Get Mystery Box with random crypto!

ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመጨረሻው ደብዳቤ ተላከላቸው የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስ | ሁለገብ መረጃ

ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመጨረሻው ደብዳቤ ተላከላቸው

የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል እና አድቮከሲ ኔትወርክ #ለፕሬዝደንት_ጆሴፍ_ባይደን የመጨረሻ ግፊት ይሆናል ያለውን ደብዳቤ ዛሬ #ለዋይታሃውስ አስግብቷል።

ሰሞኑን ከበርካታ ኮንግሬሽናል መሪዎች ፣ ከዋይታሃውስ ባለስልጣናት እንዲሁም ከጥቁር አሜሪካውያን የኮንግረስ መሪዎች ፣ እና የሴኔት መሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ሁሉም ኢትዮጵያ በአግዋ (AGOA) መቀጠል አለባት ፣ ምክንያቱም አግዋ (AGOA) የሚያተኩረው በዜጎች የዕለት ተዕለት የኑሮ እድል መሻሻል እንጂ ከመንግስት ጋር የሚያገናኘው ነገር አለመኖሩን አረጋግጠውላቸዋል።

በመሆኑም "የእርሰዎ መሪዎች የተናገሩትን ድምፅ በመስማት ድሃ ዜጎችን ከመጉዳት አሜሪካ እንድትቆጠብ አጥብቀን እንጠይቃለን" ሲል ድብዳቤውን አስገብቶል። ይህን ደብዳቤ የዋይታሃውስ Office of Presidential Correspondence ዴሬክተር የሆኑት ወሮ Eva Kemp መቀበላቸውንም ካውንስሉ በሎቢ ድርጅቱ አማካኝነት አረጋግጧል። በተጨማሪም ለስቴት ዲፓርትመንት ደብዳቤው እንዲገባም መደረጉን የካውንስሉ ፕሬዝደንት ዲያቆን #ዮሴፍ_ተፈሪ አስታውቀዋል ፣ አያይዘውም "የአሜሪካ ፕሬዝደንት ይህንን አግዋ (AGOA) ለፖለቲካ መጠቀሚያ እንዳይውል በማድረግ ውሳኔቸውን በመሰረዝ መልካም ግንኙነትን በሁለቱ ሀገራት መካከል ይፈጥራሉ ብለን እናምናለን" ሲሉም ተናግረዋል።

እንደሚታወሰው ካውንስሉ ባሳለፍናቸው ሳምንታት በርካታ ውይይቶችን እና ጫናዎችን በማድረግ ታሪካዊ ድሎችን በዲፕሎማሲው መስክ ማስመዝገቡ የሚታወስ እና በተለይም HR4350 እንዲሰረዝም አድርጓል። በዚህ ሳምንትም ይህን ውሳኔ ለማስቀየር የሚረዳ ሃቅ የያዘ ደብዳቤ ለ700 የኮንግረስ አባላትና ሃላፊዎች አስገብቷል።

ይህ የባይደንን የአግዋን ውሳኔ በማስለወጥ ኢትዮጵያ በፕሮግራሙ ላይ ተጠቃሚ ሆና እንድትቀጥል ካደረግን ካወንስሉ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ዲያስፖራው ወደ ሃገሩ በገና ሲመጣ የሚያበረክተው የዲፕሎማሲ የገና ስጦታችን ድል ለህዝባችን ይሆናል ሲሉ አቶ #አምሳሉ_ካሳው መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል።