2020-11-22 10:39:33
ሕይወት እና ወቅቶች!
ቀን- 29
በድሮ ጊዜ 4 ልጆቹን አንድ ትምህርት ሊያስተምር የፈለገ አባት ልጆቹን እሩቅ ቦታ ያለችን አንድ የኮክ ተክል ሄደው እዲያዩ አዘዛቸው::
ታድያ ይሄን እንዲያደርጉ ያዘዛቸው በተለያየ ወቅት ነበር::የመጀመርያው ልጅ በክረምት(በበረዶ) ነበር የተላከው ፣ሁለተኛው በፀደይ፣ ሶስተኛው በበበጋና ፣ አራተኛው ደግሞ በመኸር ወቅት ነበር::
በጨረሻም አባትየው አንድ ላይ ሰብስቦ ስላዩት ዛፍ እንዲነግሩት ጠየቃቸው:: እንዲህም ሲሉ ነገሩት...
የመጀመሪያው - በጣም የሚያስጠላ ዛፍ ነው ፣አንድ ቅጠል እንኳን የሌለው የተጣመመ ዛፍ ነው አለ
2ኛው - በአረንጓዴ እንቡጦች እና አበቦች የተሞላና ተስፋ የሚሰጥ ዛፍ ነው...
3ኛው- የፈኩ አበቦች ያሉበትና ለአከባቢውም ጥሩ ማኣዛ ሚሰጥ በጣም የሚያምር ዛፍ ነው...
4ኛው - እኔ ያየሁት ግን በበሰሉና በተንዥረገጉ ፍሬዎች የተሞላ ዛፍ ነው ሲል ተናገረ
አባትየውም እንዲ አሉ፤
"ሁላችሁም ያያችሁትና ያላችሁት ነገር ልክ ነው! ምክንያቱም ደግሞ ሁላችሁም ያያችሁት የዛፉን አንድ ወቅት ብቻ ነውና:: የሰውንና የዛፍን ህይወት በአያቹት በአንዱ ወቅት ብቻ አትፈርጁ:: የነገሮችን ሙሉ ምንነት ምትረዱት በሁሉም ወቅቶች ስታልፋ ብቻ መሆኑንም አትዘንጉ::
በበረዶው ወቅት ተስፋ ከቆረጣችሁ ፤በመኸር ወቅት የሚመጡትን የደስታ ፍሬዎች አታጣጥሙምና!”...
ሰላም ይብዛላችሁ!
@inspiredjourney
@rezuzu
3.8K viewsRèzzé, edited 07:39