Get Mystery Box with random crypto!

ቀን- 32 ዳወን ሲንድሮም/ Down syndrome/ ዳወን ሲንድሮም የሚከሰተው አንድ ልጅ ሲ | ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)

ቀን- 32

ዳወን ሲንድሮም/ Down syndrome/

ዳወን ሲንድሮም የሚከሰተው አንድ ልጅ ሲወለድ ሊኖረው ከሚገባ 46 ክሮሞዞም በተጨማሪ አንድ ክሮሞዞም ኖሮት 47 ክሮሞዞም ያለው ሆኖ ሲወለድ ነው።

ይህ ተጨማሪ ክሮሞዞም መኖሩ በሚወለደው ልጅ የአእምሮ እና የመልክ/አካላዊ ገፅታ እድገት ላይ ተፅእኖ እንዲኖር ያደርጋል።

የሚከሰትበት ምክንያት ይህ ነው ተብሎ ማስቀመጥ ባይቻልም ፤ ከዘር ጋር በተያያዘ ማለትም በቤተሰብ ውስጥ ዳወን ሲንድሮም ያለው ሰው መኖር እና የወላጆች የእድሜ ሁኔታ መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቀሳል። ነገር ግን፤ በሃያዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወላጆችም ችግሩ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ጥናቶች ያመለክታሉ ።

አንድ ልጅ ዳወን ሲንድሮም ያለው ወይም የሌለው መሆኑ በእርግዝና ወቅት በሚደረግ አምኒዬስንተሲስ የተባለ ምርመራ ማወቅ ሲቻል 3 አይነት የዳወን ሲንድሮም አይነቶችም አሉ። ( Trisomy 21,Mosaic, Translocation)

ዳወን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ ትምህርት የመቀበል፣ አካባቢን የመረዳት፣ የማስታወስ፣የንግግር፣ እጅና እግርን አቀላጥፎ የመጠቀም እና እራስን የመርዳት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል።

የተቀናጀ ባህሪ እና ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ እና ደስተኛ ሂወት እንዲመሩም ያግዛቸዋል።

በየአመቱም March 21 - የዳውን ሲንድሮም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ተብሎ ይከበራል።


ሰላማችሁ ይብዛ!

@inspiredjourney
@rezuzu