Get Mystery Box with random crypto!

ቀን- 31 ፍረጃ! በአንድ ወቅት አንዲት የ 7 ዐመት ልጅ ከወላጅ አባቷ ጋር በመንገድ ላይ | ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)

ቀን- 31

ፍረጃ!


በአንድ ወቅት አንዲት የ 7 ዐመት ልጅ ከወላጅ አባቷ ጋር በመንገድ ላይ እየሄዱ አፕል /ፖም/ የሚሸጥ ሰው ታይና እባቷን እዲገዛላት ትጠይቀዋለች::

አባቷ ብዙ ገንዘብ ባይዝም ፤ባለችው ሳንቲም ለእሱ እና ለልጁ ሁለት ፍሬ አፕል ገዛ::

ታድያ ሁለቱም አፕል ህፃኗ እጅ ላይ ነበርና አንዱን እንድትሰጠው ሲጠይቃት ሁለቱንም አፕሎች በየተራ ገመጠቻቸው!...አባትየው በልጁ ድርጊት በጣም አዘነ፤ ፊቱ ላይ የነበረውም ፈገግታ ሁሉ ጠፋ:: ለኔ ብቻ የምትል ራስ ወዳድ ልጅ መሆኗም አስከፋው::

ብዙም ሳይቆይ ግን ፤ልጁ "አባዬ እየጠራሁ እኮ አትሰማም.... ይሄኛውን እንካ፤ ከሁለቱ በጣም የሚጣፍጠው አፕል እሱ ነው"ብላ በቀኝ እጇ የያዘችዉን አፕል ሰጠችው::

አባትየውም የሚጣፍጠውን ለሱ ለመስጠት እንደሆነ እንደዛ ያረገችው ሲገባው ቀድሞ ባሰበው ነገር ተፀፀተ::...

...ነገሮችናንና ሰዎችን እንዲህ ናቸው ብለን ለመፈረጅ አንቸኩል:: ግዜ መስጠትና ለመረዳት መሞከር ከፀፀት ያድናልና!

ሰላም ለናንተ!

@inspiredjourney
@rezuzu