Get Mystery Box with random crypto!

ቀን- 30 ፊኛ እና ከፍታ! በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ አየተዘዋወሩ በአየር የተሞሉ እና የተለያ | ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)

ቀን- 30

ፊኛ እና ከፍታ!

በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ አየተዘዋወሩ በአየር የተሞሉ እና የተለያየ ቀለም ያላቸውን ፊኛዎችን ይሸጡ የነበሩ አንድ ትልው ሰው ነበሩ::

ታድያ እኝህ ሰው ገበያው ሲቀዛቀዝ፤ ውስጡ በሂልየም ጋዝ የተሞላ አንድ ፊኛ ወደሰማይ ይለቃሉ:: ይሄንንም ያዩ ህፃናት፤ ፊኛ ለመግዛት ከወላጆቻቸው ጋር ወደ እሳቸው እየተሯሯጡ ይመጣሉ::

በአንድ ወቅት እዲህ ሲያደረጉ የተመለከተ አንድ ህፃን ልጅ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው::

" ጥቁሩን ፊኛ ቢለቁት እንደሌሎቹ ፊኛዎች ወደ ላይ ይወጣል?"

እርሳቸውም...
" ልጄ ፊኛው ወደ ላይ ከፍ ብሎ እንዲነሳ የሚያደርገው ፤የቀለሙ አይነት ሳይሆን በውስጡ ያለው አየር ነው!"አሉት...

ታድያ እኛም በህይወታችን ከፍ እንድንል የሚደርገን፤ በውጣችን ያለን ቀና አመለካከት፣ አስተሳሰብና መልካምነት እንጂ ቀለማችን እና ከላይ ሚታየው መልካችን እንዳልሆነ ተረድተን ወደውስጣችን በመመልከት ክፍ ማለትን እንለማመድ!

ከፍታችሁ ይብዛ!

@inspiredjourney
@rezuzu