Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamicpos1 — ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamicpos1 — ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
የሰርጥ አድራሻ: @islamicpos1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.92K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-29 20:52:13 BREAKING:

የዙልሒጃ ወር ጨረቃ በሳዑዲ ዓረቢያ በመታየቷ ምክንያት ነገ ሐሙስ ሰኔ 23 የዙል ሒጃ የመጀመሪያ ቀን መሆኑ ተረጋግጧል።

በዚህም መሰረት

የዐረፋ ቀን አርብ : አርብ ሐምሌ 1 , 8 July 2022

ዒደል አድሀ : ቅዳሜ ሐምሌ 2 , 9 July 2022
420 views∂єαтн ıs яєαł αη∂ яєsυяяєcтıση ıs яєαł , 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:56:48 የዚልሂጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ታላቅነት

 አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የማለባቸው ቀናት መሆናቸው

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَالْفَجْرِ ﴿١﴾ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴿٢ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ

 
“በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም። በጥንዱም በነጠላውም።”
 (አል-ፈጅር 89፤ 1-3)

ከጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ
(صلى الله عليه وسلم)
እነኚህ አሥር ቀናቶች የትኞቹ እንደሆኑ በሚያመላክተው ሀዲሣቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-

《العشر عشر الأضحى، والوتر يوم عرفة، والشفع يوم النحر》

“አሥሩ ማለት አሥሩ የአድሃ ቀናት ናቸው። ‘ወትር’ /ጥንዱ/ የተባለው የዐረፋ ቀን ሲሆን ‘ሸፍዕ’ /ነጠላው/ ማለት ደግሞ የነህር /የእርዱ/ ቀናት ናቸው።” ብለዋል። ኢማም ነሣኢ እና ሃኪም በሙስሊም ሰሂህ ሀዲስ ነው ብለውታል።

ኢማም በይሀቂ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንደዘገቡት ደግሞ:-

《ليالٍ عشر، العشر الثماني، وعرفة، والنحر》
“አሥርቱ ሌሊቶች የመጀመሪያዎቹ ስምንቶቹ፣ የዐረፋ ቀን እና የእርድ ቀን ናቸው።” ብለዋል።
611 views∂єαтн ıs яєαł αη∂ яєsυяяєcтıση ıs яєαł , 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 22:00:19 የዙል ሒጃ አስሩ ቀን

‏قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله :

وَاسْتِيعَابُ عَشْرِ ذِي الْحِجَّةِ بِالْعِبَادَةِ لَيْلًا وَنَهَارًا أَفْضَلُ مِنْ جِهَادٍ لَمْ يَذْهَبْ فِيهِ نَفْسُهُ وَمَالُهُ ، وَالْعِبَادَةُ فِي غَيْرِهِ تَعْدِلُ الْجِهَادَ لِلْأَخْبَارِ الصَّحِيحَةِ الْمَشْهُورَةِ:. ‏
الفتاوى الكبرى : (343/5)

ሸይኹል ኢስላም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል፦
"የዙል ሒጃ አስሩ ቀን ለሊቱንም ቀኑንም በዒባዳ ማሳለፍ ነፍስና ገንዘብ ካልሄደበት ጂሃድ ይበልጣ። ዒባዳ ከእነዚህ ቀኖች ውጪ ጂሃድን ይስተካከላል ሶሂህ የሆኑና የታወቁ መረጃዎች ስለመጡ"

http://t.me/bahruteka
372 views∂єαтн ıs яєαł αη∂ яєsυяяєcтıση ıs яєαł , 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 21:54:13 "ሀጅ" የምህረት በር

የኢስላም መሰረት ነው ለአማኞች በረከት
መሰብሰቢያ የሆነ ለሙስሊም ሙስሊማት
አላህ የወፈቀው እድሜንም ያደለው
ብዙ ሙእሚን አለ ቤቱን የጎበኘው
ካእባ ላይ ጧፍ አርገን እንባ እናነባለን
ጌታየ ሆይ ማረኝ ስንል እንለምናለን
ሰፋ እና መርዋንም እንዞራቸዋለን
ሰባት ጊዜ ያክል ተመላላሽ ሆነን
ትልቅ ቦታ ናቸው ካእባ ሙዝደሊፋ
የሀጁ ውብ ገፆች ሚና እና አረፋ
ሙዝደሊፋ ሂደን ጠጠር እንይዛለን
ጀመራት ላይ ስንደርስ እንወረውራለን
ሸይጣንን አባረን ለበይክ እንላለን
ደጋግመን ደጋግመን አቤት እንላለን
በአማኞች ይሞላል የአረፋ ተራራ
ደምቆ ና አሸብርቆ ከተክቢራው ጋራ
ከአረብ እስከ ሃበሻ ከነጭ እስከ ጥቁር
አንድ ላይ በመሆን በዚች ታላቅ ምድር
ለበይከ ያ ረቢ ብለው ይጮኻሉ
ወንጅልን መማርን አብዝተው ይሻሉ
ሀጅን የፈፀመ ያላንዳጅ ማጓደል
እልፍ ወንጀሎቹ ይሠረዙለታል
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ወንጀሉ ይጠፋል
በምህረት ተውቦ አርካኑን ይሞላል።
328 views∂єαтн ıs яєαł αη∂ яєsυяяєcтıση ıs яєαł , 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 08:26:52 በቆነጅዬ ድምፀ የጥዋት ዚክር
ተጋበዙልኝ
388 viewsعامي ami, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ