Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamicpos1 — ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamicpos1 — ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
የሰርጥ አድራሻ: @islamicpos1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.92K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-24 20:54:56 የጂል ቀልድ አትቀልድ!
~
በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣… ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም]

በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።"
አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው በምርም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 30/2010)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
194 viewsamir عمير, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:43:03 የስልክ አጠቃቀማችንን እናሳምር !

ሣይታሰብ ሊመጣ የሚችለውን ሞት እናስታውስ! ነገ ሟቾች ነን!

ጨለማውን ቀብር እናስታውስ !

አጠገባችን ማንም፣ ምንም ሣይኖር አሏህ ፊት መቆም አለ !

የማይቻለው ና ከባድ የሆነው የእሳት ቅጣት አለ !

ከዚህም ጋር ፣ ሐራም ነገርን በመመልከትና በመስማት ደስተኛ ህይወትን መግፋት በፍፁም አይታሰብም ! በአምላክህ ላይ አመፀኛ እየሆንክ ደስታን እጎናፀፋለሁ ማለት ቂልነት ነው!


አሏህን እንፍራ !

ስልኮቻች የተከለከሉ ነገሮችን መስሚያ ና መመልከቻ ከሚሆኑ ከነ አካቴው አለመጠቀሙ ይሻላል !


https://t.me/Muhammedsirage
150 viewsamir عمير, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 07:54:55 #ቡሔ_የኛ_አይደለም__!!
❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞❞
ገና ህፃን ሳለሁ አባዬ ሲነግረኝ
አሊፍ ባ ታ ብሎ ቁርዐን ሲያስተምረኝ፡
ቡሔንም የዛን ለት አስታውሶ መክሮኛል፡
የአማራ በአል ነው ተጠንቀቅ ብሎኛል፡
ከዚያን ጊዜ ወድህ አልሀምዱ ሊላሒ፡
አንቅሬ ተፋሁት አስጠላኝ ወላሒ፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ስለዚህ እንበርታ በኢስላም እንፅና፡
አይጠቅመንምና አጉል ፍልስፍና፡
በቀጥታ እንጓዝ በተውሒዲ በሱና፡
በነብያት ፈለግ በጠራው ጎዳና፡
እምነትህን እወቅ አሊም ሆንክ ሙሔ፡
ጂራፍ አትተብትብ ለክርስቲያን ቡሔ፡
በአላት ከፈለክ ሁለት ኢድ አለልህ፡
የአርሹ ባለቤት የደነገገልህ፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ኢስላምን እንወቅ ሙስሊሞች እንንቃ፡
ግፍና መከራው ጭቆና እንዳበቃ፡
የክርስቲያን በአል ወርሰን ከምንጨፍር፡
ምናለ ብንቶብት አሏህን ብናፍር፡
ከሌሎች እምነት ላይ ጥመት እያመጣን፡
ክህደት በመፈፀም ከምንሆን ሰይጣን፡
አሏህም በወንጀል ወስኖ ሳይቀጣን፡
አንመለስም ወይ ከዚህ መጥፎ ተግባር፡
አይቀርብንም ወይ ሬስቶራንትም ባር፡
ቡሔ ነው እያሉ ቢራ ከመጠጣት፡
ክህደት ከመፈፀም ራስን ከመቅጣት፡
ቡሔ እሚባል በዐል በኢስላም እንደሌለ፡
ቁርዐን ሀዲሱ ተናግሯል አይደለ..!!?
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ታዲያ ለምን ይሆን መተው ያቃተን፡
ዱንያ አሸንፎን ነው አኸይራን ረስተን!?
ድንገት እንደተኛን ሞት ቢመጣ
በአፄው ስርዐት በጭቆናው ዘመን፡
እውነተኛ ሲሞት ውሸታም ሲታመን፡
የዛን ሰአት ነበር
#ቡሔን_የጫኑብን
ክህደታቸውን ያስተላለፉብን፡
አሁን ግን በንቃት መጠንቀቅ አለብን፡
በእስልምናችን እንድህ አይነት የለም፡
የነርሱ ነው እንጂ ቡሔ የኛ አይደለም፡
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
#በኑረዲን_አል_አረቢ__!!
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
174 viewsamir عمير, 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 22:11:44 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

የሙሃረም 9ኛው ቀን እሁድ ነሀሴ 1 ሲሆን የአሹራ ቀን ደግሞ( 10ኛው የሙሃረም ቀን) ሰኞ ነሀሴ 2 ይሆናል ማለት ነው
ከአይሁዶች ጋር ላለመመሳሰል ከቻልን ሁለቱንም ቀኖች እንፁም ሁለቱንም ካልቻልን 10ኛውን የአሹራን ቀን እንፁም! 10ኛው የአሹራን ቀንን መፆም የ 1 ዓመት ወንጀልን ያስምራል።

ሁላችንም እንፁም ሌሎችንም በማስታወስ ባስታወስናቸው ሰዎች ቁጥር አጅርን እንፈስ አላህ ያድርሰን!
283 viewsamir عمير, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 20:50:25
የፎቶ ሱስ ያለባችሁ ይችን ነሲሃ ስሟት ከሼይኻችን አሏህ ይጠብቃቸው

اقوال علماء السلف

https://t.me/As_Sunah_Yeruqa_telegramgroup

https://t.me/As_Sunah_Yeruqa_telegramgroup
371 viewsamir عمير, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 21:17:19
ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ ባረከላፊኩም
72 views ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆᎩᗴ ᗩᗰᑌ ᗩᗰᏆᎩᗩ ᗩᗰᏆᖇᝪ ᗩᗰᏆᖇᗩ ᗩᗰᑌᎢᏆ ᗩ, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:11:23 ታላቅ የሆነ ምንዳ እንዳያመልጣችሁ!!
የዚል-ሒጃ 9ኛው ቀን የውሙ ዐረፋ ፆም
–––––
አላህ ባሪያዎቹን በብዛት ነፃ የሚያወጣበት ታላቅ የሆነ የዐረፋ (ዙልሂጃ 9ኛው) ቀን ነው

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“አላህ ባሪያዎቹን በብዛት ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት እንደ ዐረፈ ቀን አንድም ቀን የለም!…” [ሙስሊም ዘግበውታል]

የዐረፋን (ዚል-ሂጃ 9ኛውን) ቀን መፆም ያለፈውን 1 አመት እና የቀጣዩን 1 አመት ወንጀል ያብሳልና የነገው እለተ ጁምዓ 9ኛው የዚል-ሒጃ ቀን ነውና ፆሙ እንዳያመልጣችሁ!!

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ እለተ ዐረፋ ጾም ተጠይቀው እንዲህ በማለት መለሱ:- "ያለፈውን እና የቀጣዩን አመት ወንጀል ያስምራል (ይሰርዛል)።” [ሙስሊም ዘግበውታል]

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህም ብለዋል:-
“የዐረፋን ቀን መፆም ከፊቱ ያለውን አንድ አመት እና ከኋላው ያለውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አድርጋለሁ።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 3853]

ምርጥ (በላጭ) ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነውና ነገ ፆመኛ የሆነችሁም አጋጣሚ በበሽታና መሰል ከባድ ምክንያቶች መፆም የማትችሉም ካላችሁ ዱዓ ላይ በርቱ!!

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“ምርጥ (በላጭ) ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው፣ ከተናገርኩት ነገር ሁሉ በላጩ እኔና ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት የተናገሩት ላ! ኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ! ሸሪከ ለሁ, ለሁል ሙሉኩ, ወለሁል ሀምድ, ወ ሁዋ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር (የሚለው) ነው!!። ትርጉሙም:- ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም! እርሱም ብቸኛ ነው፣ ለእርሱም ምንም ተጋሪ የለውም!፣ ንግስናም ለእርሱ ነው፣ ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ነው፣ እርሱም በሁሉ ነገር ላይ ቻይ የሆነ ነው።” (የሚለው ታላቅ የሆነ የተውሒድ ቃል ነው) [ትርሚዚይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ነው ብለውታል።]

ነገ እለተ ጁምዓ ሐምሌ 1/2014 ዚል-ሒጃ 9ኛው የዐረፋ ቀን ነውና አደራ በፆሙም በዱዓውም አትዘናጉ!!
ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
233 views ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆᎩᗴ ᗩᗰᑌ ᗩᗰᏆᎩᗩ ᗩᗰᏆᖇᝪ ᗩᗰᏆᖇᗩ ᗩᗰᑌᎢᏆ ᗩ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:56:11 #የአረፋ ቀን ፆም!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።
178 views ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆᎩᗴ ᗩᗰᑌ ᗩᗰᏆᎩᗩ ᗩᗰᏆᖇᝪ ᗩᗰᏆᖇᗩ ᗩᗰᑌᎢᏆ ᗩ, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:18:21 ሱብሀነላህ

ሀቢቢ ልንገርህ ሀጢያት ወይም ወንጀል በ አላህ ሲታይ

በመጀመሪያ ጥያቄ ልጠይቃችሁ በፍጥነት መልሱልኝ

1.ሀሽሽ መሸጥ መጥፎ ነዉ ጥሩ??መጥፎ
2.ሰዉ መግደል መጥፎ ነው ጥሩ??መጥፎ
3.ዝሙት መስራት መጥፎ ነዉ ጥሩ??መጥፎ
4.ህጻናት መግደልስ>> >>??መጥፎ
5.አልኮል መጠጣትስ >> >>??መጥፎ
6.ከባድ ወንጀል መስራትስ ...??መጥፎ

አንድ ሰው ይህን ሁሉ ሀጥያት ቢሰራ
እነዚህንም ሁሉ ሃጥያቶች በየጊዜው ቢሰራቸው ነገር ግን ሰላት የሚሰግድ ከሆነ ከነ ሀጢያቱ አላህ ዘንድ የተሻለ ነዉ ምንም ወንጀል ሳይሰራ ከማይሰግደዉ

አንተ ዛሬ ጥሩ ሰው ነኝ ብለህ ታስባለህ የ ቂያማ ቀን ግን እሱ አይሰራም .

ማንኛውም ሰው ያለ ምንም ምክንያት ሰላትን ከተወ ከ ገዳይ በላይ ነህ
ከ ደፋሪ በላይ ነህ
ከ አሸባሪ በላይ ነህ...
በ አላህ ዘንድ።


እህት ወንድሞች አንድ ነገር ልበላችሁ
የሰው ልጅ ያለ እጅ መኖር ይችላል
ያለ እግር መኖርም ይችላል
ያለ አይን >> >>
በ አንዱ ኩላሊትም መኖር ይችላል
ነገር ግን ያለ አንገት መኖር አትችልም
ሰላትን የማይሰግድ ሰው ማለት ልክ አንገት እንደሌለው ሰው ነው ።
356 views ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆᎩᗴ ᗩᗰᑌ ᗩᗰᏆᎩᗩ ᗩᗰᏆᖇᝪ ᗩᗰᏆᖇᗩ ᗩᗰᑌᎢᏆ ᗩ, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:42:34 5ኛ ሺርክ ስንኝ
303 views ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆ ᗩᗰᏆᎩᗴ ᗩᗰᑌ ᗩᗰᏆᎩᗩ ᗩᗰᏆᖇᝪ ᗩᗰᏆᖇᗩ ᗩᗰᑌᎢᏆ ᗩ, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ