2022-06-30 22:08:44
በቀላል ስራ እጅግ በጣም ብዙ ምንዳعن أوس بن أوس الثقفي قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول : «من غسل يوم الجمعة واغتسل ، ثم بكر وابتكر ، ومشى ولم يركب ، ودنا من الإمام ، فاستمع ولم يلغ ، كان له بكل خطوة عمل سنة ، أجر صيامها وقيامها » رواه وأبو داود وغيره وصححه الألباني
አውስ ኢብኑ አውስ አስ–ሠቀፍይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ረሱልን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ይላሉ:-
«የጁሙአ ቀን እራሱን እና የቀረ ሙሉ ሰውነቱን የታጠበ ቀድሞም በወቅቶ (ወደመስጅድ የሄድና) የመጀመሪያውንም ኹጥባ ያገኘ (ምንም) ነገር ሳይጋልብ በግሩም የሄደ ወደ ኢማሙ የቀረበ ኹጥባም ያዳመጠ ያላወራ (ወደ ጁሙዐ ሲሄድ) በተራመድው እርምጃ ልክ የአንድ አመት ስራ የፆሟና የለይል ሶላቷ ምንዳ ይኖረዋል »
[አቡ ዳውድ እና ሌሎችም አውርተውታል] [አልባኒ ሶሒሕ ነው ብለዋል]
በሐድሱ ላይ የጁመዐ ቀን እንድንፈፅመው የታዘዝናቸው ነገሮች አምስት ናቸው። እነርሱም
1, ከራሳችን ጋር ሙሉ ሸዋር መውሰድ
2, ወደ መስጅድ ቀደም ብሎ መሄድ ኢማሙ ኹጥባ ሲጀምር እኛ እዛው መገኘት አለብን ምክኒያቱም የመጀመሪያ ውን ኹጥባ ማዳመጥ እንዳለብን ስለተጠቀሰ
3, ወደ መስጅድ ሲሄዱ እንስሳም ሆነ መኪና ወይንም ሌሎችን የመጓጓዧ አይነቶች ሳይጠቀሙ በእግር ወደ ጁሙዓ መሄድ
4, ወደ ኢማሙ መቅረብ ( ብዙ ሰዎች ወደ ጁሙዐ ከሄዱ በሇላ ከመስጅድ በረንዳ ላይ ወይንም ወደ መጨረሻ አከባቢ በመቀመጥ ያወራሉ እሄን ማድረግ እንድህ ያለ ትልቅ ምንዳን ስለሚያሳልፍብን ጥንቃቄ ልና ደርግ ይገባናል)
5, ወሬም ሆነ ሌሎች ውድቅ የሆኑ ኹጥባ ከማዳመጥ ቢዚ ሊያደርጉን የሚችሉ ተግባሮችን ሳይፈፅሙ ኹጥባ ማዳመጥ
እነዚህን አምስት ተግባር የጁሙዐ ቀን በትክክል የፈፀመ ሰው በተራመደው በእያንዳንዱ እርምጃ በአንድ አመት ቀኑን በፆም ሌቱን በሶላት አሳልፎ የሚገኘውን ምንዳ ያስገኛል
ይህ የአላህ እዝነት ነው እንጅ አንድ አመት ሙሉ አንድም ቀን ሳያቋርጡ ቀኑን በፆም ሌቱን በሶላት ማሳለፍ ይከብዳል በታሪክም ማንም ቢሆን አድርጎት አያውቅም ግን ተግባሩ ከባድ ቢሆንም አዛኙ ጌታችን በቀላል ስራ የዚህን ከባድ ስራ አጅሩን የምናገኝበት መንገድ አምቻቸልን
እንደውኩ በአንድ ጁሙዐ የአንድ አመት ሌቱን በሶላት ቀኑን በፆም ያሳለፈ ምንዳ ነው የምታገኙት ቢባል ለራሱ እጅግ ብዙና ገራሚ ነበር ግንሳ ከቤታችን ተነስተን መስጅድ እስከምንደርስ ድረስ በተራመድነው እያንዳዱ እርምጃ አመቱን ሙሉ ቀኑን በፆም ሌቱን በሶላት ያሳለፈውን ምንዳ ነው የምና ገኘው። ሱብሓነሏህ!!
ወንድሜ እሰበው:- ከቤትህ ጁሙዐ እስተምትሰግድበት መስጅድ ድረስ ያለው ርቀት 500 እርምጃ የሚያስኬድ ቢሆን በውስጡ ምንም ሀጢአት ሳይኖርበት ሌቱ ሶላት ቀኑ ፆም ተፆሞ የሚገኘውን የ 500 አመት አጅር ታገኛለህ ማለት ነው። በወር የ 2000 አመት አጅር ታገኛለህ ማለት ነው።
እኔ እዚህ ላይ የጠቀስኩት ቁጥር እንደምሳሌ ነው እንጅ ርቀቱ ከዚህም በላይ ከጨመረ ይጨምራል
ማሳሰቢያ: የሐዲሱን አንዳድ ቃሎች ሲፈስሩ ዑለሞች የተወሰነ ተለያይተዋል እኔ እዚህ ላይ ስተረጎም የተጠቀምኩት ሸይኽ ሙሐመድ ዒሊ አደም አል ኢትዮጲይ (ረሒመሁሏህ) ዘኺረቱል ዑቅባ ላይ እሄን ሐዲሥ ሲያብራሩ ከእያንዳዱ ልዩነት በሗላ እርሳቸው የመረጡትን ነው የተጠቀምኩት
እድሚያችን አጭር ቢሆንም በቀላል ተግባር የብዙ አመት አጅር እንድናገኝ ያምቻቸልን አላህ ምስጋና ይገባው ወንድማችሁ/ ኢብኑ ሙሐመድዘይን
(ሸዋል 5/1443 ሂ)
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn
255 views∂єαтн ıs яєαł αη∂ яєsυяяєcтıση ıs яєαł , 19:08