Get Mystery Box with random crypto!

ሁለገብ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hulegebmereja — ሁለገብ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hulegebmereja — ሁለገብ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @hulegebmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 97
የሰርጥ መግለጫ

ሁለገብ መረጃ- ቀዳሚ ምርጫዎ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
ContactHere👇
@hulegbmereja_bot
@hulegbmereja

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 21:49:16
ሰበርመረጃ!!
የኢትዮጵያ መከላከያ ቆቦን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።

በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።

 
11 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:23:09
በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመቶ ስለወደቀው አውሮፕላን የአየር ሀይል አዛዥ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ የሰጡት ተጨማሪ መረጃ!!

ከቀናት በፊት በተከለከለ የበረራ አቅጣጫ ከፍታና ወደ ኢትዮጵያ የአየር ክልል መስመር ጥሶ የገባ አውሮፕላን የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ትእዛዝ ባለመቀበሉ በኢትዮጵያ አየር ሃይል ተመቶ መውደቁ መገለፁ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት:-

አይነቱ:- የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ስሪት አንቶኖቭ 26

የመጫን አቅም:- 5 ቶን እና 40 ወታደሮችን ከነትጥቃቸው የሚይዝ

አጠቃላይ ክብደት:- 24 ሺ ኪሎ ግራም

ንብረትነቱ :- "የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት መሆኑ የታመነበት" በሚል ተጠቁሟል።

የተመታበት ሰአት:- ምሽት 3:30 መሆኑን የኢፌድሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌ/ጀ ይልማ መርዳሳ አሳውቀዋል።
 
12 views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 10:43:30
#AddisAbaba

ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ቶታል አካባቢ የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

የከባድ እና ቀላል ጉዳት መጠን ቁጥር ለጊዜው አልታወቀም።

የተገጩ ተሽከርካሪዎች ከመንገዱ እስኪነሱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል
75 views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 10:16:32
ፈገግ የሚያስብል መረጃ
እሁድ ለት አላማጣ ላይ ስብሰባ ላይ የነበሩ የጠላት ወታደራዊ መሪዎች በድሮን ተመተው አላማጣ ሆስፒታል ይገባሉ።
ከቆቦ አቅጣጫ ወደ አላማጣ በኮረምና በማይጨው አቅጣጫ የሚሸሸው መ*ንጋ ያስደነገጣቸው ቁስለኛ ባለስልጣናት 12ሰአት ምሽት ገደማ ወደ ኮረም በአንቡላንስ ይጓዛሉ።

መግቢያ ሲደርሱ ግን የኮረምን ቴክኒክና ሙያ ለመልሶ ማደራጀት ሲሰባሰቡ የነበሩትን ድሮኗ እያደባየች ይመለከታሉ። አጠገባቸው ወዳለችው የማሪያም ቤተክርስቲያን ዘው ብለው ከነ አንቡላንሳቸው ገቡ። እዛው አድረው ጠዋት ላይ ከማሪያም ወደ ኮረም ሆስፒታል ሊሄዱ ቁስለኞቻቸውን አስገብተው በሩ ላይ ሲደርሱ በላይነሽ አመዴ ከደመናው ወርዳ አላማጣ የጀመረቻቸውን ኮረም ላይ ጨረሰቻቸው።

እግዜር ሊቀጣህ ሲሻ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትምሀል። የጁንታው ሚዲያ ደግሞ በንዴት ድሮኗ ንፁሀንን ጨፈጨፈች ብለው የውሸት ዜና ሰሩ ማለት ነው
50 views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 10:14:10
ደብረ ብርሃን ከተማ አዲስ ተቀዳሚ ከንቲባ ተሾመላት

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬው ታህሳስ 12 2014 ዓ.ም ባካሄው 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 32ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ #ካሳሁን_እምቢአለን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

የተቀዳሚ ከንቲባው ሹመት በደብረ ብርሃን ከተማ ብልፅግና ፅህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በአቶ #ቃሉ_ተፈራ ለምክር ቤቱ ቀርቦና በምክር ቤት አባላቱ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
39 views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 10:10:37
29 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 10:10:20 ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመጨረሻው ደብዳቤ ተላከላቸው

የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል እና አድቮከሲ ኔትወርክ #ለፕሬዝደንት_ጆሴፍ_ባይደን የመጨረሻ ግፊት ይሆናል ያለውን ደብዳቤ ዛሬ #ለዋይታሃውስ አስግብቷል።

ሰሞኑን ከበርካታ ኮንግሬሽናል መሪዎች ፣ ከዋይታሃውስ ባለስልጣናት እንዲሁም ከጥቁር አሜሪካውያን የኮንግረስ መሪዎች ፣ እና የሴኔት መሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ሁሉም ኢትዮጵያ በአግዋ (AGOA) መቀጠል አለባት ፣ ምክንያቱም አግዋ (AGOA) የሚያተኩረው በዜጎች የዕለት ተዕለት የኑሮ እድል መሻሻል እንጂ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው ነገር አለመኖሩን አረጋግጠውላቸዋል።

በመሆኑም "የእርሰዎ መሪዎች የተናገሩትን ድምፅ በመስማት ድሃ ዜጎችን ከመጉዳት አሜሪካ እንድትቆጠብ አጥብቀን እንጠይቃለን" ሲል ድብዳቤውን አስገብቶል። ይህን ደብዳቤ የዋይታሃውስ Office of Presidential Correspondence ዴሬክተር የሆኑት ወሮ Eva Kemp መቀበላቸውንም ካውንስሉ በሎቢ ድርጅቱ አማካኝነት አረጋግጧል። በተጨማሪም ለስቴት ዲፓርትመንት ደብዳቤው እንዲገባም መደረጉን የካውንስሉ ፕሬዝደንት ዲያቆን #ዮሴፍ_ተፈሪ አስታውቀዋል ፣ አያይዘውም "የአሜሪካ ፕሬዝደንት ይህንን አግዋ (AGOA) ለፖለቲካ መጠቀሚያ እንዳይውል በማድረግ ውሳኔቸውን በመሰረዝ መልካም ግንኙነትን በሁለቱ ሀገራት መካከል ይፈጥራሉ ብለን እናምናለን" ሲሉም ተናግረዋል።

እንደሚታወሰው ካውንስሉ ባሳለፍናቸው ሳምንታት በርካታ ውይይቶችን እና ጫናዎችን በማድረግ ታሪካዊ ድሎችን በዲፕሎማሲው መስክ ማስመዝገቡ የሚታወስ እና በተለይም HR4350 እንዲሰረዝም አድርጓል። በዚህ ሳምንትም ይህን ውሳኔ ለማስቀየር የሚረዳ ሃቅ የያዘ ደብዳቤ ለ700 የኮንግረስ አባላትና ሃላፊዎች አስገብቷል።

ይህ የባይደንን የአግዋን ውሳኔ በማስለወጥ ኢትዮጵያ በፕሮግራሙ ላይ ተጠቃሚ ሆና እንድትቀጥል ካደረግን ካወንስሉ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ዲያስፖራው ወደ ሃገሩ በገና ሲመጣ የሚያበረክተው የዲፕሎማሲ የገና ስጦታችን ድል ለህዝባችን ይሆናል ሲሉ አቶ #አምሳሉ_ካሳው መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል።
36 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 10:09:45
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው ተባለ

የአገሪቱ የሲል ባለስልጣናትን እና የአገሪቱን ጦር ስምምነት በመቃወም ከሰሞኑ ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሱዳን አካባቢዎች ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የቅርብ ቀናት ውስጥ ትውስታዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር #አብደላ_ሃምዶክ ከሲቪል ባለስልጣናት ሹመት ጋር በተያያዘ አለ ባሉት ጣልቃገብነት ምክንያት ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውንና የጠቅላይ ሚኒስርነታቸውን ስልጣን ሊለቁ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰዓታት ውስጥ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ያስገባሉ ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
39 views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-09 09:01:08
የጸጥታው ምክር ቤት የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት እንዲታይ ወሰነ።

ግብፅ የተለያዩ ምክንያቶች ለመከራከሪያ አቅርባለች። የኢትዮጵያ መከራከሪ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እና በጋራ መልማትን ነው መርህ ያደረገቺው።

የታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ የጉላ ጉዳት የማያደርስ እንደሆን ደጋግማ ብትገልጽም ግብጽና ሱዳን ጉዳዩን አለማቀፋዊና የጸጥታ ጉዳይ አደርገውታል። በጸጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ እንዲታይ የቀረበውን ክርክር ያደመጠው የጸጥታው ምክር ቤቱ ደርድሩ በአፍሪክ ህብረት እንዲታይ ወስኗል።
191 views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-07 10:49:34
በትግራይ ክልል ለአዲስ ግጭት ዝግጅት መኖሩ እየተነገረ ነው

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለአዲስ ግጭት ዝግጅት መኖሩን ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዋች አመለከተ።

ትግራይ ውስጥ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥት ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ወደ ጎን ብለው ለአዲስ ግጭት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ድርጅቱ ዛሬ በማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴ ገጾቹ በአጭሩ ይፋ ያደረገው መረጃ ያሳያል።

በክልሉ ቀደም ሲል በነበረዉ ግጭት ሳቢያ በርካቶች ተፈናቅለው ለረሀብ መጋለጣቸውንም የሚጠቅሰዉ ሂውማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ሕብረት ይኽን ድርጊት ማውገዝ እና የተጠናከረውን በደል ሊያስቆም ይገባው ነበርም ብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የትግራይ ክልል ኃይሎች በብዙ መኪኖች ተጭነው ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ከአማራ ክልል ጋር ወደሚያዋስነው የድንበር አካባቢ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ በትግራይ የሚገኙ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ የዩናይትድ ኪንግደሙ 'ዘ ጋርዲያ' ጋዜጣ ዘግቧል። (አዲስዘይቤ)
157 views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ