Get Mystery Box with random crypto!

ቀን- 33 ፎቢያ /Phobia/ ፎቢያ የሚለው ቃል መሰረቱ ከግሪክ ቃል ፎቦስ( Phòbos) | ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)

ቀን- 33

ፎቢያ /Phobia/


ፎቢያ የሚለው ቃል መሰረቱ ከግሪክ ቃል ፎቦስ( Phòbos) ሲሆን ፤ትርጓሜውም ፍራቻ እንደማለት ነው::

ፎቢያ ከመጠን ያለፈና ምክንያታዊ ያልሆነ ፍራቻ ሲሆን፤ በዋነኝነት በሶስት ዋና ዋና አይነቶች ይከፈላል::

የመጀመያው አይነት ሶሻል ፎቢያ(Social Phobias) ሲባል ፤ይህም በውስጡ ሰው ፊት ቆሞ ማውራት መፍራትን፣ ከሰዎች ጋር ተቀላቅሎ የመጫውት ፍራቻ እና ሌሎች ከማህበረሰብ መስተጋብር ጋር የተያያዙ ፍራቻዎችን በውስጡ ያጠቃልላል::

ሁለተኛው አይነት ደግሞ አጎራ ፎቢያ (Agoraphobia) የሚባለው ሲሆን ፤ከቤት ውጭ መውጣትን መፍራት፣ ውጭ ብወጣ በሽታ ይዘኝ ይሆን ብሎ ያላግባብ መስጋት፣ በተወሰነ ቦታ ላይ ተገድቦ መኖርን እና የመሳሰሉትን ያካትታል::

ሶስተኛው አይነት ደግሞ፤ ስፔስፊክ ፎቢያ (Specific Phobias) ይሰኛል:: ይህ ደግሞ የተመረጡ እቃዎችን፣ እንስሳትን ፣የተፈጥሮ አከባቢዎችን ወይም ሁኔታዎችን ያለ ልክ መፍራትን ይጨምራል::

በአለማችን እጅግ ብዙ ሰዎች ካሉባቸው ፎቢያዎች መካከል፤
አክሮ ፎቢያ (Acrophobia)- ከፍታን መፍራት ፣
ኦፊድዮ ፎቢያ (Ophidiophobia )- የእባብ ፍራቻ፣
ትራይፓኖ ፎቢያ ( Trypanophobia )- የ መርፌ ፍራቻ፣ አራክነ ፎቢያ ( Arachnophobia) - የ ጊንጥ(Spider) ፍራቻ ጥቂቶቹ ናቸው::

ሰላም ይብዛላችሁ!
@inspiredjourney
@rezuzu