪያት እሱ ዘንድ አይጠጉም፡፡ ፍጡራን ግን ዕውቀታቸው ተለዋዋጭ ነው፡፡ ያውቁት ከነበረው ብዙውን ይረሳሉ፡፡ ሌላ አዳዲስ ዕውቀት ይቀስማሉ፡፡ ወደ እርጅና ዕድሜ ሲሄዱ ደግሞ ምንም ወደ-አለማወቅ ይመለሳሉ፡-

" وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَلِكَ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا " سورة مريم 64
"(ጂብሪል፤ አለ) በጌታህም ትእዛዝ እንጂ አንወርድም፤ በፊታችን ያለው ቡኋላችንም ያለዉ፣ በዚህም መካከል ያለዉ ሁሉ የርሱ ነው፤ ጌታህም ረሺ አይደለም።" (ሱረቱ መርየም 65)፡፡

" قَالَ فَمَا بَالُ الْقُرُونِ الْأُولَى * قَالَ عِلْمُهَا عِنْدَ رَبِّي فِي كِتَابٍ لَا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنْسَى " سورة طه 52-51
"(ፈርዖንም) የመጀመሪያይቱ ዘመናት ሕዝቦች ሁኔታ ምንድን ነው? አለ። (ሙሳም) ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሃፍ የተመዘገበ ነው፤ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም አለው።" (ሱረቱ ጣሀ 51-52)፡፡
1.2K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:03:27
1.1K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 11:37:30
1.3K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 14:35:57 የጦርነት ዉጤት ይሄ ነዉ!!!
804 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 14:35:39
812 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 20:26:55
የ ዶ/ር ሸይኽ ሙሃመድ ሓሚዲን ስራዎች ይቀርብበት የነበረው "ሱና መልቲሚድያ" ሃክ በመደርጉ ምክንያት አዲስ ዩቲዩብ ቻናል ለመክፈት ተገደዋል። አዲሱን ቻናል ሰብስክራብ በማድረግና በመቀላቀል ጠቃሚ ትምህርቶችን ይቋደሱ። ሼር በማድረግም ሌሎች እንዲቀላቀሉት ይጋብዙ።



621 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 20:23:24 ከአብደላህ ኢብን ኡመር በተወራ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

‏( ﻣَﻦْ ﺣَﻠَﻒَ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻘَﺪْ ﺃَﺷْﺮَﻙَ ‏
(ከአላህ ውጪ ባለ አካል የማለ ርግጥም አጋርቷል)
[አቡ ዳውድ 3251 አልባኒ ሰሒሕ ብለውታል]

https://t.me/islamictrueth
742 views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ