Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወት እና ወቅቶች! ቀን- 29 በድሮ ጊዜ 4 ልጆቹን አንድ ትምህርት ሊያስተምር የፈለገ አ | ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)

ሕይወት እና ወቅቶች!

ቀን- 29


በድሮ ጊዜ 4 ልጆቹን አንድ ትምህርት ሊያስተምር የፈለገ አባት ልጆቹን እሩቅ ቦታ ያለችን አንድ የኮክ ተክል ሄደው እዲያዩ አዘዛቸው::

ታድያ ይሄን እንዲያደርጉ ያዘዛቸው በተለያየ ወቅት ነበር::የመጀመርያው ልጅ በክረምት(በበረዶ) ነበር የተላከው ፣ሁለተኛው በፀደይ፣ ሶስተኛው በበበጋና ፣ አራተኛው ደግሞ በመኸር ወቅት ነበር::

በጨረሻም አባትየው አንድ ላይ ሰብስቦ ስላዩት ዛፍ እንዲነግሩት ጠየቃቸው:: እንዲህም ሲሉ ነገሩት...

የመጀመሪያው - በጣም የሚያስጠላ ዛፍ ነው ፣አንድ ቅጠል እንኳን የሌለው የተጣመመ ዛፍ ነው አለ
2ኛው - በአረንጓዴ እንቡጦች እና አበቦች የተሞላና ተስፋ የሚሰጥ ዛፍ ነው...
3ኛው- የፈኩ አበቦች ያሉበትና ለአከባቢውም ጥሩ ማኣዛ ሚሰጥ በጣም የሚያምር ዛፍ ነው...
4ኛው - እኔ ያየሁት ግን በበሰሉና በተንዥረገጉ ፍሬዎች የተሞላ ዛፍ ነው ሲል ተናገረ

አባትየውም እንዲ አሉ፤
"ሁላችሁም ያያችሁትና ያላችሁት ነገር ልክ ነው! ምክንያቱም ደግሞ ሁላችሁም ያያችሁት የዛፉን አንድ ወቅት ብቻ ነውና:: የሰውንና የዛፍን ህይወት በአያቹት በአንዱ ወቅት ብቻ አትፈርጁ:: የነገሮችን ሙሉ ምንነት ምትረዱት በሁሉም ወቅቶች ስታልፋ ብቻ መሆኑንም አትዘንጉ::

በበረዶው ወቅት ተስፋ ከቆረጣችሁ ፤በመኸር ወቅት የሚመጡትን የደስታ ፍሬዎች አታጣጥሙምና!”...

ሰላም ይብዛላችሁ!

@inspiredjourney
@rezuzu