Get Mystery Box with random crypto!

ቀን- 27 ተመስገን (መቅደላ መኩርያ እንዳካፈለን) ሰው ሆይ፦ 'ሁሌ በተቻለኝ መጠን የም | ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)

ቀን- 27

ተመስገን
(
መቅደላ መኩርያ እንዳካፈለን)

ሰው ሆይ፦

"ሁሌ በተቻለኝ መጠን የምሰብካት ስብከት አለችኝ … የምሬን!!!

ጠዋት ስትነቃ ተመስገን በል። በርዕሷ በረከቶችህን ቁጠር። ተመስገን በል … ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ። ከዛ በኋላ ከአልጋህ ወርደህ ስትቆም ተመስገን በል … በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበራ። ስትንጠራራ ደግሞ … (ደስ አይልም?) …

መንጠራራትን የሰጠህን ተመስገን በል። እንዲህ እያልክ ደሞ ሽንትህ ወጥሮህ ስትሸና … የጠጣኸው ሁሉ ሽንት ሆኖ መውጣቱ … ይኼ ሁሉ የማናውቀው ተዓምር ውስጣችን በመሰራቱ … ተመስገን በል። ከዚያ ደግሞ ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድ መንገዱ ሁሉ ጤና ነው … ታክሲው፣ ሰዉ፣ ምኑም ምኑም፣ ለማኙም፣ መነኩሴውም … ተመስገን በል።

ምክንያቱም … ጀነራል ሰጥአርጋቸው … (ህምምም .. ቆይ አይ አሪፍ ስም ነበረች) … ሰጥአርጋቸው የሚባሉ ጀነራል "ጨለማን ተገን አድርገው" በታንክ ገብተው አገሩ ፀጥ ብሎ ቢቆይህስ… ምን ታደርግ ነበር? … ጠላት አለኝ ይሆን እንዴ? … ተመልሼ ልግባ? … አይ ደግሞ ተመልሶ ገባ ይሉኝ ይሆን? … ምናምን ትል ነበር። አገር ሰላም በመሆኑ ተመስገን በል። እቺን እያልክ ስትሄድ ደግሞ ቆማጣ ስታይ … እረስቼው … መዓት ነው … ይሄ ነው እንግዲህ ሁል ግዜ። ተመስገን በል አሁን … ተመስገን!!!"

ስብኃት ገብረእግዚአብሔር (ከDire Tube ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ እንደወረደ የተወሰደ)

ምስጋና ይብዛላችሁ!

@inspiredjourney
@rezuzu
@positivetunes